Wednesday, December 4, 2013

ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረጉ ያሉ ችግሮች መፍትሔ ያላገኘ ችግር እየተባባሰ ሄዶ አገርንና ሕዝብን ለአደጋ ይዳርጋል



#Ethiopia #eprdf  #UDJ

ምንሊክ ሳልሳዊ:-በኢትዮጵያ ውስጥ በቅድሚያ መፍትሄ ማግኘት ያለበት የመንግስት አመራር እና ፖሊሲ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ ነው:: ወያኔ ተሸክሜዋለሁ ከሚለው መንግስታዊ የህዝብ ሃላፊነት አንጻር ሲታል ለዜኦች እና ለሃገሪቱ ደንታ ቢስ በሆኑ ብድናዊ የማይናበቡ አመራሮች ታጥሮ ከፊቱ የማይፈታው ከባድ አደጋ በራሱ እና በሃገኢቱ ላይ ጋርጧል::በሃገራችን ውስጥ ጠንካራ እና የጋራ የሆነ ንቁ መንግስት አለመኖሩ ህዝቦች ነገን በጭለማ እንዲያማትሩ እያደረገ ሲሆን በፖለቲካ ዱላ እየታሸ ያለው ህዝብ በኑር ውድነት እየተገረፈ ያለው ህዝብ ከአደጋ ራሱን ለማዳን እየተራወተ እየታገለ ይገኛል::

የወያኔ ገዢዎች ሃገርና ሕዝብን ሳያወያዩ እና ሳያማክሩ በሚፈጥሩት የሰነድ እና የጥናት የእቅድ ጋጋታ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መቃብር ውስጥ ከመክተታቸውም አልፈው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ራሳቸው የፈጠሯቸው ፕሮጀክቶች በገንዘብ እጥረት ምክንያት እየቆሙ ሲሆን የፖለቲካ ጡዘት በወሕኒ እንዲገደብ መደረጉ የሃይማኖት ጥያቄዎች መፍትሄ አለማግኘታቸው የሰው ልጅ መብቶች ሕጋዊ መሰረት አለመያዛቸው እንዲህና የመሳሰሉት ጉዳዮች መፍትሄ ስላልተሰጣቸው ተስፋፍተው ሃገሪቱን አደጋ ውስጥ መንግስት ነኝ ባዩንም አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል::

ገዢው ፓርቲ ውስጣዊ አንድነቱ ተናግቶ በሃገር አመራር ላይ በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው አለመናበብ እናም መራራቅ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ለመጣው ችግር ዋነኛ መንስኤ ከመሆኑም በላይ የህዝብ አካል ነኝ የሚል ዝግጁነት ከነኣካቴው ጠፍቷል::የገዢው ፓርቲ ሰዎች በሙስና ተጨማልቀዋል::ይህ ሙስና ከመስፋፋቱ በፊት ምንም አይነት እርምጃ ሲወሰድ አይታይም የሙስና ምንጩን ማድረቅ ሳይሆን የተያዘው በፓርቲ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና ወዳጆቻቸውን መንከስ አስመስሎታል:: ከሙስና አንዱ አካል የሆነው የፖለቲካ ሙስናም በአመራሮቹ ውስጥ ተስፋፍቶ የህዝብ ጩኸት ሰሚ አቷል::በተለያዩ መስኮች የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሙስናዎች እንደአዲስ እየተፈጠሩ ነው:;ይህ አደገኛ አደጋ መፍትሄ ካልተበጀለት....
የወያኔው ጁንታ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለበት የሃገሪቱ በጀት ጸደቀ ለዚህ ፕሮጀክት ይህን ያህል ተመደበ እየተባለ በቃላት ጣፍጦ ቢወራም ተግባር ላይ ግን ተመደበ የተባለውን ለመልቀቅ ከባድ ፈተናዎች ውስጥ ገብቷል::የበጀት አፈጻጸም እንዳይኖር ከባድ እንቅፋቶች እየገጠሙ ነው የባንጎች እንቅስቃሴ ከመድከሙም በላይ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ከባድ እና የማይፈታ የገንዘብ ግሽበት እና መፍትሄ ተብለው የሚወሰዱ ውሳኔዎች ወያኔን ናላውን አዙሮታል::

ህዝቡ አቤቱታውን የሚያሰማበት አካል የለም:; መልካም አስተዳደር ፖለቲካን የተመረኮዘ እንጂ ህዝባዊነትን ያቀፈ አይደለም የመንግስት ባለስልጣናት እና የህዝብ አገልጋዮች በፓርቲ ስብሰባ ተጠምደው እለት ከእለት የህዝኡን አቤቱአይደለም የቤተሰቦቻቸውን ፍቅር እና እንክብካበ ሊያስተናግዱ አልቻሉም::የፓርቲ ስራ እና የመንግስት አገልግሎች በጋራ መማከሉ አለመለየቱ ከባድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየፈጠሩ ናቸው ይህ ደግሞ የገዢው ፓርቲ አደገኛ አካሄድ የፈጠረው አደጋ ነው:: ...የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መፈታት ሃገርን ከአደጋ ይታደጋታል ሰላምንም ይሰጣታል::

በአሁን ሰአት ከበፊቱ በባሰ መልኩ ከፍተኛ የተማረ የሰው ሃይል እንዲሁም የሰለጠነው በተጨማሪም ከስደት ተመላሹ ዜጋ በስራ አጥነት ተወጥሮ ስለሚገኝ የስራ እድሎች እንዴት እንደሚፈጥር ወያኔን ግራ ገብቶታል:: ዜጎች በሃገራቸው የሚገባቸውን መብት ማግኘት ከጀመሩ እና ባወጡት ህግ መገዛት ከቻሉ እንዲሁም እያንዳንዱ ዜጋ በሃገሩ እንዲያገባው ተደርጎ ከተገራ እና እኔ አውቅልሃለሁ ማለት ከቆመ በተጨማሪም ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ተደርገው በሃሳብ አማራኝ ላይ ለሃገር የሚበጀው ከተሰራ ሁላችንም በነጻነት መኖር እንደምንችል ማረጋገጥ እወዳለሁ::

No comments:

Post a Comment