Saturday, December 28, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ተከፈተ::


Andinet Party
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የአባይ ግድብ በየትኛውም መመዘኛ የአንድ ግለሰብና ፓርቲ ራዕይ መሆን አይችልም፡፡ኢህአዴግ ራሱን የግድቡ ባለቤት በማድረግ ተቃዋሚዎችን በተለይም አንድነትን የግብጽ መንግስት ተላላኪ አድርጎ መሳሉ ነውረኝነት ነው፡፡አንድነት አሁንም ኢትዮጵያ አባይን የመጠቀም ህጋዊና ታሪካዊ መብት ያላት መሆኑን አንድነት ያምናል፡፡አንድነት የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው የሚል አስተሳሰብ እንደሌለው በድጋሚ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
‹‹2007ን ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ›› በሚል መሪ ቃል ከመላ ሃገሪቱ ተወክለው የመጡ ከ450 በላይ የአንድነት አመራሮች/አባሎች በተገኙበት በዛሬው ቅዳሜ እለት ጠቅላላ ጉባዬውን ፓርቲው በደመቀ ሁኔታ እያካሄደ መሆኑን ከአዲስ አበባ ምንጮች ገልጸዋል:
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በቀጣዮ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ መሳተፍ የምርጫውን ሜዳ መስፋትና መጥበብ ተከትሎ የሚወሰን መሆኑን አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ገልጸዋል፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በቀጣዮ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ መሳተፍ የምርጫውን ሜዳ መስፋትና መጥበብ ተከትሎ የሚወሰን መሆኑን አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ገልጸዋል፡፡
ይህ በዛሬው እለት የተከፈተው የጠቅላላ ጉባዬ ስብሰባ ነገም የሚቀጥል ሲሆን እንዲሁም በተጨማሪ ዛሬ ቅዳሜ ለሊቱን የፐርቲው ስራ አስፈጻሚ ስለወደፊቱ የፓርቲው የትግል ስልትና ብቃት ያላቸው አባላትን በመመልመል የፓርቲውን አደረጃጀት አሁን ካለው በእጥፍ በማሳደግ በ2007ዓ.ም በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ህዝብን አስተባብሮ በአሸናፊ ለመውጣት በሚቻልባቸው ስልቶች ዙሪያ የጠለቀ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል::
Andinet Party 4አንድነት ለጠቅላላ ጉባዬው የሚሆን አደራሽ ለማግኘት በየሆቴሉ እና አደራሽ አከራዮች ቢፈልግም ከገዢው ፓርቲ በተደረገ ማስፈራሪያና ተጽእኖ ማንም ሊያከራየው ፈቃደኛ ካለመሆኑም በላይ የህዝብ ንብረት የሆነውም የምርጫ ቦርድ አደራሹን ሰበብ በመፍጠር ከልክሎታል::
ከአፋር ክልል ተወክለው የመጡት የአንድነት አባል ሚከተለውን ብለዋል “ኢህአዴግ ወድቋል እሱን ለማስወገድ ያቃተን በኛ ችግር ነው፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል አንድነት ለአፋር ክልል የበለጠ ትኩረት ይስጥ” ብለዋል፡፡ ከኦሮሚያ ቦረና ዞን የተወክለው የመጡት አባል በበኩላቸው ኢህአዴግን ለመጣል እታች ድረስ የተዘረጋው መዋቅር መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ከቤንሻንጉል ክልል ተወክለው የመጡት አባል በ2005ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በመቅረቱ ህብረተሰቡ ቅሬታ ማቅረቡን ተናግሯል፡፡





አንድነት ፓርቲና ዴሞክራሲያዊ ባህሉ
————————————
በነብዩ ኃይሉ
—————–
መጪዎቹ ሁለት የእረፍት ቀናት ለአንድነት ፓርቲ አባላት በናፍቆት የሚጠበቁ ሆነዋል ፤ ምክንያቱ ደግሞ ለወራት ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜና እሁድ (ታህሳስ 19 እና 20) የሚካሄድ መሆኑ ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲ የቀደመ ተሞክሮ እንደሚያስረዳው ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያው ለወጉ የሚሰበሰብ አይደለም፡፡ ይልቁኑም በግልፅ የሚታይ የአመራር ለውጥ የሚደረግበትና ወሳኝ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችም የሚስተናገዱበት ነው፡፡
አንድነት በ2001 እና በ2004 ባደረጋቸው ጠቅላላ ጉባኤዎች በግልፅ የሚታይ የአመራር ለውጥ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ የፓርቲው አካሄድ በሀገር ደረጃም ቢደረግ የሚያስብሉ ዴሞክራሲያዊ ክዋኔዎችንም ያካተተነው፡፡ በሌሎች ፓርቲዎች ሲደረግ የማይስተዋል ቢሆንም አንድነት በሁለቱም ጉባኤዎች ሊቀመናብርቱን የመረጠው ጠንካራ ፉክክር ካደረጉ በኋላ ነው፡፡
በ2001ዓ.ም በተደረገው የፓርቲው የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እና አቶ ተመስገን ዘውዴ ጠንካራ ፉክክር ካደረጉ በኋላ ጉባኤው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን በሊቀመንበርነት መርጧል፡፡
በ2004ዓ.ም በተደረገው የፓርቲው ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር ንጋት አስፋው እና ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ጠንካራ ፉክክር ካደረጉ በኋላ ጉባኤው የቀድሞውን የሀገሪቱን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን የአንድነት ሊቀመንበር እንዲሆኑ መርጧል፡፡
አንድነት በመጪው ቅዳሜና እሁድ (ታህሳስ 19 እና 20) በሚያደርገው ልዩ ጠቅላላ ጉባኤም በግልፅ የሚታይ የአመራር ለውጥ ለማደረግ ተዘጋጅቷል፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ተክሌ በቀለ እና አቶ ግርማ ሰይፉ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ተያይዘውታል፤ አንድነትም ይህን ዴሞክራሲያዊ ባህሉ አንግቦ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ ይቀጥላል፡፡
Ze-Habesha

No comments:

Post a Comment