Sunday, December 29, 2013

ሰበር ዜና፣ በዓረና-ትግራይ ስብሰባ መታወቅያ የሌለው እንዳይገባ ተከለከለ


Tigray, Ethiopia map

December 29, 2013
by Abraha Desta
እሁድ፣ ታህሳስ 20 – 2006፣ 10፡AM
በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ እንገኛለን። የህዝብ ስብሰባው ለመጀመር አዳርሹ ሲከፈት ህዝብ በስብሰባው ለመሳተፍ መግባት ሲጀምር አስተዳዳሪዎቹ ደንግጠው ‘በስብሰባው መሳተፍ የሚችል ሰው የቀበሌ መታወቅያ ያለው’ ብቻ መሆን እንዳለበት አወጁ። መታወቅያው እየመዘገቡ ለማስገባት ወሰኑ። ህዝቡ ተቃወመ። የዓረና አመራር አባላትም ድርጊቱ ተቃወሙ። መታወቅያ የሌለው እንዳይገባ ስለተወሰነ ብዙ ሰው ተቃውሞ ስላነሳና መግባት ስለፈለገ የአዳራሹ መግብያ በር ተዘጋ። አሁን የተፈቀደልን አዳራሽ ዝግ ነው። ዓረና ስብሰባው በአዳራሹ በር ባለው ሜዳ ለማካሄድ ወስኗል። ባደራሹ በር አከባቢ ብዙ ህዝብ አለ። ካድሬዎቹ ህዝቡ ለመበተን እየፈተኑ ነው።
source ecadforum.com

No comments:

Post a Comment