Thursday, January 16, 2014

የትግራይ ሕዝብና ሕውሓት የተለያዩ መሆናቸውንና የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ የተለየ ጥቅም አላገኘም , ይህ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ አባባል ...


የትግራይ ሕዝብና ሕውሓት የተለያዩ መሆናቸውንና የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ የተለየ ጥቅም አላገኘም፡፡ ይህ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ አባባል ነው፡፡ ተመስገን በችኮላ የጻፈው፣ አሁን ግን እኔ ይህችን ማስታወሻ ስጽፍለት አንገት የተፈጠረው አዞሮ ለማየት ነው እንዲሉ ሃሳቤን ይጋራል ብዬ አስባለሁ፣ ምክንቱም  1- 10 የዘረዘርኳቸው ሁሉ እርሱም በየዕለቱ በአካባቢው የሚያያቸውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ያሉበት ሕወት ነው፡፡
1. ትግራይ ውስጥ የተሠራውና እየተሠራ ያለው ብዙ የአገር ሃብር የፈሰሰበት ልማት ዓይነት በየትኛው የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ከምባታ፣ ወዘተ   ሠራ አይተሃል፡፡ሰመራ ወይም አፋር ብትለኝ አልቀበልም ምክንያቱም ወያኔ ወደፊት አፋርን ከትግራይ ጋር ለማዋሃድ ዕቅድ እንዳለው
ስለማውቅ ነው፡፡
2. ለምን የአማራ ቄስ ወይም የኦሮሞ ሙስሊም ኢማም በትግራይ ሲሠሩ አይታይም፡፡
3. ትግራይ ውስጥ ለምን ጉራጌ ወይም የሌላ ብሔረሰብ ነጋዴ ሲንቀሳቀስ አይታይም፡፡
4. ሰሞኑን በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢ ድርጅት መ/ቤት ውስጥ 13 ቁንጮ ባለሥልጣናት ሲሾሙ ሁሉም ትግሬዎች ነቸው፡፡
5. የወያኔ ጀነራሎች ሁሉም ትግሬዎች ናቸው፡፡
6. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለወታደሮች መኖሪያ በተሰሩ ሕንጻዎች ውስጥ የሚኖሩት ወታደሮች 97 ከመቶ ትግሬዎች ናቸው፡፡
7. በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች የቤክርስቲንና የመስጊድ አስተዳዳሪዎች/መሪዎች ትግሬዎች ናቸው፣ ነገር ግን ትግራይ ውስጥ አነድ ቤትክርስቲያን   ውስጥ የሚቀድስ ቄስና ዲያቆን ወይም እንድ የሌላ ብሔር ኢማም ያለበት መስጊድ የለም፡፡
8. በትግራይ ት/ቤቶች ውስጥ ሁሉም መምህራን ትግሬዎች ሲሆኑ አማርኛ ለማስተማር እንኳን አንድ አማርኝ ተናጋሪ መምህር የለም፡፡ በአማራና 
በሌሎችም ክልሎች ግን ብዙ ትግራዊ አስተማሪዎች አሉ፡፡ በጣም የሚያስቀው ደግሞ በአማራ ክልል አማርኛ ለማስተማር ትግሬ መመደቡ ነው፡፡

9. በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ትግርና ተናጋሪ በየመስሪያ ቤቶች ተቀጥሮ የሠራል፣ ነገር ግን በትግራ ክልል አንድ የሌላ ብሔረሰብ አባል በየትኛውም 
መ/ቤት መሥራት አይችልም፡፡ ለሥራ ጉዳይ በደርሶ መልስ የሚመላለሱትን የመብራት፣ የቴሌ፣ ወዘተ. ሠራተኞች እንዳትጠቅስልኘ አደራ፡፡

10. በገነት ዘውዴ የተነደፈው የትምህርት ፖሊሲ በርካታ ኢትዮጴያውያንን ቦዘኔ አድርጎ ያስቀረ መሆኑ የሚታይ ሲሆን በትግራይ ግን በወቅቱ እስከ 12ኛ     ክፍል ድረስ የሚል የተለየ ፖሊሲ ስለነበር ወድቀው የቀሩ ወጣቶች አይታዩም፡፡

11. አዲስ አበባ ውስጥ በየመንደሩ ሥራ ፈት ሆነው ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ከሚውሉት ወጣቶች መካከል አንድም ትግሬ ወጣት አይገኝም፡፡
12. በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማና በሌሎች መ/ቤቶች ውስጥ ከሚሰሩት መካከል በርካታዎቹ ትግሬዎች ናቸው፡፡
13. ትግርኛ ተናጋሪ የሆነ ሰው በአሸባሪነት ተፈርጆ አይታሰርም
14. ትግርኛ ተናጋሪ የሆነ ሰው ከሥራ አይቀነስም
15. ትግርኛ ተናጋሪ ከመንገድ ታፍኖ አይወሰድም
16. ትግርኛ ተናጋሪ ታፍኖ ተወስዶ ተገሎ ሲጣል እስካሁን አላየንም
17. ትግርኛ ተናጋሪ የወያኔ ተቃዋሚ ሆኖ እስር ሲፈርድበት አላየንም፣ ከስየ አብርሃ በስተቀር፡፡
18. በ97 ምርጫ ሳቢያ በግፍ ከተገደሉትና ከቆሰሉት ኢትዮጵያውን ውስጥ አንድም ትግሬ የለም፡፡
19. እንደወጡ መቅረት፣ ከሥራ መባረር፣ተገሎ ጅምላ መቃብር ውስጥ መጣል የሌሎች ኢትዮጵያውን ዕጣ ፋንታ እንጂ ትግሬውን ሲመለከተው አላየነም.
እንግዲህ እነዚህንና እነዚህን በሚመስሉ ሌሎች ያለተጠቀሱ ምክንያቶች የተነሳ የትግራይ ሕዝብና ሕውሓት የተለያዩ አለመሆናቸውንና ,የትግራይ ሕዝብ ሌላውኢትዮጵያዊ ወገኑ ላይ በደል ሲፈጸም እያየ ዝም የሚለው ያው ወያኔ ነኝ ብሎ ነው ማለት ነው፡፡
Babille Tolla

No comments:

Post a Comment