Monday, January 13, 2014

በህዝብ ስም ተደብቆ ጠባብነትን ማራመድ ክሽፈትን ያመጣል እና እንጠንቀቅ:

ኢትዮጵያዊነት የሚለው ቃል እኮ የኢያንዳንዳችን መከበሪያ እና መኩሪያ እንጂ ማፈሪያ አይደለም:: ምንሊክ ሳልሳዊ:-ለአመታት ታገልን የሚሉ ከወያኔ ጎን እየፈሉም ያሉ እና የከሰሙ የብሄር ድርጅቶች በታገሉባቸው አመታቶች ከወሬ ውጭ ለሃገሪቱም ይሁን ለሚጠሩት ብሄር ምንም የፈየዱት ነገር የለም:: ያመጡትም ነጻነት የለም ይብሱኑ እርስ በእርስ ከማጨፋጨፍ ውጪ እና ህዝብን ለእልቂት ከመዳረክ ውጪ ምንም ያመጡት ውጤት የለም:: በብሄር ስም መታገል እና ዘረኝነት ማራመድ ለብሄራዊ ጭቆና በር መክፈት ነው :: ገዢው ፓርቲን ሕወሓትን እንኳን ብትመለከቱት ለትግራይ ህዝብ የፈጠረው አዲስ ነገር የለም:: የትግራይ ህዝብ በዘመናዊ ጭቆና ፍዳውን እያየ ነው:: እኛ በጋራ እስካልታገልን ድረስ ለውጥ አይመጣም:: ከሃገር ሲወጡ የወያኔን ጽዋ ጠጥተው እዚህ ከመጡ በኋላ የሚከረበቱ አስመሳይ ተለጣፊ ፖለቲከኞችን ማስወገድ ግዴታችን ነው:: ኢትዮጵያዊነት የሚለው ቃል እኮ የኢያንዳንዳችን መከበሪያ እና መኩሪያ እንጂ ማፈሪያ አይደለም:: ከሌላው አለም የምንወስደው ትምህርት ምንድን ነው??ሌላው ዜጋ ሃገሩን እና ሌላውን ወገኑን እንዴት ነው የሚወደው?? የዘር እና የቀለም ልዩነት እየተወገደ በሚሄድበት በዚህ በሰለጠነው አለም ላይ ትላንትን እያሰብን የምንኖር ሰዎች ግንዛቤያችንን ማስፋት ይጠበቅብናል:: ኢትዮጵያ ምን አደረገችልኝ የሚል አነጋገር የሚናገሩ ጠባብ ብሄርተኞች አላማቸው የት ላይ እንደሚያርፍ ራሳቸው አያውቁትም::ኢትዮጵያ እኮ አንዲት ግኡዝ አካል ነች :: ተንቀሳቅሳ ላንተ ላንቺ እና ለእናንተ የምትፈይደው ነገር የለም ምድሯን እየረገጥን እየተማርን እየኖርን ያለነው እኛ ነን ::የእኛ ስራ ደሞ አገርን ከክፉ ገዢዎች አድነን ራሳችንን ነጻ በማውጣት የወገንን እምባ ማበስ እንጂ በወገን እንባ እና ደም መነገድ አላስፈላጊ ኪሳራ ያስከትልብናል ለኢትዮጵያ ምን ሰራሁላት ለወገኔ ምን አደረኩለት ብለህ ጠይቅ እንጂ እንደ ከብት አታጓራ:: በህዝብ ጥያቄ ስም ተደብቆ ጠባብነትን ማራመድ ክሽፈትን ያመጣል እና እንጠንቀቅ:: በየትኛውም አገር ያለን ኢትዮጵያውያን በጡት ነካሾች የታሰበውን ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ልንቃወም ይገባል::
#‎MinilikSalsawi‬ 

No comments:

Post a Comment