Friday, January 3, 2014

ከሙስና ጋር በተያያዘ ሲፈለጉ የነበሩት አቶ ጌቱ ገለቱ እንግሊዝ አንደሚገኙ የቅርብ ሰዎች አረጋገጡ።(እየሩሳሌም አረአያ)


ሼህ አላሙዲ ከምክትላቸው አቶ አብነት እንዲሁም አበበ ባልቻ (የሰውለሰው አስናቀ) ጨምሮ በበርካታ የቅርብ ሰዎቻቸው ታጅበው ዋሽንግተን ዲሲ ከመጡ 15 ቀን አለፋቸው። ከአገር ቤት ዘፋኞችን ጭምር አስመጥተዋል። ዲሲ በሚገኝ አንድ የምሽት መዝናኛ አዲሱን የፈረንጆች አመት በተለየ ግብዣና ፈንጠዝያ አሳልፈዋል። በዚህ ምሽት እዚህ ያሉት የገዢው አምባሰደርና ተከታዮቻቸው ያሳዩት የነበረው እጅግ ራስን የሚያዋርድ ተግባር በአንዳንድ ታዳሚዎች ግርምትን ፈጥሯል። ባለሃብቱና ተከታዮቻቸው አሜሪካ ከመጡ ዛሬ 18 ቀን ሆናቸው። ይህ ያልተለመደ በመሆኑ የተለያዩ ወሬዎች መናፈሳቸው አልቀረም። ለመሆኑ “ምክትላቸው ከጉምሩክ ጋር በተያያዘ ስለሚፈለጉ ነው” የሚባለው ወሬ ነው ወይስ…?…አንድ ለባለሃብቶቹ ቅርብ የሆነ ሰው እንደነገረኝ ሁለት ነገሮች እንደሚወሩና አንደኛው ከላይ የተገለፀው ሲሆን ሌላኛውና እርሱ የሚያውቀው ምክትሉ ቦርጭ (ፋት) ለመቀነስ ሲሉ 7 አሜሪካዊያን እንደቀጠሩ እንደሚያውቅ ነግሮኛል። ሌሎች መረጃዎች ቢኖሩም… አሁን ማለፍን መረጥኩ። …ከሙስና ጋር በተያያዘ ሲፈለጉ የነበሩት አቶ ጌቱ ገለቱ እንግሊዝ አንደሚገኙ የቅርብ ሰዎች አረጋግጠዋል። ግን ጌቱ ብቻ ለምን?…ሲሉ ጠይቀዋል።…እስር ቤት የተወረወሩት የኬኬ ባለቤት የደርጉን ባለስልጣን ሻ/ል ፍቅረስላሴ ወግደረስን በየሳምንቱ እየሄዱ ይጠይቁትና ከተፈታም በኋላ ቤትና መኪና ገዝተው እንደሰጡት ተነግሯል። እስሩን ከዚህ ጋር የሚያያይዙት አሉ። እውነቱ የቱ ነው?…ሌላው ረቡዕ ማታ የፈረንጆቹ አዲስ አመት የሚገባበት ቀን ነበር። የፌስቡክ ወዳጄ ቢኒያም ታምራት “ለፈረንጆቹ 2014ኒው ይር እኔና እናንተን ምን አገባን? ” ያለው እውነት ነው። ረቡዕ ማታ በዲሲ ሃበሻ በሚበዛበት መንደር 20 ሃበሾች በስካር ተነሳስተው ከመደባደብ ባለፈ በድንጋይ እስከመፈነካከት ደርሰዋል። የሚገርመው ድንጋዩን ከየት እንዳመጡት ነው፤ በዚሁ ድብድብ ሶስት ሴቶች በስለት ተወግተው ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ደርሶ ሁሉንም ወደ እስር ቤት መውሰዱ ታውቋል። ሽጉጥ የተተኮሰ ሲሆን ከማን ወገን እንደተተኮሰ ግን አልታወቀም። ..የተፈፀመው ነገር አሳፋሪ ነው። ብዙዎች ተጎድተዋል። በጩቤ ሴትን ልጅ መውጋት (ያውም አሜሪካ) ምን አይነት የጭካኔ ድንቁርና ይሆን?….ጥፋተኞቹ ከታሰሩ በኋላ ከአሜሪካ እስከመባረር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። የሚያሳዝነው አንዳንዶች ትንሽ ሲቀምሱ .መደባብደብን እንደትልቅ ጀብድ መቁጠራቸው ነው። በአሉ የነጮች ሆኖ ሳለ የሚፈነጥዙት፣ ስለት እስከመማዘዝ የሚደርሱት የእኛው ጉዶች። ይህን ምን ይሉታል?…

No comments:

Post a Comment