Wednesday, December 25, 2013

ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!


ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ።
ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ።
በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል።
በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።

ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።
በዚህ ዙሪያ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የአንባስደሩን አማካሪ ዲፕሎማት አቶ ዘላለም እና አንባሳደር መሃመድ ሃሰንን ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም !
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment