Sunday, December 8, 2013

የአፄ ምኒልክ 100 ኛ ሙት-ዓመትና ክንዋኔዎቻቸው


minilikበዘመኑ ብቸኛይቱን አፍሪቃዊት ነጻ ሀገር ይመሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ህዝባቸውና የጦር አለቆቻቸውን አስተባብረው ፣ መላ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የዘመተውን የኢጣልያ ጦር ኃይል አድዋ ላይ ድል በመምታት ፣ በዘመኑም የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩ ስልክና ባቡር ሐዲድ በማስገባት ፣ ት/ቤትና ባንክ የመሳሰሉትን ተቋማት በመክፈት ይታወቃሉ።
 በውጭው ዓለም የተፈሩ ፣ የተከበሩ ፣ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩ አፍሪቃውያንና ከባህር ማዶ ፣ በካሪቢያን ደሴቶችና በሰሜን አሜሪካ፣ ለአፍሪቃ ዝርዮች እንደ ነጻነት አባት፤ ሀገራቸውም የጥቁር ህዝብ አለኝታ ሆና ትታይ ነበር። 
ከጦርነት ይልቅ፤ ውዝግቦችን በሰላም፤ በዘዴ ፣ መፍታትን ይመርጡ የነበሩት ንጉሠ-ነገሥት፣ ሉዓላዊ ግዛት በመመሥረቱ ረገድ፣ በዓለም ታሪክ ውስጥ የተለዬ ነገር ባያደርጉም፤ ካረፉ ከ 100 ዓመታት ወዲህም፣ ብዙዎች የሚወዷቸውንና የሚያደንቋቸውን ያክል የሚወቅሷቸውና የሚከሷቸውም አሉ። 
አጼ ምኒልክና ክንዋኔዎቻቸው በታሪክ እንዴት ይመዘናሉ?በዛሬው እንወያይ፣ የዳግማዊ አፄ ምኒልክን 100ኛ ሙት ዓመት መነሻ በማድረግ፤ ክንዋኔዎቻቸውን ፤ ውርሳቸውን በአጭሩ እንቃኛለን። 
Source/www.dw.de.com

No comments:

Post a Comment