Tuesday, December 31, 2013

እስቲ አንድ ሆነን እንነሳ ,አንድነት እኮ ሃይል ነው !!!


አገራችን ከ መችውም ጊዜ በላይ የእኛ እርዳታ ያስፈልጋታል.. እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልህ ስፍራ የለም:: አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ የሚኖረን በመሆኑ ሁላችንም በተገቢው መጠን በሃገራችን ፖለቲካ ላይ አውንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር የምንቸገር ሊሆን ይችላል ...  
ለጋሸ አገራት የሚያወጧቸው ሃሰተኛ ጸረ አፍሪካ ሪፖርቶች በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ተገን አድርጎ የተመቻቸው የብሄራዊ ጥቅማቸው ፎርሙላ ስኬት የአምባገነኖችን እድሜ በማስረዘም ህዝብ እንዲጭበረበር የህዝብ ጥያቄዎች እንዲደናቀፉ ለገዢዎቻችን የልብ ልብ ሰቷቸዋል:: ለብሄራዊ ጥቅም አስጊ ይሆናሉ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን እስከማጨማደድ ከተቻለም አንዲጠፋ በማድረግ እና በእጅ አዙር ህዝባዊ ጥያቄዎች እንዲታፈኑ እየተደረገ አምባገነናዊ አገዛዝን አፍልተውብናል, ምን ይደረግ ተረጅ መሆን በራሱ የሚያመጣው ሳንካ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም:: 
እርስ በርሳቸው የሚላተሙ አንድ ኣቁዋም እና ኣንድ አላማ ይዘው የማይግባቡ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በላም አለኝ በሰማይ ተስፋ ህዝባችንን አረንቋ ውስጥ እየጨመሩት ነው: በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ መሆኑ ግልፅ ሆኖ, አንድ አላማ ይዘው የማይግባቡ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የህዝባችንን የመታገል ስሜት አሉታዊ በሆነ መልኩ ማዳከማቸው አሳዛኝ ነው ::

መሰረታዊ ፍላጎቶች እና የአገልግሎት ፍጆታችን በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበት አገር መንግስት ፕሮጀክት ለመጨረስ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ በሚልበት አገር ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የለኝም በሚልበት እና የመንግስት ካዝና ባዶ ሆኖ በዕቃ ግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ለቱጃሮች መንግስት ያለምንም ማስያዣ ገንዘብ በሚበደርባት አገር ጥቂት ፖለቲካው የወለዳቸው ሃብታሞች እና እጅግ ብዙ የኢኮኖሚ ድቀት ያፈራቸው ደሃዎች በፈሉበት አገር ምን አይነት የኢኮኖሚ እድገት እንደተመዘገበ እራሱ ወያኔ  ቢያብራራው የተሻለ ይሆናል ::ለጋሽ አገሮች ከእኛ የሚያገኙት ብሄራዊ ጥቅም ሞቅ ባለ ቁጥር ኢኮኖሚያችሁ በመቶ ይህን ያህል አድጓል ይሉናል::  በሃገሪቱ ውስጥ ያለው የሃብት ክፍፍል ጤናማ ያለመሆኑን ሁላችንም  የምንገነዘበው ግልፅ የሆነ የአደባባይ  ሚስጥር ነው .ለጋሽ አገሮች ከእኛ ስለሚያገኙት ብሄራዊ ጥቅም ኢኮኖሚያችሁ በመቶ እጥፍ ይህን ያህል አድጓል ቢሉ እንኩዋን ትውልዱ ያለውን እውነታ መጋፍጥ ይኖርበታል ኮ .... እስከመቼ የአምባገነኖችን ደጋፊዎች ዉሸት ተሸክመን እንዘልቃለን ? በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ ነው:: 
ወያኔም ማን እንደወከላት አይታወቅ ፖለቲካዊ ማጭበርበር እና ኢኮኖሚያዊ ደላልነትን አፋፍማዋለች ,ታዲያ እኛ ቢያንስ በዚ ጊዜ እንኩዋን ምናለበት  ቢያንስ  ያለንን ልዩነት አጥብበን  በአንድ ልብ በጋራ ጠላታችን ላይ መዝመት ብንችል ,ኣንድነት ሃይል ነው የተባለው እውነት ይመስለኛል . 

መታሰቢያ ታደሰ
እግዚአብሄር  ኢትዮጲያን ይባርክ 

No comments:

Post a Comment