Wednesday, January 1, 2014

ኦሕዴድ/ኢሕኣዴግ የቴዲ አፍሮ የፍቅር ጉዞ ኮንሰርት እንዲሰረዝ ደብዳቤ ጽፏል::


ኦሕዴድ/ኢሕኣዴግ የቴዲ አፍሮ የፍቅር ጉዞ ኮንሰርት እንዲሰረዝ ደብዳቤ ጽፏል:: ‪#‎MinilikSalsawi‬
የመንግስት ባለስልጣናት በቀጥታ እጃቸውን አስገብተዋል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Bedele‬
በሄይከን በደሌ ላይ ጫና ቢበረታም የካምፓኒው ማኔጅመት ኮንሰርቱን ላለማቋረጥ እየጣረ ነው:: ጥረቱ እንደቀጠለ ነው::ሔይከንስ በደሌ ቢራ በይፋ ከመንግስት አቋርጡ የሚል መመሪያ እስካልመጣ ድረስ በአንድ ግለሰብ በወጣ ሌሎች አናውቅም ባሉት በፓርቲ ደብዳቤ ኮንሰርቱ አይቋረጥም በሚል አቋሙ እንደጸና ነው::
        የሕወሓት ታማኝ እና ታዛዥ ሰዎችን የሰበሰበው እና ራሱን የኦሮሞ ህዝብ ወኪል አድርጎ በሕወሓት የጦር እልቅና ሕዝቡን እየጨቆነ የሚገኘው ኦሕዴድ/ኢሕኣዴግ በበዴሌ ቢራ በኩል የሚደረገውን የቴዲ አፍሮ የፍቅር ጉዞ እንዲቋረጥ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩ ወደ ፋብሪካው ከመደውል እና ውጥረት ከመንዛት ጀምሮ እስከ ደብዳቤ መጻፍ ድረስ የደረሰ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::እንዲሁም በተጨማሪ ኢሕኣዴግ በኦሮምኛ ቋንቋ በሚተላለፉ የመንግስት ሚዲያዎች ሁሉ ጸረ ምንሊክ የጥላቻ ዘገባዎችን በተከታታይ በወጣ ገባ እያቀረብ የሚገኝ ሲሆን ይህም እንዲቀጥል ተደርጓል:: በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የታቀዱ መንግስት ሰራሽ ተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዱ አይካሄዱ በኦሕዴዶች መካከል ጭቅጭቅ ፈጥረዋል::
         የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ባለቤት የሆነው የአውሮፓው ሄንከንስ ቢራ ከቴዲ አፍሮ ጋር ባደረገው ውል የመጀመሪያው ክፍያውን 1.5 ሚሊዮን ብር በቴዲ አፍሮ ስም በቼክ ቢሰጥም ለጊዜው ብሩ እንዳይገባ የተደረገ ሲሆን ኮንሰርቱ ባይካሄድም ገንዘቡ መከፈሉ አይቀሬ ነው::የሄይከን በደለ ቢራ ኮንሰርቱ እንዳይቋረጥ እስካሁን ከመንግስት ባለስልታናት ጋር ግብግብ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የፋብሪካው ማናጀር አማካሪ የሆነው የኦሮሞ ብሄር ተወላጁ ለኦሮሞ ህዝብ የበደለ ቢራ ካሳ መክፈል አለበት የሚል ሃሳብ በማቅረቡ አለመግባባት ስለተከሰተ ከስራው የለቀቀ መሆኑ ታውቋል::
           ይህን ሰሞን ኦሕዴድ ለትምህርት አሜሪካን አገር የላከውና በዲሲ የወያኔ ኤምባሲ መኖሪያው አድርጎ ከሕወሓት ዲፕሎማቶች ጋር ሳይስማማ ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ የተባረረው ጽንፈኛው ኦቦ ሜንጫ የተባለው ግለሰብ በቴዲ አፍሮ እና በበደሌ ቢራ ላይ እና በሃገር ኢኮኖሚ ላይ የጠባበኝነት እና የጥላቻ ዘመቻ በመክፈት ሕወሓት የሆኑ የቀበሮ ለምድ ለብሰው ለኦሮሞ የቆሙ አስመሳዮች ለስልታን እድሜ ማስረዘሚያ ይረዳቸው ዘንድ ሲያሟሙቁ እንደነበር ይታወሳል::ይህ አጀንዳ ያገናኛቸው ኦቦ ሜንጫ እና ኦሕዴድ በሕወሓት አበረታችነት በጋራ ዘመቻውን በመምራት ክንሰርቱን ለማስቆም አስፈላጊውን ወደ ተግባር በመግባት ስራቸውን ጀምረዋል::
         የበዴሌ አምራች የሆነው አውሮፓዊው ካምፓኒ የፍቅር ጉዞ የተባለው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርትን ለማቆም ምንም አይነት ችግሮች አለመኖራቸውና ኮንሰርቱ በታቀደለት ቀን እንደሚካሄድ ደጋግሞ ቢናገርም የኦሕዴድ አመራሮች እና ጠባብ ዲያስፖራዎች በጋራ ከተጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ በተየቡት መሰረት ኮንሰርቱ ቢካሄድ በሚነሳው የሕዝብ ቁጣ ሊከተል የሚችል አደጋ በማለት በማስፈራራት እንዲሁም የተለመደው የጸጥታ ሃይሎች እጥረት በሚል ለማስተጓጎል ጥረቱ ውስጥ ውስጡን እንደቀጠለም ይገኛል::ከዚህ ክንሰርቱን ከማስቆም ጀርባ የዲያስፖራ ኦሮሞ ጽንፈኞችን ዘመቻ አለመሳካቱ ያንገበገባቸው የሕወሃት ባለስልጣናት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::

No comments:

Post a Comment