Saturday, December 7, 2013

ኢትዮጵያና ኤርትራ በሱዳን በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር እያካሄዱ እንዳሉ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሽር ሀሙስ ዕለት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን መግለጻቸው ተሰማ፡፡

| ኢትዮጵያና ኤርትራ በሱዳን በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር እያካሄዱ እንዳሉ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሽር ሀሙስ ዕለት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን መግለጻቸው ተሰማ፡፡

“በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አንዳንድ ጥረቶች እያደረግን ነው” ያሉት አልበሽር፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበሩ ጉዳይ፣ በእጅ አዙር በሚያደርጉት ግጭት (Proxy war) ዙሪያና በሌሎችም ተዛማች ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ ለማስቻል ህቡዕ የሆን የሶስተኛ ወገን ድርድር በሱዳን በኩል እንደጀመሩ ገልጸዋል፡፡

“ሱዳን ከሁለቱም ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን ከዚህ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር በተጨማሪ በቅርቡ የሁለቱንም ሀገራት መሪዎች ካርቱም ላይ ጠርተን እንዲወያዩ እናደርጋለን” ሲሉ አልበሽር መናገራቸውም ታውቋል፡፡
Sudan mediating indirect talks between Ethiopia and Eritrea 

No comments:

Post a Comment