Thursday, December 5, 2013

‹‹አድርባይነት›› የወያኔ/ኢህአዴግ መለያ ባህሪው ነው።


የወያኔ/ኢህአዴግ መለያ ባህሪው ነው።
‹‹አድርባይነት›› ምን ማለት ነው?
አንድ መልካም እድል ሲገኝ በዚያ ዕድል ቀዳሚ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያንቀዠቅዥ ልክፍት አለ። የዚህ ልክፍት መጠሪያም ‹‹አድር ባይነት›› (Opportunism) ይባላል።

መልካም አጋጣሚ ወይም ዕድል (Opportunity) ሲገኝ በዚያች ለመጠቀም ያለምንም ይሉኝታ መሽቀዳደም፤በስተኋላ ሊከሰት የሚችለውን ጎጂ ውጤት እያወቁም ቢሆን ‹‹እንደ አመጣጡ እመልሰዋለሁ›› በሚል ድፍረት
መግባት፣ ከየት አመጣ? እንዴት አገኘ? በምን ዘዴእዚህ ደረሰ? የሚሉ የህዝቡ ምን ይላል ጥያቄዎችን ወደ ጎን አሽቀንጥሮ ጥሎ ጥቅም ፍለጋ ሲል ብቻ ለመሰል አለቆቹ እየተሽቆጠቆጠና የእሱ ቢጤዎችን እያሰባሰበ የሚንቀሳቀስበት አሰራር አድርባይነት ነው። 

ሰውሸንኮራ አገዳ አይደለም፤ እየተመጠጠ አይታይም። ከላይ ስታየው የሚጣፍጥ የመሰለህ አገዳ ገዝተህ ስትቀምሰው ሊጎመዝዝህ ይችላል። የአድርባይም ጉዳይ እንዲሁ ነው።አድርባይነት የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉየግል ጥቅምና አላማን ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ አቋምን ያመለክታል። 

ጥቅም የሚያስገኝ እስከሆነ ድረስ ማንኛውንም አቋም ለማራመድ (ለመደገፍ) ቆርጦ መነሳትን፣ ለግምገማም ሆነ ለህጋዊ ተጠያቂነት ንቀት ማሳየትን፣ የህዝብን ውክልናና ስልጣን አሳንሶ ማየትን፣ አይንን በጨው አጥቦ ለጥቅም ሲሉ ብቻ የድርጅቱን ራዕይመመሪያና ደንቦችን የህዝብን ትዝብትና ሃይማኖትንጭምር ጨፈላልቆ ለመሄድ ያለንን ውስጣዊ የጠባይ(የባህርይ) ዝግጁነት የሚያሳይ ክፉ አመለካከት ነው።አድርባይ ሰው በድርጅቱ የፖለቲካ አቋምአያምንም። 

ያመነ የሚመስለውና ከእሱ በላይ ተቆርቋሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ለመሪዎቹ(አለቆቹ) ፍቅር ያለው ይመስል የሚሽቆጠቆጠው ያቺን ያሰባትን ጥቅም በእጁ እስኪያስገባና ተጨማሪ ጥቅምለማግኘት የሚያስችል እድል (አጋጣሚ) Opportunity እስካለ ድረስ ብቻ ነው። 

‹‹የራስ ጥቅምን መፈለግና ለዚህም ተግቶ መንቀሳቀስ ምን ችግር አለው?›› የሚልጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ሁላችንም የምንሰራው ለመጠቀም ነው። ራሳችንንና ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ሰው የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው። መሬት፣ መኪና፣ቤት፣ ኢንቨስትመንት፣ አካውንት፣ ደህና ዕቁብ ጥሩዕድር ቢኖረንና የጣፈጠ በልተን ያማረ ለብሰን ብንኖር አንጠላም። ይህ ደግሞ ኃላፊነት በሚሰማውና በእውቀትና በጉልበት ተሳትፎ ተሰርቶ የሚገኝ ሲሆን ደስ ይላል።

እንደ ምርጫና ወዘተ... በመሳሰሉት አጋጣሚዎች በተገኘእድል ከህዝብ በተሰጠ አደራ የራስን ጥቅም ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ እሽቅድድም ግን አያዋጣም።አድርባይነት በፓርቲና በመንግስት ተቋማት ኃላፊዎችና ሠራተኞች አማካይነት ሲፈፀም ከፍተኛ ችግር ያስከትላል።ታማኝነት (Loyalty)... ግልፅነት(transparency)...ምስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)... ሀቀኝነት(Honesty) ተጠያቂነት (Accountability) አለማዳላት(Impartiality)...ምላሽ ሰጪነት (Responsiveness)አርአያ መሆን (Exemplary) የህዝብ ጥቅም (Public Interest) ወዘተ... የሚባሉት መሰረታዊና ስትራቴጂክ የዕድገት እሴቶቻችን በሙሉ ጥንጣን እንደበላው የበረሃዛፍ ውስጥ ውስጡን እየተቦረቦሩ ያልቁና ራዕያችንን ገንድሰው ይጥሉብናል። ከዚያ ኋላማ ‹‹የማን ቤት ጠፍቶየማን ሊበጅ... የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ›› እያልን እርስ በርስ ከመጨካከንና ከመተራረድ በቀር የሚተርፈን ነገር የለም።ይህ ማለት ደግሞ ሰዎችን ስንጠረጥራቸውእንኑር፣ ወይም በየጆሯቸው ስር መረጃ እናቁምባቸው፣ስህተታቸውን የሚያሳብቅ ቃጭል እናንጠልጥልላቸው ማለት አይደለም። 

ወደንና ፈቅደን እንደሰው መጠን አገናዝበን የመረጥናቸው ወኪሎቻችንና አገልጋዮቻችን ስለሆኑ አዲሶቹ በአድርባይነት በሽታ እንዳይለከፉና የተለከፉትም ከዚህ የአድርባይነት አስተሳሰብ እንዲወጡ በተቻለን አቅም እንርዳቸው፣ እናግዛቸው ማለት ብቻ ነው። 
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment