Wednesday, January 8, 2014

ኢትዮጵያዊ ዜግነቴን ማንም የሰጠኝ ሳይሆን የእግዚአብሔር የፈጣሪዬ ስጦታ ነው አከብረዋለሁ እንከባከበዋለሁ እውደዋለሁእኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ ! በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ መንግስታቶች በዘሬ ወይም በሃይማኖቴ ምክንያት በደሎችን በህዝባችን እንዳይቀጥሉና መቀጠል እንደሌለበት ስለማምን እቃወማቸዋለሁ አወግዛቸዋለሁ እነሱ ደግሞ ሊያስሩኝ:ከሀገር ሊያባርሩኝ እንደውም ሊገድሉኝ ሁሉ ይችላሉ ግን ኢትዮጵያ ሀገሬን እንድክድ እና እንደጠላ ሊያድርጉኝ በፍጹም አይችሉም ! ኢትዮጵያዊ ዜግነቴን ማንም የሰጠኝ ሳይሆን የእግዚአብሔር የፈጣሪዪ ስጦታ ነው አከብረዋለሁ እንከባከበዋለሁ እውደዋለሁ :: አምባገነን ሃይማኖት ወይም ዘር አይለየውም:: ስለዚህ አምባገነንነትን እቃወማለሁ!!!

ባለፉት 22 አመታት በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት፦
1.የእምነት ነጻነቶችን ማክበር ባለመቻሉ፤ በሀይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ስለምቃወም
2.የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን ባላቸው አመለካከት ብቻ በሽብርተኝነት ስም በማሰሩና ግፍ መፈጸሙን ስለምቃወም
3.የነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞችን በጹሁፋቸውና በአመለካከታቸው ብቻ በሽብርተኝነት በመፈረጃቸውና ለእስረ መዳረጋቸውን ስለምቃወም
4. ዜጎች በሀገራቸው በየትኛውም ቦታ ተዘዋውረው የመኖርና የመስራት ህገ-መንግስታዊና ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ ከኖሩበት ቀዬ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፎ እንዲባረሩ መደረጋቸውን ስለምቃወም
5.ሌሎች ዲሞክራሲዊና አስተዳደራዊ በደሎችን ስለምቃወም

ህገ-መንግስታዊ መብቴ በሆነው ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ከማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር በመቆም መንግስት እያደረገ ያለውን ጭቆናና የመልካም አስተዳደር ችግር ለአለም ሕዝብ አጋልጣለሁ ፡፡

No comments:

Post a Comment