Saturday, December 28, 2013

የፖለቲካ አናሊስስ፣ ተብሎ በተለያየ ሚዲያ ላይ ትንተናን በመሰጥ የሚታወቀው የአገሬ ልጅ JUWAR MOHAMED

Get Taff ወጣቱ፣ ምሁር፣ የፖለቲካ አናሊስስ፣ ተብሎ በተለያየ ሚዲያ ላይ ትንተናን በመሰጥ የሚታወቀው የአገሬ ልጅ JUWAR MOHAMED የተጠናወተውን የአፍራሽ አመለካከት የተባይ ተስቦ ከሰሜን ተጋብቶበት ሲሰቃይ ሳየው ልቤ አዘነለት።ምክንያቱም ሁለታችንም ተወልደን ያደግነበት በአንድ አካባቢና መሀበረሰብ ዉስጥ ስለሆነ ባገር ልጅነት ስሜት ነው መሰለኝ እጅግ በጣም አዝኜለታለው። ይህ ወንድሜ በተለያየ ርእስ ዜማዎቹ ቢታወቅም በኢትዮጵያ ህዝ እውቅናን ያተረፉለት ሶስቱ ዜማዎቹ ናቸው። ከነጠላ ዜማዎቹ ውስጥ በርግጥ ጆሮዬን ከማሳከክ በስተቀር ለልቤ መልክትን አልሰጡም። ከዜማዎቹ ርእስ ዉስጥ፣ 1• ኦሮሞ ፎቢያ 2• ኦሮሞ ፈርስትና 3• ለሙስሊም ጥያቄ መልስ ኦሮሞን ደግፉ፣ የተሰኙት ዜማዎቹ የወንድሜን ጤንነት የሚያጠራጥሩ ስለሆነ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር፣ በኦሮሞ ጋዳ ባህል፣ በዋቀ ሜጫፍ ቱለመ ዱኣ እንዲደረግለት በጥብቅ አሳስባለው።በሽታ ሁሉ በሁለት ይመደባል፣የሚተላለፉና የማይተላለፉ ሲሆን ይመስለኛል ወንድሜ የተጠቃው ከሰሜን አካባቢ የተነሳው የዘረኝነት ተስቦ ገብቶበት ነው እንጂ እኔ አውቀዋለው ቅን እና አስተዋይ እንደነበረ። ለማንኛዉም ተመርምሮ የተመረዘው ልቡ እኪታከም ድረስ ዱኣ ማድረጉ አይከፋም። እንደኔ እምነት ከሆነ አንድነትን፣ ፍቅርንና መቻቻልን የማያስተምር ግለሰብም ሆና መሀበረሰብ፣ ሀይማኖትም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ሴይጣናዊ ሀዋርያነትን ሹመት ከዳቢሎስ ተቀብሎ ጥላቻንና አመጽን እየሰበከ በፈጣሪ ሀይል ስኬትን ሳይጎናጸፍ ጃሃነብ ይገባል እንጅ እቅዱ እውን አይሆንም። ለኔ ከምከተለው ሀይማኖት ይልቅ በዉስጤ ያለው አምነት ይበልጣል። እንዲሁም፣ በመወለድ የተጎናጸፍኩት ከጠባቧ ብሄሬ ይልቅ፣ የማንነቴ ህልውና ታሪኬ የሆነችው ሰፊዋ አገሬ ትበልጥብኛለች። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች፣ የጠላቶቿምን ዉድቀት ታያለች

No comments:

Post a Comment