Wednesday, December 4, 2013

እኔ የማይገባኝ ሌሎች ግን የገባቸው ነገር አለ ....

እኔ የማይገባኝ ሌሎች ግን የገባቸው ነገር አለ ይኸውም በሃገራችን ህግ የበላይነት አለ ብለው ፍጹም በማመናቸው ይሁን በሌላ ምክንያት አይገባኝም ሲላቸው ፍርድ ቤት ሄደው ክስ ሲቂርቡ ሲላቸው ሲከሰሱ ህጋዊ እና ህጋዊ መንገድ ብቻ ተከትለን ነው የምንሄደው በማለት ራሳቸውን በማሞኘት ሲከራከሩ አያለሁ፡፡  

ታዲያ ፍርድ ቤቱ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያቶች ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ብሎ ህጋዊን መንገድ ሲተው ጩኀታቸውን ያሰማሉ፡፡ ታዲያ ይልቁን የሚገርመኝ አንዱ ከሌላው አይማርም ፡፡ 

ስዬ ከታምራት አይማርም ብርቱካን ከስዬ አትማርም፤ የቅንጅት ታሳሪዎች ከኦነግ ታሳሪዎች አይማሩም ፤ የሙስሊም ጉዳዮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ከአንድነት ታሳሪዎች አይማሩም ውብሸት ከርዮት አይማርም ሁሉም ብቻ ችግሩ ራሱ ላይ ሲደርስ ብቻ የህግ የበላይነት የለም ሲሉ ይታያሉ፡፡ 

ማን ይሆን የወገኔ መጎዳት የእኔ መጎዳት ነው የወገኔ ጥቃት የእኔ ጥቃት ነው የሚለው ከእማማ አልማዝ ጠባሳ ተምረን በእሳት መጫወት አቁመን ወይ እሳቱን በአግባቡ ለመጠቀም የምንሞክረው አሊያም እሳቱን የማናጠፋው፡፡ እረ ሰው ሰው እንሽተት ሰው መሆን እንኳን ቢያቅተን፡፡ እውን እኛ እውነት የቀደሙ የአባቶቻችን የጀግኖቹ የአርበኞቹ ልጆች ነን ፡፡ 
እሳት አመድ ወለደ ይልኋል ይሄነ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ህጋዊ እና ህጋዊ መንገድ ሲባል ሁሌም ፍርድ ቤት ብቻ አይደለም ሁለት ማሳያ ብቻ ልናገር
1. አንድ ሰው ንበረቱን ይዞ ሳለ ሌላ ሰው ቢወስድበት ቢመጣ ህጋዊ የሆኑ ሁለት ምርጫ አለው አንድ በጉልበቱ ነጥቆ የማስመለስ ሁለት አቅም ከሌለው ለህጋዊ አካል ሄዶ በመጠቆም ጉልበት እዲሆኑት መንገር

2. በሁለት ሃገራት መካከል አንድ ሃገር ቀድማ ሌላዋን ሃገር በጉልበት ብታጠቃ ሌላኛዋ ሃገር ሁለት ምርጫዎች አሏት አንድ በሃይል ጥቃቱን መከላከል ሁለት ጉልበት ከሌላላት ለአለም አቀፉ ማህበር በመናገር ሃይል እዲሆኗት መለመን
ይሄ እንግዲህ ህጋዊን አመራጭ ነው በህግ እውቅና ተሰጠው ፡፡ ስለዚህ 22አመት ሙሉ ሲያጨበረብር ሲታልልህ ፤ሲልም በጉልበት መብትህን ክብርህን ንብረትህን ሲነጥቅብህ ህጋዊ የሆኑ ሁለት አማራጮች አሉ ማለት ነው፡፡ 
ልቦና ይስጠን,,, የአባቶቻችን ልጆች ያድረገን

Hirut Hailu

No comments:

Post a Comment