Monday, December 30, 2013

በትግራይ ክልል ውስጥ በእብድ ዉሻ ለተነከሱ ዜጎች በቂ መድሓኒት ባለመገኘቱ ዜጎች ለአደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው ተገለጠ፣


Dec. 30, 2013

መረጃው እንዳመለከተው በትግራይ ከተሞች የዉሾች በሽታ እየጨመረ መሆኑንና ለዚህ አደገኛ በሽታ ለመከላከል ተብሎ የተሰጠ ክትባትና። ሰዎች ከተነከሱ በኋላ የሚታከሙበት የተዘጋጀ መድሃኒት ባለመኖሩ, በርከት ያሉ ዜጎች ብበሽታ በተለከፉ ዉሾች ተንክሰው የተሟላ ህክምና ባለማግኘታቸው ለስቃይ እና ሞት ተጋልጠው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል::

በዚህ ወቅት ባበዱ ዉሾች መነከስ ምክንያት በየአካባቢው በርከት ያሉ ዜጎች በበሽታው ተለክፈው እንደሚገኙ የጠቆሞው መረጃው። በዚሁ ግዜ የማይሰጥና መፍትሄ ያልተገኘለት አሰቃቂ በሽታ የተደናገጡ የሕብረተሰብ አካላት በታህሳስ 2/ 2006 ዓ.ም ወደ ክልል ጤና ቢሮ ሄደው በጠየቁበት ግዜ። የመድሃኒት እጥረት ስለ ገጠመን ምንም ልናድርግ አንችልም ተብለው ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ ያገኘነው መረጃ አስረድተዋል::

መረጃው አክሎ በሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ያላገኙ በበሽታው የተለከፉ ወገኖች። የሞት እጣ እንዳጋጠማቸውና በሆስፒታል ውስጥ ገብተው መድሃኒት ባለማግኘታቸው የሞት ዕጣቸው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል::

Source : ዴ.ም.ህ.ት

No comments:

Post a Comment