Thursday, December 5, 2013

የሰው አገር ማምሻ እንጂ ማደሪያ አይደለም!!


በአንድ የታሪክ ሂደት አስገዳጅነት በተከሰተ ሁኔታም ይሁን ፣ ተፈጥሮ በቸረው ልዩነት ፣ እንደ ጌጣችን ልናየው ፣ የሚገባን ታሪካችንን ፣ አንዱ ከሌላው ፣ የተመረጠ ፣ የተሻለ ፣ ቆንጆ ፣ ጸጉረ ዞማ ፣ አፍንጫ ሰልካካ ፣ ጎበዝ ተዋጊ ፣ ታላቅ ሕዝብ ፣ ወርቅ ሕዝብ .......ወዘተ የመሳሰሉ ፣ በጣም ኋላ ቀር የሆኑ ዘረኛ ፣ ቅጽላዊ ማበላለጦችን በሕዝባችን መሃል ፣ በአለንበት በሃያ አንደኛው ዘመን ማዳመጡ ጆሮ ያሳምማል ፤ አንገት ያስደፋል ፣ ተስፋ ያጨልማል ፡፡ ይህ አይነት አላስፈላጊ ወገንተኝነት ፣ ቆመንለታል ለሚሉት ክፍል ከሌላው ወገኑ እንዲነጠልና ፣ የጥቃት ኢላማ እንዲሆን ከመርዳት ባሻገር የሚጠቅመው ነገር የለም ፡፡

በእርግጥ በማንኛውም ወገናችን ላይ በተናጠል የሚደርሰው ፣ በጎም ይሁን ጉዳት የጋራችን መሆኑን መቀበል አለብን፡፡ የማንኛውም ክፍል ወጋናችን በተናጠልና በተራ በሚደርስበት ፣ መሰቃየት ፣ መታሰር፣ መፈናቀል ፣ መጋዝ ፣ መዋረድ ፣ ለሌላውም ህመም ሆኖ ሲሰማው ኖርዋል ፡፡ ለመፍትሄውም አብሮ ተዋድቋል ፣ ታግሏል ፣ አብሮ በደም የተሳሰረ አንድነት ገንብቷል ፡፡ ያም እየተደናቀፈም ቢሆን ወደፊት ይቀጥላል ፡፡
ለሰባዊ መብቶች (human rights)መቅደም ስንታገል ፣ ዘር ፣ ሃይማኖት ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ ታላቅነት ፣ ጀግነት ፣ የመሳሰሉትን ``እንደ መለኪያ `` አስቀምጠን ሳይሆን ፣ ወይም በቡድንና ፣ በግለሰብ የተደራጁና ያልተደራጁ በሚል ስሌት ከፋፍለን ሳይሆን ፣ በዚህ ምድር ላይ ለተፈጠረ ፣ ለሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮዋዊ መብቱ የተጣሰ በመሆኑ ብቻ ነው ፡፡

በሌላው ወገናችን ላይ የሚደርሰው፣ እስር፣ እንግልት ፣ መፈናቀል ፣ የሚሰማን ፣ የእኛ በምንለው ላይ ብቻ ሲደርስ ከሆነ ? የሌላው ወገናችን ስቃይና መከራ ፣ እንደራሳችን የማይሰማን ከሆነ ? ሕዝባችንን ያስተሳሰረውን ሰንሰለት እየበጣጠስን ፣ ለጎጣችን ፣ ለመንደራችን ፣ ብቻ የምንጨነቅ ከሆነ፣ በእውነት እንደ ናዚዎቹ ፣ በዘረኞች በሽታ እንደተለከፍን መቀበል አለብን

አሁን የምናደርገው እንቅስቃሴ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በእርግጥ በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ህብረት አሳይተናል፡፡ ለነገሩ ኢትዮጵያዊያን ስንነካ እንደ ንብ ግር ብለን ህብረታችንን እናሳያለን፡፡ ግን ይህ ብቻ በቂ ነው ወይ?
መፍትሄውን ለማበጀት እስከ ጥግ መሄድ አለብን በሰው አገር ተቀምጠን መኩራራቱ መፍትዬ አይሆንም።የሰው አገር ማምሻ እንጂ ማደሪያ አይደለም!!!


ባጠቃላይ ይህን ሁሉ ዘርፈ ብዙ የጋራ ችግራችንን፣ ለማስወገድና አደጋውን ለመከላከል የምንችለው፣ ባልሆነ ተስፋ እራሳችንን በማታለል ፣ ወይም በእልህ እነሱ በሄዱበት የጎጥ መንገድ በግልባጩ ተጉዘን ሳይሆን ፣ ሰከን ብለን ፣ ትግላችንን ሳናቀዘቅዝ ፣ ትጥቃችንን ሳናላላ ፣ ለዋናው ብሔራዊ ደህንነታችን ስንል መለስተኛ ልዩነቶቻችንን በይደር አቆይተን ``cease-fire`` ይህች ሓገር እንደ ሃገር እንድትቀጥል የምንፈልግ የአንድነት ሃይሎች ፣ ጋባዥ ሳይጠራን ፣ አስተናጋጅ ሳያስፈልገን፣ ግርግር ፣ ድግስ ፣ አሜሪካ ኦባማ እያልን ``መቀላወጥ`` ሳናበዛ ፣ እንደ ጥንቱ አባቶቻችን ፣ ተፈላልገን ፣ ተጠቃቅሰን ፣ ተሰባስበን ፣ ተደራጅተን፣ ብሔራዊ አጀንዳችንን ቀርጸን በጋራ አምርረን መታገል ስንጀምር ብቻ ነው፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment