Saturday, December 7, 2013

ኢትዮጵያ ለማንዴላ ሀዘን ከሰኞ ጀምሮ ለሶሰት ቀናት ሰንደቅ ዓላማዋን በግማሽ ታውለበልባለች ....


አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ በሞት በመለየታቸው ከሰኞ ህዳር 30፣ 2006 ዓ.ም  ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ  ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወሰነ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ማንዴላ በሃገራቸው የአፓርታይድን ሰርዓት ለማስወገድ የተደረገውን ከፍተኛ ትግል የመሩ የነፃነት ታጋይ ናቸው ነው ያለው።
ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በህዘቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር ያበረከቱት አስተዋፅኦም ከትውልድ ሃገራቸው ደቡብ አፍሪካ አልፎ በመላው አፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያስገኘላቸው እንደሆነ ገልጿል።
በሃገራችንና በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ መሪ ኔልሰን ማንዴላ መካከል ያለውን የረዥም ዘመን ወዳጅነትን ምክር ቤቱ አስታውሷል።
ኔልሰን ማንዴላ  በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር በ1960ዎቹ በኢትዮጵያ ቆይታ የነበራቸው ሲሆን፥  በአገራችንም  ወታደራዊ  ሰልጠና በመውሰድ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

No comments:

Post a Comment