Wednesday, January 8, 2014

አልናግርም ብየ ዝም ብል ልፈነዳ ሆነ ከእንግዲህ ዝም ይላል ማለት ዘበት የመጣው ይምጣ!!!!

eprp

ከግለሰብ ጋር ቁማር የጀመረና የተሸነፈ መንግስት!!
በዕውን ግን እውነትን ማሸነፍ ይቻላልን!! ይህን ሃውልት ሰርቶ አማራና ኦሮሞን ለማፋጀት ከመሞከር ይልቅ ምናለበት አፄ ሚኒሊክ የሰሩትን ጀብድ እና አለም የመሰከረለትን ታሪካቸውን ቢያወድስ ከቢቢሲ ብሶ ባዕድ ያለጠላት መንቀሳቀስ ያለ ጥላቻ ለመግዛት ሳይቸገር መኖር አይችልም ነበር፡፡
አስቡት አድዋ ሲነሳ ሚኒሊክ፤ እምየ ሚኒሊክ ሲነሱ አድዋ ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ታድያ በ1996 አካባቢ መንግስት በራሱ የውሸት መንዣ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያው እኮ ምንትስ ያክል ሜትር ወይም ኪ.ሜትር ያህል የአድዋ ጦርነት የተካሄደበት የአድዋ ኮረብታ ላይ በአንድ ልጅ ዲዛይን አድዋ የሚል ፅሁፍ አስቀመጥን እናም ለቱሪስት መስብዕነት ይጠቅመናል እያለ ፕሮፓጋናዳ ሲነዛ አድንቀን ማለፋችን ረሳንና ነው እምየ ሚኒሊክ እንዲብጠለጠሉና እንዲጠሉ መጣሩ ለእርሳቸውስ ጥሩ ነው ሲጠራ፡፡
ታዲያ እምየ ሚኒሊክ ለሃገር የሰሩት አነሰና ነው ማነሱንስ ይነስ ምን ግፍ ሰሩና ነው አንዲህ የተቆረጠ ጡት በተቆረጠ እጅ ይዞ ሃውልት ማሰራት!!!
ለነገሩ የተቆረጠውን ጡት የያዘው እጅ ራሱ የተቆረጠ ነው፡፡ ምናልባትም ታሪክ ራሱ ምስክር እየሆነ ይሆናል፡፡ የተቆረጠ ጡት በተቆረጠ እጅ መያዙ!! ሆሆሆሆሆሆሆሆሆ…
አርፈን ከተቀመጥንበት ነገር አስተማሩን እኮ ስዎች፡፡ እንዲያው ከጀመርን አይቀር እስኪ ትንሽ እንበል፡፡ ይህ ጦርነት የተካሄደበት ቦታ በአፄ ዘመነ መንግስት ምንድን ነው ከሌላው ሁሉ ልዩ የሚያደርገው፡፡ ወዳጄ አፄ ሚኒሊክ የሰሩት ስራ ጦርነት ሄዶ ማሸነፍ በወቅቱ ጠላት የሚሉትን የታጠቀ አካል ማሸነፍ ብቻ ነበር እንጅ ጡት ቆረጣ አደለም የሄዱት፡፡ እዩትላችሁ እንዴት ኢትዮጵያዊውን ኢትዮጵያዊ ይቆርጠዋል ይገድለዋል ከሆነ ይህ ከወቅታዊ እና ዘመን ባበበበት ምዕተ አመት እንኳን ተቀበይ የሚሆን አደለም ይባስ ብሎ ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡
ይሁን ካልንማ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግስት ተብየ አውደልድል ቡድን፤ ለምን ነፍጥ ያነሱ ያውም ለዲሞክራሲ ራሳቸውን አሳልፈው ለሰጡ፤ የሞቾትና ያማረ የስኬት መስመራቸውን ህይወታቸውን ትተው በዱር በገደሉ ለህዝብ ደህንነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህ እና ነፃነት የሃገራቸው ዜጋ ከግፍ አገዛዝ ነፃ ሆነው ለማየት የሚኳትኑትን ወገኖቻችን እህቶቻችንና አባት እናቶቻችን ለምን እስከነፍሳቸው ከተማ ለከተማ በመኪና እንደ ጩቤ ከሚበሳሳ ጠጠር መንገድ ላይ ይጎተትታል፡፡
ለምን እንደዛ አሟሟት ይገደላሉ ካሉ ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ከምንም የማይፃፍ የረከሰና ከሰውኛ እውነታ ወይም ተፈጥሯዊ እውነታ ፍልስፍና መውጣት ነው፡፡ ጦርነት ጦርነት ነው ወዳጄ እድለኛ ይሞታል እድለኛ ይድናል 50/50 ነው፡፡ ሁለቱም መሞትም መዳንም መቆረጥ መበጣጠስም ዕድል ናቸው፡፡ በጦርነት ጡታቸው ተቆረጠ ተብሎ ታሪክ የለም ታዲያ እንዲህ ካሰብንማ ስንተኩስም ሆነ ጠላታችንን ስንወጋ ነቀላ መረጣ ልንገባ ነዋ እህህ፡፡
ነቀላ ነቀላ ነቀላውን በለው
አለ ያገሬ ሰው፡፡
ሆሆሆሆሆሆሆሆሆ…ሰው ወዶ እኮ አደለም ለቅሶ ላይ የሚስቅ እናንተየ!!!
ለማንኛውም ኢህአዴግየ መጠየቂያሽ ጊዝ እጅግ በጣም ቅርብ ነዋ ይህ ሁሉ ያንች የእንጀራ እናታችን ሴራ ነዋ ከነቃን ቆየን እኮ እንዲያው ዝም አልን እንጅ ክድን ብሎ ይብሰል ብለን፡፡ እምየ ሚኒሊክስ ምንም ያድርጉ ምንም ከበርካታ አስርት አመታት በፊት ሰሩት ስለተባለው ጦርነት እነድንጨነቅ እና ተጨንቀንም እንዲህ አይነት ገተት ከመጣ አንች ግን ወዮልሽ ወያኔ ጉድሽ ነው፡፡
የ 120000 ወንወድሞቻችን ያላንዳች አላማና ዕቅድ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ያላናዳች ፋይዳ ፈሶ የቀረው ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፋረድህ ይሆናል፡፡ ቢሊቭ ሚ ይህ እና ያኛው አይገናኝም፡፡ የምምምምምም…ላችሁንንንንንን ስስስስ…ሙሙኝኝኝኝኝኝኝኝ በጦርነት የመመቻ ቦታ አይመረጥም፡፡ ለዛም ነው እናንተ ጡት ይገርማችኋል ጭንቅላቱ ተበጥሶ አናቱ ፈርሶ በህይወት ሲንፈራፈር ቆይቶ በከባድ ስቃይ ህይወቱ የሚያልፍ ሞልቷል፡፡ ስለዘረኝነት ምናምን ከሆነ እመኑኝ እኔ በ1997 ዩኒቨርሲቲ ከመግባቴ በፊት አማራ ልሁን ኦሮሞ ትግራይ ልሁን ከንባታ አፋር ልሁን ወላይታ ሶማሌ ልሁን ምን አንዳችም የማውቀው አልነበረኝም፡፡ እድሜ ለመንግስታችን ተጫወተብኝ ከዚያ ጊዝ ጀምሮ ግን ህሊናየ ቡጀሌ በቡጀሌ ሆኗል፡፡ ለዚህም አንድ ቀን የምፋረድበት አቅም እስካገኝ አመሰግናለው፡፡ በ1997 ለተራ ስልጣን ሲባል የተሻለ ስትራቴጅ አምጥቶ ተወዳዳሪ ከመሆን ይልቅ ብሄር ሚላቸውን ያለናታቸው የማይሆንላቸውን ቡችሎች ማባላት ጀመረ ተሳካለትም ለጊዜውም ቢሆን አሁንም መባላታችን መልሶ ማስተካከል የሚችል ምትሃታዊ ሃይል እስኪመጣ ይቀጥላል ግን ዘላቂ አይሆንም፡፡ በመሰረቱ ማንም በኢትዮጵያዊ አንድነታችን የሚለየን ሙከራ በግለሰብም ቢሆን በቡድን አደለም ጡቱ ምኑም ቢቆረጥ ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡
ስዎች ሞኝ አትሁኑ አሜሪካ እኮ ሊበራል ዲሞክራሲን ብትከተል ሁሉንም ሴትል አድርጋ እርግጠኛ ከሆነች በኋላ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደማይሞከር ስለምታውቅ ነው ለዛም ነው አለማዊ የሆነች አሜሪካ ውስጥ ዘር የሌለው ሀገር ማን አለና፡፡ ይሕ ነው ብልጠት ይሕማ የግለሰቡን መብት መገርሰስ ነው እንዳትሉ፡፡ የግለሰቦች መብት ይከበር እናዳትሉ ብየ ነው፡፡
ስለዚህ ለሃገር አንድነት አደለም አንድን ቡችላ መብት ለመንካት አደለም በመገንጠል ስም እንኳን ስንት ትውልድ የማይተካው የበላይ ወጋኖቻችን አልቀው አደል በራሱ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፡፡ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ ይህን ሴራ የመበታተንና የመከፋፈል እንዲሁም የ ማግለል ሴራ ትግራይ ላይ ተሞክሮ ማለትም የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ሀዝብ የተሻለና ምርጥ ህዝብ አድርጎ ለመቁጠር ሲሞከር በርካታው የትግራይ ህዝብ ኖ ኖ ኖ አይሆንም ሌሎች ጋር ነው ኢትዮጵዊ የምንባል ብቻችን አደለም በማለት ጥንካሬያቸውን ሲያሳዩ የተበከሉ የተማረኩም የሉም ለማለት አደልም፡፡
በአጠቃላይ ግን በትግራይ ህዝብ ያልተሳካውን ሴራ በኦሮሞ ህዝብ ላይ መጀመሩ ነው እንግዲህ ይህ በቴወድሮስ ካሳሁንና መሰሎቹ አስመስሎ በሳይጣናዊው ጃዋር ተብየ ደደብ መተላለፊያነትና እባብነት ይህ ውዥንብር እንዲመጣ ያደረጉት፡፡ ነገር ግን በዚህ ዘመን ከ96 ሚሊዮን ህዝብ ምናልባት በሽህዎች ማግኜታቸው ብርቅ አደለም፡፡ ግን አይሳካም የተጋደመ ሁሉ አላንቀላፋም ያንቀላፋም አልሞተምና ነው ነገሩ፡፡
ይህ ሲከሽፍ ደግሞ ወደየት ይሄዱ ይሆን ወደ ሶማሌ ክልል ወይስ ወደ አማራ ወይስ ወደ ደቡብ ወዴት ይሆን ለማንኛውም ተከታትለን ዲባቅ እንመታለን ጀመርን አደል ገሃዳዊ ትግላችን፡፡
ለነገርማ አለ ኢትዮጵያዊ
ኤኒ ወይስ ወደ ጉዳየ ልመለስና
እንዴ ሰው ምን ነካው!!!
መችም ከዚህ በታች ዝቅ ብሎ ማስረዳት ሳይከብድ አይቀርም፡፡ ታዲያ ማን ይሙት አሁን የሁለት ህዝቦችን ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሲተባበሩና በውጭውም ይሁን በአገር ውስጥ አየሁ እና ለኔ ነገ ስጋት ናቸው እርስ በርሱ ካልተናቆረ በማለት አንድ መንግስት ነኝ የሚል ሃይል አንድን ብሄር ከሌላ ብሄር የሚያናቁር ተራ ሃውልት አሰርቶ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል!!!
ኣረ ተው ስዎች አንድያችን መሳቂያ መሳለቂያ ሆንን
እንደ ሰፈር ባልቴት ሆኜ ልምከር እንጅ አልሆነልኝ
እዩማ ልጆቼ…እኔ በዚያ ሰዓት ነበርኩኝ ባልቴት ነኝ ብየ ላስብና ማለቴ እንጅ አልነበርኩም ግን እድሜ ለታሪክ ማለቴ ያን ጊዜ የአጤ ሚኒሊክ ጦርና የአርሲ ሙስሊሞች ሲገጠሙ…የአርሲ ሙሲሊሞች ጦራቸውን ሰብቀው…ጎራዴያቸውን ስለው የአጤ ሚኒሊክን ሰራዊት ካገኙት ቦታላይ ከቻሉ አንጀቱን አውጥተው ለማነቂያ ገመድ ለመፍተል ካልተቻለም ሴት ወንዱን አንገቱን ቆራርጦ በመጣል ታሪክ ሊያስመዘግቡና የእስላም መንግስት ለመመስረት ያ ማን ነው የሚባል ጨካኝ መሪያቸውን ከፊት ከፊት አድርገው እየፎገሉ መጡ፡፡
እናማ ይገርማችኋል የእነዚህን ወታደሮች መምጣት የሰሙት ሃገሪቱን አንድ የማድረግና ድንበሯን የማካለል ስራ ላይ እንዲሁም ባንዳዎችን የማጥራት ስራ ላይ የነበሩት የሽዋው እና ኢትዮጵያን ከጎንደሬው ግን ኢትዮጵያዊው እጤ ቴወድሮስ የተረከቡት ብርቅየና በወቅቱ ብቸኛው ንጉስ አጤ ምንልክ ውስን ጦራቸውን ይዘው ሳያታሰብ ዘው ብለው በርካታ ወታደሮቻቸውን አጥተው ጠላት ያሉትን ማሸነፍን ግን አላማ የሌለውን ሃይል አፈር ዱሜ አብልተው፡፡ ድል ነስተው ወደ መሃል ሃገር ተጓዙ፡፡ ልብ በሉ ወደ ሃገራቸው አደለም የተመለሱት ወደ መሃል ሃገር እንጦጦ ማርያም ነው፡፡
ግን የታሪክ ፀሃፊያን ስህተት የሚጀምረው ከዚህ ነው በርካታ መፅሃፍት ወደ ሃገራቸው ብልው ነው የሚፅፉት ሃገራቸውማ ሃገራቸው ነው ያሉት ወደ ሃገራቸው የመጣውን ከዛው እርሳቸው ከሚያስተዳድሯት ሀገራ ኢትዮጵያ የወጡ ተላቶቻቸውን ጨረሱ፡፡ ጨረሱ የሚለው አሸነፉ በሚል ይተካልኝ፡፡ ድል ነሱ ለማለት ነው፡፡ እነዚያኛው ደግሞ ድል ተነሱ ወይም ተሸነፉ ይባላ ታዲያ!!!
እናም አጤው ከሰራዊታቸው ጋር እየፎገሉ ሄደው እየፎገሉ የተመለሱበት ጦርነት ሆነና ተመልሰው ሃገራቸውን አአንድ ወደ ማድረግና ወደ ማዋሃድ እንዲሁም ባናዳን ወደማጥራት ብሎም ድንበሯን ወደ ማካለል ተመለሱ፡፡ እላችኋለው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በዚህ አንዳንድ ማፈሪያ ተምሬያለሁ ባይ አንድ ጥይት ቢጮህበት እየቀዘነ በሚሮጠው ሁሉ ሲቪላዊ መወደሻ አድርገው የ ሚፀዳዱብን፡፡ ይቅርታ እኔ ላይም ለምን እንዲህ አይነት አስፀያፊ ቃል ተጠቀምክ ብላችሁ ጦርነት እንዳትከፍቱብኝ፡፡
አስቡት የተካሄደው ጦርነት ያሸነፉት ሚኒሊክ የተሸነፉት ሸፋቾች የቆሰሉ የሞቱትና የጋዩት አናታቸው የተፈረካከሰው ጡታቸው የተቆራረጠው እግራቸው የተሰባበረውና የተበታተነው ሆድ እቃቸው እንደ ገመድ እየወጣ የተጎተተው ወታደሮች ከሁለቱም ወገን ታዲያ ለምን የተሸናፊው ወገን በነዚህ እውር መሪዎች እየተመሩ በቅጡ እንኳን መመራት የማይችሉ በሚቀድሙበት ሁናቴ እንዴት እንጃዋር በመሩት ቡድን አንድ ዘፋኝ ግላዊ አስተሳሰብ ላይ ለተመሰረተ ዘፈን ወይም አባባል ተሳሳተም አልተሳሳተ አያገባኝም ይህን ያክል የምትነሽሩን/ የምታምሱን/ ኣረ ምን አደረግን ምን አደረግን፡፡
ሌላው ይቅርና እንኳን ለእምየ የህችን የመሰለች ሃገር ላስረከቡን የዘመናዊነት መቀነትን ላጎናፀፉን ለሂትለርና ለፋሽሽቶች እንኳን ተዘፍኖ አደል እንዴ፡፡ መንግስትስ ቢሆን ሚኒሊክን እንርሳቸው ይረፉበትና መንግስት አሁን ኢህአዴግስ ቢሆን አሁን በዚህ አምባገነን አገዛዝህ ላይ እንኳን እንኳን አደለም በርካታ ወታደር አስከትሎና አንድ ሽፍታ ብቻውን ብታገኙ አደልም ጡት ኖሮት ጡቱን ጠብሳችሁ ብትበሉት እየተለተላችሁ ብትበሉት ትጠግባላችሁ፡፡
እንዲያው አጼ ሚኒሊክም ስህተት ሰሩ ማለት ባንችልም እንኳን ሰሩ እንበልና
እንደጠላቶቻቸውና የራሳቸውን ድካም ጠንካራውን ወደታች በመጎተት የጎለበቱ በሚመስላቸው ደደቦች እንደሆነ ማን ይሙት አጼ ሚኒሊክ ካለምክንያት ሊጨክኑበት በማይችሉት ህዝብ ላይ ቆረጡት ከተባሉት ጡት እና በአንድ ቀን ብቻ ከ30 ሽህ ህዝብ ፋሽሽት ጣሊያን ከጨረሰው ኢትዮጵያዊ ያውም ለአንዲት ኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ሲታገል ከነበረው እና ባንድ ቀን ከጨረሰው ታሪክ የትኛው ይከፋል!!! የትኛውስ አስቀያሚ ታሪክ ነበር በመጥፎ እና አይረሴነቱ ሊወሳ የሚገባው የነበር፡፡
አንድ ነገር ቁርጥ ያለ ልንገራችሁ እናት ሃገራችንም ሆነ አባት ሃገራችን እንደርዕዮተ አመለካከታችን ሊበጣጥሥና ሊቆራርስ የሚያስብ ማለትም ሊገነጥል የሚመጣ አካል ገደል ይግባ፡፡ አደለም ጡቱን ምኑንም ከመቆራረጥ አንድ በኢትዮጵያ የሚያምን በአንዲት እናት ወይም አባት ሃገር በሚያምን መሪ አደልም በግለሰብም አይማርም፡፡ ስለዚህ ታሪክን ምንበብ ብቻ ሳይሆን ታሪኩን ማን ፃፈው መች ተፃፈ ዋቢ መፅሃፍቶቹ ምን ምን ናቸው ብሎ ማሰብ ግድ ይሆናል፡፡ ያለዚያ ታሪክና ተረት አፈታሪክ ይዳቀሉና ከዚህ የባሰ ውጤት ያስከትላሉ፡፡
መንግስታችን እባክህን ለዚህ ያበቃህን የእምየ ሚኒሊክ ታሪክ ከማጠልሸት ብሎም የ ተሳሳቢና ተፋቅሮና ተከባብሮ ኖረውን ህዝባችን ከእቃ እቃ ያልተናነሰ ስልጣንክን ለማቆየት ስትል ከምታበላሽብን ይልቅ እባክህን የቀረው ብሄራዊ ጥቅም ይቅርብን በአንድ ቀን ህዝባችን ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች እና ዘረኛ ያልሆኑ ከኢትዮጵያዊነታቸው ውጭ ምንም የማያውቁትን ወገኖቻችን ደም ያፈሰሰውን የጀግናው ብፁህ አባታች አቡነ ጴጥሮስን ደም በሰላሳ ጥይት ያፈሰሰውን ጠላታችን ሁሌም በቆሻሻ ታሪክነቱ እንድናስታውሰው እባክህን የግራዚያኒ ፋሽሽቱን ሃውልት ጭንቅላት ብቻ ይዞ አሰራልንና ጨፍረን እናስመርቀው፡፡
አሁንም ቢሆን ይህ የተቆረጠ ጡት ዬያዘ የተቆረጠ እጅ አጥፋልን ለኢትዮጵያዊነታችን ፈተና አታብዛብን፡፡ እባክህን ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ላትችል ለማፈራረስ አትሞክር ትዝብት ብቻ ላይ ነው የሚጥልህ፡፡
ተው ተው ተው መንግስታችን ሳትሆን ሳይጣናዊ መንግስታቸው ኣረ ተው ደንበራች እየቆረስክ ለሃብታም ስዎችና ለሃብታም ሃገራት አትስጥብን እኛ እርቦናል እኛ ጠምቶናል፡፡
ሰዎቻችን ሸጥክ፤ መሬታችን ሸጥክ፤ ክብራችን ሸጥክ፤ ማንነታችን ሸጥክ፤ ጭንቅላታችን ሸጥክ፤ አንድነታችን ሸጥክ፤ ኢትዮጵያዊ ፍቅራችንን ሸጥክ፤ መከባበራችንን ሸጥክ፤ መነፋፈቃችንን ሸጥክ፤ ምን ቀረህ ምን ቀረህ ተው እናቴ ትሙት አታበላላን ተው አታበላላን
ተው ጭንቅላታችን ላይ ውረድ!!!
 http://www.eprp.com/PressReleases/MeglechaEP_December12013.pdf

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

No comments:

Post a Comment