Wednesday, December 25, 2013

በታማሚዎች መነገድ ያተርፋል!? ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ (ከማረሚያ ቤት)


በታማሚዎች መነገድ ያተርፋል!?ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ  (ከማረሚያ ቤት)‹‹ጸሐይ በሞቀው-----›› የፍርድ ሂደት ራሴን ለመከላከል አቅርቤው ከነበረው የተከሳሽ የመከላከያ ቃል በኋላ ዳግም ድምጼን ለማሰማት የተመለስኩበት  አጋጣሚ ለወራት ሲያሰቃየኝ ለቆየው የኩላሊት ሕመሜ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹የጤና ባለሞያዎች ››ምንም ሕክምና ሊሰጡኝ እንደማይችሉ በመግለጽ በተራቸው የሕክምና ፋይሌን መዝጋታቸው ቅር ያሰኘኛል፡፡ጥልቅ ፍቅር እና ክብር ላለኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመልካም ዜና ጋር ብወጣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ግን አልሆነማ!ጉዳዮን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ፣በተደረገልኝ የኩላሊት የአልትራ-ሳውንድ ምርመራ ፣በተለይ በግራ ኩላሊቴ ላይ በአሳሳቢ ሁኔታ ፣እጅግ የተከማቸ አሸዋ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡በግራም በቀኝም ያሉ ወገኖች ይህን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ይችላሉ፡፡(ለጠላትም ለወዳጅም አላልኩም፣ምክንያቱም በግራ እና በቀኝ በተሰለፉት ውድ ኢትዮጵያዊያን መካከል እየከረረ የመጣው የሐሳብ እና የመስመር ልዮነት እንጂ፣ጠብታ የጠላትነት መሰረት እንደሌለው ታሪክ እና እውነት ይመሰክሩታልና፡፡)ለማንኛውም የቃሊቲዎቹ ሐኪሞች ስቃዬ ሊሰማቸው አልቻለም ወይም አልፈለጉም ፡፡ከቶ ለምን ይሆን!?ይህንን ከአስደማሚ የሰቆቃ ድራማ ፣ከጀርባ ሆኖ እየመራ ያለው ባለ ረዥም እጅ ማን ይሆን?ለመሆኑስ አማራጭ በሌላቸው ታማሚዎች ጤንነት መነገድስ ስንት ያተርፋል?ምን ይሉት እርካታንስ ያጎናጽፋል?ከእኛ ስር የበቀለው የነገይቱ ኢትዮጵያችን ተረካቢ ትውልድስ ይህን አስጸያፊ ድርጊት እንዴት ይመለከተዋል ትላላችሁ ?ሁላችንንም ቸር እና ፍጹም የሆነው እግዚአብሄር ይርዳን፡፡በተለይ እኔ ባለሁበት የእስር እና የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገለጽ ሐሳብ ፣ስሜታዊነት ሊንጸባረቅበት ቢችል እንኳ ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ሌሎችን ለመውቀስም የጥላቻ ስሜትንም ለመግለጽ ተደርጎ እንዳይወሰድብኝም በትሕትና እጠይቃለሁ፡፡ክብር እና ፍቅር የሚገባችሁ  ውድ  ኢትዮጵያዊያን በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅር እና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡ደግሞም እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ የታሪክ ፣የእምነት፣የወግና የባህል በአጠቃላይም የማንነት ጽኑ መሰረት አለን፡፡ትናንት የመጣን ነገ የምንሄድ አይደለንም ፣እንኖራለን ቢያንስ ትውልድ ይኖራል፡፡ታዲያ እንዴት ሕክምና በመንፈግ ፣ከቤተሰብ አርቆ በማሰር (የሁለትዮሽ እንግልት ለመፍጠር በማሰብ)ይህንን ማንነት እንጣው?አይሆንም!እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክአክባሪ ወንድማችሁ ውብሸት ታዬጸሐይ በሞቀው—–›› የፍርድ ሂደት ራሴን ለመከላከል አቅርቤው ከነበረው የተከሳሽ የመከላከያ ቃል በኋላ ዳግም ድምጼን ለማሰማት የተመለስኩበት አጋጣሚ ለወራት ሲያሰቃየኝ ለቆየው የኩላሊት ሕመሜ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹የጤና ባለሞያዎች ››ምንም ሕክምና ሊሰጡኝ እንደማይችሉ በመግለጽ በተራቸው የሕክምና ፋይሌን መዝጋታቸው ቅር ያሰኘኛል፡፡
ጥልቅ ፍቅር እና ክብር ላለኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመልካም ዜና ጋር ብወጣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ግን አልሆነማ!
ጉዳዮን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ፣በተደረገልኝ የኩላሊት የአልትራ-ሳውንድ ምርመራ ፣በተለይ በግራ ኩላሊቴ ላይ በአሳሳቢ ሁኔታ ፣እጅግ የተከማቸ አሸዋ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡በግራም በቀኝም ያሉ ወገኖች ይህን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ይችላሉ፡፡(ለጠላትም ለወዳጅም አላልኩም፣ምክንያቱም በግራ እና በቀኝ በተሰለፉት ውድ ኢትዮጵያዊያን መካከል እየከረረ የመጣው የሐሳብ እና የመስመር ልዮነት እንጂ፣ጠብታ የጠላትነት መሰረት እንደሌለው ታሪክ እና እውነት ይመሰክሩታልና፡፡)
ለማንኛውም የቃሊቲዎቹ ሐኪሞች ስቃዬ ሊሰማቸው አልቻለም ወይም አልፈለጉም ፡፡ከቶ ለምን ይሆን!?ይህንን ከአስደማሚ የሰቆቃ ድራማ ፣ከጀርባ ሆኖ እየመራ ያለው ባለ ረዥም እጅ ማን ይሆን?ለመሆኑስ አማራጭ በሌላቸው ታማሚዎች ጤንነት መነገድስ ስንት ያተርፋል?ምን ይሉት እርካታንስ ያጎናጽፋል?ከእኛ ስር የበቀለው የነገይቱ ኢትዮጵያችን ተረካቢ ትውልድስ ይህን አስጸያፊ ድርጊት እንዴት ይመለከተዋል ትላላችሁ ?ሁላችንንም ቸር እና ፍጹም የሆነው እግዚአብሄር ይርዳን፡፡
በተለይ እኔ ባለሁበት የእስር እና የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገለጽ ሐሳብ ፣ስሜታዊነት ሊንጸባረቅበት ቢችል እንኳ ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ሌሎችን ለመውቀስም የጥላቻ ስሜትንም ለመግለጽ ተደርጎ እንዳይወሰድብኝም በትሕትና እጠይቃለሁ፡፡
ክብር እና ፍቅር የሚገባችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅር እና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡ደግሞም እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ የታሪክ ፣የእምነት፣የወግና የባህል በአጠቃላይም የማንነት ጽኑ መሰረት አለን፡፡
ትናንት የመጣን ነገ የምንሄድ አይደለንም ፣እንኖራለን ቢያንስ ትውልድ ይኖራል፡፡ታዲያ እንዴት ሕክምና በመንፈግ ፣ከቤተሰብ አርቆ በማሰር (የሁለትዮሽ እንግልት ለመፍጠር በማሰብ)ይህንን ማንነት እንጣው?አይሆንም!
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
አክባሪ ወንድማችሁ ውብሸት ታዬ         ምንጭ .ዳዊት ሰለሞን

No comments:

Post a Comment