Tuesday, January 14, 2014

በአፅቢ ከተማ 17 ወጣቶች በጩቤ ተወግተው ቆሰሉ


Abraha Destaበአፅቢ ከተማ የህወሓት ባለስልጣናት አዘውትረው የሚጠጡበት ቤት አለ። በመጠጥ ቤቱ አንድ ወጣት ከወረዳው የፖሊስ አዛዥ ጋር ይጣላል። የፖሊስ አዛዡና የወረዳው የፀጥታ ሐላፊ ተባብረው፣ በሽጉጥ አስፈራርተው (ሽጉጥ ተኩሰው ነበር) ወጣቱ ደብድበው ጥርሱ አውልቀው ይሄዳሉ።
ጥርሱ ያጣ ወጣት ለመክሰስ ሲሞክር የወረዳው የፍትሕ አካላት “ባለስልጣናትን ከሰህ አያዋጣህምና ከነሱ ታርቀህ አርፈህ ተቀመጥ” ይሉታል። ወጣቱ ከደብዳቢዎቹ ጋር በመደራደር ለወለቀው ጥርሱ ሦስት ሺ ብር ብቻ ካሳ ተከፍሎ ቤቱ ይመለሳል።
በገና በዓል በዛው የህወሓት ባለስልጣናት በሚጠጡበት ቤት ሌላ አዲስ ግጭት ይቀሰቀሳል። ግጭቱ የህወሓት ካድሬዎችና ከስዑዲ የተመለሱ ወጣቶች ተሳትፈውበታል። አብዛኞቹ ባለስልጣናት ሮጠው ያመለጡ ሲሆን ከስዑዲ ከተመለሱ ወጣቶች መካከል ግን አስራ ሰባቱ (17) በጩቤ (ካራ) ተወግተው ቆስለዋል። የተወሰኑ በጠና ቆስለው በመቀለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ይገኛሉ። አሁን የፖሊስ አዛዡ ወደ ሌላ ወረዳ መቀየሩ ተሰምቷል።
ይህ በንዲህ እንዳለ በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ተቃውም የሚነሳበት አከባቢ እየተመረጠ ምልሻዎች ጠመንጃቸው እየተነጠቁ ነው። ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የህወሓት ባለስልጣናት በየአከባቢው ጥያቄ የሚጠይቅ ዜጋ እያስፈራሩና ጠመንጃው እየነጠቁ ነው።
በወረዳው “ጎልጎል ናዕለ” በተባለ ጣብያ ሙስና ያጋለጡ አርሶአደሮች ማስፈራርያ እየደረሰባቸው ነው። ለምሳሌ አቶ አበራ አስገዶም የተባለ የጣብያው ኗሪ የአከባቢው አስተዳዳሪዎች የሙስና ተግባር በስብሰባ በማጋለጡ ምክንያት ህዝቡ እንዲያገለው ተጠይቋል። በአስተዳዳሪዎች ዉሳኔ ከአቶ አበራ ጋር አብሮ የተንቀሳቀሰ ሰው “ጠላት” ተብሎ ይፈረጃል። የመንግስት አገልግሎትም አያገኝም።
ህወሓቶች በትግራይ ክልል ዓመፅ እንዳይቀሰቀስ ስጋት ስላደረባቸው በማያምኑት አከባቢ የሚገኙ ሰዎች ጠመንጃቸው እንዲያራግፉ እያስገደዱ ነው። ተቃውሞ ከተነሳ ወድያው በ አከባቢው የሚገኙ ባለ ጠመንጃ ምልሻዎች ወይም የድሮ ታጋዮች ጠመንጃው እንዲያስረክቡ ይታዘዛል።
It is so!!!
Abraha Desta

No comments:

Post a Comment