Friday, January 10, 2014

የጥንካሬ ዋጋ››ርዕዮት አለሙ

ጥንካሬ ለሁሉም ድርጊት ታላቅ ዋጋ አለው፡፡ ጥንካሬ ከሌለ ማንኛውንም አይነት ዋጋ ያለው ተግባር ማከናወንም ሆነ ማቀድ አይቻልም” ያለችው ታላቋ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጸሃፊ ማያ አንጀሉ ናት፡፡
***‹የጥንካሬ ዋጋ››ርዕዮት አለሙ***

“ጥንካሬ ለሁሉም ድርጊት ታላቅ ዋጋ አለው፡፡ ጥንካሬ ከሌለ ማንኛውንም አይነት ዋጋ ያለው ተግባር ማከናወንም ሆነ ማቀድ አይቻልም” ያለችው ታላቋ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጸሃፊ ማያ አንጀሉ ናት፡፡
ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ ብዙ ነገሮች የሉም፡፡ ለ32 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Jourዙnalism Award winner እና የዓለም አቀፉ ሜዲያ ፋውንዴሽን (IWMF) የ2012ን ታላቁን “የጋዜጠኝነት ጀግንነት” ሽልማቱን ለአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ ሸልሟል፡፡ አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡ አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን ለአለም አስተላልፋለች፡፡
ርዕዮትና ሰርክዓለምን ለዚህ ክብር ያበቃቸው “ጥንካሬያቸው” ምነድን ነው? ጥንካሬ በተለያየ መልኩ ይከሰታል፡፡ እራሱን ለመስዋእትነት ለማሳለፍ ቆርጦ በጦር ግንባር የተሰለፈ ተዋጊ አደጋው ከፊትለፊቱ እንዳለ ቢያውቅም በጥንካሬው ይጋፈጠዋል፡፡ ወጣት የሆነች ሴት ‹‹ጭቆናና ድምጻቸው የታፈነባቸው ምትክ ለመሆንና ጩኸታቸውን ለመጮህ፤ እሮሯቸውን ለማሰማት፤ ለሕዝብ በመወገን፤ አቆማለሁ›› ለማለት መቁረጥ የሚጠይቀውን ዋጋም ለመክፈል ቆርጦ መነሳት ጥንካሬን ያሳያል፡፡ “ጥንካሬ” በራሱ ግን ምንድን ነው? ታላቁ ፈላስፋ እንደሚለው ‹‹ጥንካሬ በውስጥ በህሊናችን በመንፈሳችን የሚገኝ ግፊት ነው፡፡ በመረረው አደጋ ውስጥ እንድንጋፈጠውና ገትረን እንድንቋቋመው ያስችለናል፡፡›› ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ ጥንካሬ በፍርሃትና በጅልነት መሃል የሚገኝ ነው፡፡ ምናልባትም ጥንካሬ ሌሎችንም ዋጋዎችን ቆራጥነትን፤የዓላማ ጽናትን፤ፈቃደኝነትን፤ትእግስትን፤አሳቢነትን አመኔታን ያካተተ፤ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥንካሬን ዓላማቸው ያደረጉ ርዕዮትና ሌሎችም መስሎቿ በግል ለሚደርስባቸው ችግር፤መከራ ስቃይ ወይም እስርና እንግልት ጨርሶ አያስቡም አያስፈራቸውም፡፡ ስለዚህም እንደ ርዕዮትና ሰርክ ዓለም ያሉ ጠንካሮች እህቶችና እስክንድር ነጋንና ውብሸት ታዬን የመሰሉ ቆራጦች ስላሉን በእጅጉ ልንኮራ ይገባናል፡፡ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ከፍተኛውን የጥናካሬ ደረጃ ያመላከቱንን ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በእስር በመማቀቅ ላይ ቢሆኑም መከራና ችግሩ፤ ግፉና ጭካኔው ግን ጨርሶ ከዓላማቸው ዝንፍ ጥንካሬያቸውንም ሸብረክ አላደረገውም፡፡
በኦክቶበር 24/2012 በሽልማቱ ስነ ስርአት ላይ የተነበበው የርዕዮት የእጅ ጽሁፍ መልእክት ለመጪው ትውልድ የጥንካሬ ማረጋገጫ ነው፡፡የታሪክ ነጻነት፤የፕሬስ ነጻነት፤በኢትዮጵያ በሚጻፍበት ጊዜ መጪው ትውልድ ይህን የርዕዮትንና ሌሎችንም እውነታዊ መልዕክቶች ያነባል፡፡ ጊዜያዊ ግፈኛ ገዢዎች ሕዝቡን ለስቃይና ሚዛን ላጣው ግፍ በዳረገበት መራር ወቅት ርዕዮትና መሰሎቿ ሃሰትን በማጋለጥና ለግፍ እምቢታን በመምረጣቸው ለእስራት ቢበቁም ቀኑ ሲመጣ ግን በድርጊታቸው የሚኮሩ ይሆናሉ፡፡ ከዓላማዋ ሳታፈገፍግ፤ በዓለም ካሉት ወህኒዎች ሁሉ ያዘቀጠና ግፍ የበዛበት ቦታ ሆና( ወህኒው በኢትዮጵያ የገዢው መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ የቀጠረው ኤክስፐርት እንደገለጸው) ለዓላማዋ በመቆም፤ በተራ መጻፊያና በብጭቅጫቂ ወረቀት ላይ በማቃሰት ላይ ያለውን አምባገነን መንግሥት ከወህኒ ቤት ሆና እየሞገተችውናእየሞጨረች እየተዋጋች ነው፡፡

በኢትዮጵያችን የተሻለ ሁኔታ እንዲመጣ ለማገዝ የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ፡፡ በርካታ ፍትሕ አልባነት፤ጭቆናዎች፤በኢትዮጵያ ውስጥ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በመፈጸም ላይ ናቸውና በጽሁፌ እንዚህን ሁኔታዎች እያነሳሁና እያጋለጥኩ መኮነን ይኖርብኛል፡፡ ንጹሃን ነጻነትንና ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ባዶ እጃቸውን አለ የሚባለውን ሕገ መንግስት ላይ የሰፈረውን በማመን ሰልፍ በመውጣታቸው መረሸናቸው፤የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮች ማሸነፋቸው ወንጀል ሆኖባቸው፤ የነጻው ፕሬስ አባላት አመለካከታቸውና አቋማቸው ከጨቋኙ አገዛዝ የተለየ በመሆኑ፤ ስለመብት መነፈግ በመሟገታቸው፤ ብክንትን፤በተመለከተ ሁኔታዎች መለወጥ እንዳለባቸው በመናገራቸው ለወህኒ መዳረጋቸውን ቀድሞም የጻፍኩበት ነው፡፡ ያንን ሳደርግም ይህን ለማድረግ በረዳኝ ጥንካሬዬ የተነሳ ዋጋ እንደምከፍልበት ተረድቼ ነው፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኝነት እኔ እራሴን የምሰዋለት ሙያ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በሌላ አንጸር ደግሞ የኢህአዴግ ጋዜጠኞች የፕሮፓጋንዳና ቆርጦ ቀጥል አገልጋይ፤ የታዘዙትን እንጂ የታዘቡትን የማይጽፉ ጋዜጠኛ ናችሁ የተባሉ ግን ያልሆኑ የገዢው መደብ አገልጋዮች እንደሆኑም እረዳለሁ፡፡ለኔ ግን ጋዜጠኞች ድምጽ ላጡ ድምጽ ሆነው የሚሰዉ ቆራጥና ጥንካሬያቸው የማይገበር መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡
ስለዚህም ነው በጭቆና መከራ ውስጥ ስላሉት እውነታውን በተመለከተ በርካታ ጽሁፎች ያቀረብኩት፡፡በዚህ ሳቢያ በርካታ ችግሮች ቢያጋጥሙኝም፤ እኔ ግን ለእምነቴ፤ ዓላማዬና ሙያዬ በጥንካሬ እቆማለሁ፡፡በመጨረሻም ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ስለ እውነቷ ኢትዮጵያ እንዲራደ አበክሬ እጠይቃለሁ፡፡እውነተኛዋ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደምታይዋት አለያም የገዢው መደብ ባለስልጣናት ፈጥረውና የሌለውን እንዳለ፤ ያልተሞከረውን እንደተከናወነ፤ ያልታሰበውን እንደተፈጸመ አድርገው እንደሚያወሩላችሁም አይደለም፡፡በእውነተኛዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ጭቆና እየተካሄደ ነው፡፡በነጻ በማሰባቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያውያን እኔ የምተርክላችሁ እውነት መሆኑን ያረጋግጡላችኋል፡፡እባካችሁ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ይህን ሁኔታ ለመለወጥ ሞክሩ፡፡

ማንም የጥንካሬን እውነተኛ ትርጓሜ ማወቅ ቢያሻው፤በፍልስፍና ጽሁፎችና አተረጓጎም ውስጥ አለያም በወታደራዊ ታሪኮች ውስጥ ለማግኘት አይሞክር፡፡ ከዚህ የርዕዮት ጽሁፍ በመማር ወደ ተግባር ይቀይሩት፡፡
እኔ ርዕዮትን አላውቃትም:: የሞራል ብቃቷንና ጥንካሬዋን ግን በአድናቆት አከብራለሁ፡፡ርዕዮትና መሰሎቿ የሚኖሩት በሃሳባቸው ጸንተው፤በእምነታቸው ተማምነው እነዚህ እሴቶቻቸው በሚፈጥሩላቸው ሁኔታ ነው፡፡ በዓላማቸው ጸንተው በሞራል ግዴታቸው ተማምነው ያላቸውንና መደረግ አለበት ብለው ለሚያምኑበት ሁሉ ችሮታቸውን ሳያጓድሉ ለዚያ ለቆሙለት እውነታ በማድረግ ነው፡፡ ምንግዜም በውስጠ ህሊናቸው ውስጥ የሞራል ግዴታቸውን የሚያነቃቃና የሚያስተገብራቸው ሃይል አላቸው፡፡ የተሸለ ዓለም፤ ሚዛናዊ የሆነ፤ሰዎች ሁሉ ያላንዳች ችግርና በደል ሊኖሩበት የሚችሉ ለማድረግ፤ ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ፍላጎትና የተግባር ጽናት በውስጣቸው አለ፡፡ ዘወትር ጭንቀታቸውና ፍላጎታቸው የሰው ልጅ ደስታና የተደላደለ ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ፍትሕ ሲዛባ፤ሥልጣን አለአግባብ መጠቀሚያ ሲሆን፤አድልዎ ሲፈጸም ህሊናቸው በጣሙን ይጎዳና እረፍት ይነሳቸዋል:: ስለዚህም ያንን ተቋቁሞ እንዲስተካከል መታገልን ተቀዳሚ ግዴታቸው ያደርጋሉ፡፡ እንደ ርዕዮት ያሉ ዜጎች ለግል ፍላ ጎታቸውና ድሎታቸው ጨርሶ አይጨነቁም፡፡ እኔ የሚባል እራስን የማስቀደም በሽታ ሊይዛቸው ቀርቶ ባጠገባቸውም ደርሶ አያውቅም፡፡ እነሱ ለራሳቸው ሳይሆን ለሰብአዊ ፍጡራን መብትና ጥቅም ብቻ የቆሙ ናቸውና፡፡ ሌሎች ሰዎች ክንዋኔያቸውን እንዲያመሰግኑላቸው አለያም እንዲፈቅዱላቸው አይጠብቁም፡፡ የስብስብ አርቲ ቡርቲና የስብስብ ዋጋ ቢስ አስተሳሰብ ያማቸዋል፡፡ ለራሳቸው የጥንካሬ ብርታት ሊከፈል የሚገባው ዋጋ እንዳለና ያም የሚያስከትለውን እኩይ ሁኔታ ቢያውቁትም ያንን ሁሉ ለመክፈል ፈቃደኛ ናቸው፡፡ የጥንካሬ ዋጋገው በመንፈሳቸው ጉዳት የሚከፈል መሆኑን ቢረዱም ያንንም ተቀብለውታል፡፡ እንዲህ ነው የአልበገሬዎች ሕይወትና ታሪካቸው!
እግዚአብሄር ይጠብቅሽ ርዕዮት!!!
ከሰብኣዊስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ ብዙ ነገሮች የሉም፡፡ ለ32 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Jourዙnalism Award winner እና የዓለም አቀፉ ሜዲያ ፋውንዴሽን (IWMF) የ2012ን ታላቁን “የጋዜጠኝነት ጀግንነት” ሽልማቱን ለአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ ሸልሟል፡፡ አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡ አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን ለአለም አስተላልፋለች፡፡
ርዕዮትና ሰርክዓለምን ለዚህ ክብር ያበቃቸው “ጥንካሬያቸው” ምነድን ነው? ጥንካሬ በተለያየ መልኩ ይከሰታል፡፡ እራሱን ለመስዋእትነት ለማሳለፍ ቆርጦ በጦር ግንባር የተሰለፈ ተዋጊ አደጋው ከፊትለፊቱ እንዳለ ቢያውቅም በጥንካሬው ይጋፈጠዋል፡፡ ወጣት የሆነች ሴት ‹‹ጭቆናና ድምጻቸው የታፈነባቸው ምትክ ለመሆንና ጩኸታቸውን ለመጮህ፤ እሮሯቸውን ለማሰማት፤ ለሕዝብ በመወገን፤ አቆማለሁ›› ለማለት መቁረጥ የሚጠይቀውን ዋጋም ለመክፈል ቆርጦ መነሳት ጥንካሬን ያሳያል፡፡ “ጥንካሬ” በራሱ ግን ምንድን ነው? ታላቁ ፈላስፋ እንደሚለው ‹‹ጥንካሬ በውስጥ በህሊናችን በመንፈሳችን የሚገኝ ግፊት ነው፡፡ በመረረው አደጋ ውስጥ እንድንጋፈጠውና ገትረን እንድንቋቋመው ያስችለናል፡፡›› ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ ጥንካሬ በፍርሃትና በጅልነት መሃል የሚገኝ ነው፡፡ ምናልባትም ጥንካሬ ሌሎችንም ዋጋዎችን ቆራጥነትን፤የዓላማ ጽናትን፤ፈቃደኝነትን፤ትእግስትን፤አሳቢነትን አመኔታን ያካተተ፤ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥንካሬን ዓላማቸው ያደረጉ ርዕዮትና ሌሎችም መስሎቿ በግል ለሚደርስባቸው ችግር፤መከራ ስቃይ ወይም እስርና እንግልት ጨርሶ አያስቡም አያስፈራቸውም፡፡ ስለዚህም እንደ ርዕዮትና ሰርክ ዓለም ያሉ ጠንካሮች እህቶችና እስክንድር ነጋንና ውብሸት ታዬን የመሰሉ ቆራጦች ስላሉን በእጅጉ ልንኮራ ይገባናል፡፡ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ከፍተኛውን የጥናካሬ ደረጃ ያመላከቱንን ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በእስር በመማቀቅ ላይ ቢሆኑም መከራና ችግሩ፤ ግፉና ጭካኔው ግን ጨርሶ ከዓላማቸው ዝንፍ ጥንካሬያቸውንም ሸብረክ አላደረገውም፡፡
በኦክቶበር 24/2012 በሽልማቱ ስነ ስርአት ላይ የተነበበው የርዕዮት የእጅ ጽሁፍ መልእክት ለመጪው ትውልድ የጥንካሬ ማረጋገጫ ነው፡፡የታሪክ ነጻነት፤የፕሬስ ነጻነት፤በኢትዮጵያ በሚጻፍበት ጊዜ መጪው ትውልድ ይህን የርዕዮትንና ሌሎችንም እውነታዊ መልዕክቶች ያነባል፡፡ ጊዜያዊ ግፈኛ ገዢዎች ሕዝቡን ለስቃይና ሚዛን ላጣው ግፍ በዳረገበት መራር ወቅት ርዕዮትና መሰሎቿ ሃሰትን በማጋለጥና ለግፍ እምቢታን በመምረጣቸው ለእስራት ቢበቁም ቀኑ ሲመጣ ግን በድርጊታቸው የሚኮሩ ይሆናሉ፡፡ ከዓላማዋ ሳታፈገፍግ፤ በዓለም ካሉት ወህኒዎች ሁሉ ያዘቀጠና ግፍ የበዛበት ቦታ ሆና( ወህኒው በኢትዮጵያ የገዢው መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ የቀጠረው ኤክስፐርት እንደገለጸው) ለዓላማዋ በመቆም፤ በተራ መጻፊያና በብጭቅጫቂ ወረቀት ላይ በማቃሰት ላይ ያለውን አምባገነን መንግሥት ከወህኒ ቤት ሆና እየሞገተችውናእየሞጨረች እየተዋጋች ነው፡፡

በኢትዮጵያችን የተሻለ ሁኔታ እንዲመጣ ለማገዝ የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ፡፡ በርካታ ፍትሕ አልባነት፤ጭቆናዎች፤በኢትዮጵያ ውስጥ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በመፈጸም ላይ ናቸውና በጽሁፌ እንዚህን ሁኔታዎች እያነሳሁና እያጋለጥኩ መኮነን ይኖርብኛል፡፡ ንጹሃን ነጻነትንና ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ባዶ እጃቸውን አለ የሚባለውን ሕገ መንግስት ላይ የሰፈረውን በማመን ሰልፍ በመውጣታቸው መረሸናቸው፤የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮች ማሸነፋቸው ወንጀል ሆኖባቸው፤ የነጻው ፕሬስ አባላት አመለካከታቸውና አቋማቸው ከጨቋኙ አገዛዝ የተለየ በመሆኑ፤ ስለመብት መነፈግ በመሟገታቸው፤ ብክንትን፤በተመለከተ ሁኔታዎች መለወጥ እንዳለባቸው በመናገራቸው ለወህኒ መዳረጋቸውን ቀድሞም የጻፍኩበት ነው፡፡ ያንን ሳደርግም ይህን ለማድረግ በረዳኝ ጥንካሬዬ የተነሳ ዋጋ እንደምከፍልበት ተረድቼ ነው፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኝነት እኔ እራሴን የምሰዋለት ሙያ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በሌላ አንጸር ደግሞ የኢህአዴግ ጋዜጠኞች የፕሮፓጋንዳና ቆርጦ ቀጥል አገልጋይ፤ የታዘዙትን እንጂ የታዘቡትን የማይጽፉ ጋዜጠኛ ናችሁ የተባሉ ግን ያልሆኑ የገዢው መደብ አገልጋዮች እንደሆኑም እረዳለሁ፡፡ለኔ ግን ጋዜጠኞች ድምጽ ላጡ ድምጽ ሆነው የሚሰዉ ቆራጥና ጥንካሬያቸው የማይገበር መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡
ስለዚህም ነው በጭቆና መከራ ውስጥ ስላሉት እውነታውን በተመለከተ በርካታ ጽሁፎች ያቀረብኩት፡፡በዚህ ሳቢያ በርካታ ችግሮች ቢያጋጥሙኝም፤ እኔ ግን ለእምነቴ፤ ዓላማዬና ሙያዬ በጥንካሬ እቆማለሁ፡፡በመጨረሻም ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ስለ እውነቷ ኢትዮጵያ እንዲራደ አበክሬ እጠይቃለሁ፡፡እውነተኛዋ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደምታይዋት አለያም የገዢው መደብ ባለስልጣናት ፈጥረውና የሌለውን እንዳለ፤ ያልተሞከረውን እንደተከናወነ፤ ያልታሰበውን እንደተፈጸመ አድርገው እንደሚያወሩላችሁም አይደለም፡፡በእውነተኛዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ጭቆና እየተካሄደ ነው፡፡በነጻ በማሰባቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያውያን እኔ የምተርክላችሁ እውነት መሆኑን ያረጋግጡላችኋል፡፡እባካችሁ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ይህን ሁኔታ ለመለወጥ ሞክሩ፡፡

ማንም የጥንካሬን እውነተኛ ትርጓሜ ማወቅ ቢያሻው፤በፍልስፍና ጽሁፎችና አተረጓጎም ውስጥ አለያም በወታደራዊ ታሪኮች ውስጥ ለማግኘት አይሞክር፡፡ ከዚህ የርዕዮት ጽሁፍ በመማር ወደ ተግባር ይቀይሩት፡፡
እኔ ርዕዮትን አላውቃትም:: የሞራል ብቃቷንና ጥንካሬዋን ግን በአድናቆት አከብራለሁ፡፡ርዕዮትና መሰሎቿ የሚኖሩት በሃሳባቸው ጸንተው፤በእምነታቸው ተማምነው እነዚህ እሴቶቻቸው በሚፈጥሩላቸው ሁኔታ ነው፡፡ በዓላማቸው ጸንተው በሞራል ግዴታቸው ተማምነው ያላቸውንና መደረግ አለበት ብለው ለሚያምኑበት ሁሉ ችሮታቸውን ሳያጓድሉ ለዚያ ለቆሙለት እውነታ በማድረግ ነው፡፡ ምንግዜም በውስጠ ህሊናቸው ውስጥ የሞራል ግዴታቸውን የሚያነቃቃና የሚያስተገብራቸው ሃይል አላቸው፡፡ የተሸለ ዓለም፤ ሚዛናዊ የሆነ፤ሰዎች ሁሉ ያላንዳች ችግርና በደል ሊኖሩበት የሚችሉ ለማድረግ፤ ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ፍላጎትና የተግባር ጽናት በውስጣቸው አለ፡፡ ዘወትር ጭንቀታቸውና ፍላጎታቸው የሰው ልጅ ደስታና የተደላደለ ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ፍትሕ ሲዛባ፤ሥልጣን አለአግባብ መጠቀሚያ ሲሆን፤አድልዎ ሲፈጸም ህሊናቸው በጣሙን ይጎዳና እረፍት ይነሳቸዋል:: ስለዚህም ያንን ተቋቁሞ እንዲስተካከል መታገልን ተቀዳሚ ግዴታቸው ያደርጋሉ፡፡ እንደ ርዕዮት ያሉ ዜጎች ለግል ፍላ ጎታቸውና ድሎታቸው ጨርሶ አይጨነቁም፡፡ እኔ የሚባል እራስን የማስቀደም በሽታ ሊይዛቸው ቀርቶ ባጠገባቸውም ደርሶ አያውቅም፡፡ እነሱ ለራሳቸው ሳይሆን ለሰብአዊ ፍጡራን መብትና ጥቅም ብቻ የቆሙ ናቸውና፡፡ ሌሎች ሰዎች ክንዋኔያቸውን እንዲያመሰግኑላቸው አለያም እንዲፈቅዱላቸው አይጠብቁም፡፡ የስብስብ አርቲ ቡርቲና የስብስብ ዋጋ ቢስ አስተሳሰብ ያማቸዋል፡፡ ለራሳቸው የጥንካሬ ብርታት ሊከፈል የሚገባው ዋጋ እንዳለና ያም የሚያስከትለውን እኩይ ሁኔታ ቢያውቁትም ያንን ሁሉ ለመክፈል ፈቃደኛ ናቸው፡፡ የጥንካሬ ዋጋገው በመንፈሳቸው ጉዳት የሚከፈል መሆኑን ቢረዱም ያንንም ተቀብለውታል፡፡ እንዲህ ነው የአልበገሬዎች ሕይወትና ታሪካቸው!
እግዚአብሄር ይጠብቅሽ ርዕዮት!!!

No comments:

Post a Comment