Tuesday, January 14, 2014

‹‹ ኢትዮጵያዊነት ማለት አንድነት ነው!››




















በሶማሊያ ችግር አብረን ስንጨነቅ
በይጎዝላቪያ ቆመን ስንሳለቅ 
በእንጀራ አባታችን በሩሲያ ስንስቅ 
ከእነሱ ሳንማር ካለፍነው በዋዛ 
አርባ መንግስት ሆነን ክልል ስናበዛ 
እንዳንጠያየቅ ፓስፖርት እና ቪዛ ››
የወንድ ቅድመአያቴ ከመንዝ ተነስቶ 
በቾ ተቀመጠ አንድ ኦሮሞ አግብቶ 
ያቺ ኦሮሞይቱ የኔ ሴት ቅድመ አያት 
ልጅ ወልዳ አሳደገች የኔን እናት አባት 
ለአቅመ አዳምም ስትደርስ በጥሩ እንዳደገች
ከመቀሌ  የመጣ አንድ ትግሬ አገባች 
‹‹ ኢትዮጵያዊነት ማለት አንድነት ነው!››

በሶማሊያ ችግር አብረን ስንጨነቅ
በይጎዝላቪያ ቆመን ስንሳለቅ
በእንጀራ አባታችን በሩሲያ ስንስቅ
ከእነሱ ሳንማር ካለፍነው በዋዛ
አርባ መንግስት ሆነን ክልል ስናበዛ
እንዳንጠያየቅ ፓስፖርት እና ቪዛ ››
የወንድ ቅድመአያቴ ከመንዝ ተነስቶ
በቾ ተቀመጠ አንድ ኦሮሞ አግብቶ
ያቺ ኦሮሞይቱ የኔ ሴት ቅድመ አያት
ልጅ ወልዳ አሳደገች የኔን እናት አባት
ለአቅመ አዳምም ስትደርስ በጥሩ እንዳደገች
ከመቀሌ የመጣ አንድ ትግሬ አገባች
ይህ የአያቶቼ ልጅ ይህ የተወለደው
አባቱ ነው ትግሬ አማራ ኦሮሞ ነው
ለአቅመ አዳምም ሲደርስ አንዲት ውብ ልጅ ወዶ
ልትኖር አዲስ አበባ የመጣች ከሶዶ
ጉልቻ ጎልተው ሶኖሩ ተዋደው
አብረው ፍሬም አዩ እኔ ወንዱን ወልደው
ኦሮሞም ትግሬም ነኝ ጉራጌ ም አማራ
ዘሬ ማን ሊባል ነው ማን ተብየ ልጠራ
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው
…………………..ከታማኝ በየነ…………………..
ይህ የአያቶቼ ልጅ ይህ የተወለደው 
አባቱ ነው ትግሬ አማራ ኦሮሞ ነው
ለአቅመ አዳምም ሲደርስ አንዲት ውብ ልጅ ወዶ
ልትኖር አዲስ አበባ የመጣች ከሶዶ 
ጉልቻ ጎልተው ሶኖሩ ተዋደው 
አብረው ፍሬም አዩ እኔ ወንዱን ወልደው
ኦሮሞም ትግሬም ነኝ ጉራጌ ም አማራ 
ዘሬ ማን ሊባል ነው ማን ተብየ ልጠራ 
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው 


                                                      ከታማኝ በየነ


No comments:

Post a Comment