Sunday, December 22, 2013

የኢትዮጵያ ሬዲዮና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1995 ተቀላቅለው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን መስርተዋል

የኢትዮጵያ ሬዲዮ መደበኛ ስርጭቱን በ1935 ጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደግሞ በ1964 የተመረቀ ቢሆንም በይፋ ከመመረቁ አስቀድሞ በ1963 አዲስ አበባ ላይ የተካሄደውን ታሪካዊውንና የመጀረመሪያውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ አስተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ ሬዲዮና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1995 ተቀላቅለው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን መስርተዋል፡፡ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም ቢሆንም ወያኔ አንባገነን በመሆኑ የራሱን ፕሮባጋንዳ ማሰራጫ አድርጎታል። 
አምባገነኖች የሚገዙትን ህዝብ ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ቀዳሚው የመረጃ ፍሰትን መቆጣጠር ነው። እነሱ ከሚሉት ውጭ እንዳይሰማ ለማድረግ ወደ ህዝብ ጆሮ የሚደርሱትን ነገሮች ሁሉ የመቆጣጠር ተግባር ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ውሸትን ደጋግሞ በማውራት እውነት
ለማስመሰል ይተጋሉ። ይህ የአምባገነን ሥርዓቶች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። 

ወያኔም በጉልበት ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ከገባበት እለት ጀምሮ እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው። ወያኔ የመረጃ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቀንና ሌሊት ውሸቶችን እውነት ለማስመሰል ይጥራል። ኢትዮጵያ ውስጥ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ስለሌለ አንዳንድ ወገኖቻችን ወያኔ ደጋግሞ የሚናገረዉ ዉሸት እዉነት ቢመስላቸዉ ልንፈርድባቸዉ አይገባም።

• ኢትዮጵያዊያን በዘረኝነት እጅግ በተማረሩበት፤ አገሪቷ በአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቃለች በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ከላይ የተጠቀሱት ሚዲያዎች የሚያወሩት በወሬ ብቻ ስለፈጠሯት በአካል ግን ስለሌለችው ኢትዮጵያ ነው።

• አጠገባቸው ሰቆቃ ሲፈፀም፤ ህፃናት ሲገደሉ፤ እናቶች ሲደፈሩ፤ ተማሪዎች ሲደበደቡ እያዩ “የኢትዮጵያ” ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚያወሩት በወያኔ አገዛዝ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩ ስለመሆናቸው ነው።

• ከአንድ ጎጥ የወጡ ሰዎች ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ሃገሪቷን እየቦጠቦጧት ባሉበት ባሁኑ ወቅት፤ በዘራቸው ከጎጡ አባላት ውጭ የሆኑት አጃቢዎች የምስለኔን ያክል እንኳን ሥልጣን የሌላቸዉ መሆኑ እየታወቀ፤ ዘርና ሃይማኖት መሠረት ያደረጉ ግጭቶች አገሪቷን እያመሷት
እና እነዚህን ሁሉ በገዛ ዓይኖቻቸው እያዩ “የኢትዮጵያ” ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚያወሩት ፍቅር ሞልቶ ስለመትረፉ እና የብሄር ብሄረሰቦች መብት ስለመከበሩ ነው።

• እነዚህ ሚዲያዎች ወታደሩ፣ ፓሊሱ፣ ደህንነቱ እና ራሳቸው የሚዲያ ተቋማቱ ሁሉም በዘረኝነት የተተበተቡ፤ ከሙያዊ ኃላፊነት ይልቅ ለጆሮ ጠቢነት ይበልጥ
 ትኩረት የሚሰጡ መሆናቸው እየታወቀ ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ የማይሉ፤ በግልባጩ “ውጤት-ተኮር”፣ ቢ.ፒ.አር. እያሉ የሚያደናግሩ አደንቋሪዎች ናቸው።

• ፍርድ ቤቶች በፍትህ እያላገጡ ዋሾ ሚዲያዎች ትዕዛዝ የተሰጠባቸውን ዶሴዎች እየቆጠሩ ስለፍርድ ቤቶች “ምርታማነት” መጨመር ያወራሉ።
• የገበሬው ማሳ ተቀምቶ ለባዕዳን በመሰጠቱ ምክንያት የበርካታ ቤተሰቦች ለቅሶ ሰሚ ባጣበት ወቅት እነኚህ የክህደት ሚዲያዎች ሚሊኒየነር ስለሆኑ ገበሬዎች ድራማ ሰርተው ያሳያሉ።

No comments:

Post a Comment