Sunday, January 12, 2014

ኢሕኣዴግ ከግንቦት ሰባት ጋር ተቆራኝተዋል ያላቸውን አባሎቹን ሊያባርር ነው:: ‪ ጦር ሰራዊቱ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ሊያደርግ ነው::‪‬


ሕወሓት መራሹ ገዢ መደብ ኢሕኣዴግ በድርጅቱ ውስጥ ባደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ መሰረት ከተቃዋሚው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ቁርኝት አላቸው ግንኙነት ፈጥረዋል ለዲሞክራሲያዊ ስርኣቱ እንቅፋት ሆነዋል የድርጅቱን መረጃ አቀብለዋል ያላቸውን አባሎቹን ሊያባርር መሆኑን ከአዲስ አበባ የኢሕኣዴግ ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::
በዚሁም መሰረት የተደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ የተገኘ ማስረጃን መሰረት በማድረግ የሚባረሩትን አባላት እና ከተባረሩ በኋላ ሊወሰድባቸው የሚገባ እርምጃ እየተጠና መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጦር ሰራዊቱ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል::ከሻለቃ ማእረግ ጀምሮ ወደላይ እስከ ጄኔራሎች ድረስ የሚደረገው ግምገማ አጀንዳው ሙስናን ያጠቃል/አያጠቃል ባይታወቅም በዚህ ሰሞን በሕወሓቱ ጄኔራል ሳሞራ ቢሮ የተሰበሰቡት ጄኔራሎች በከፍተኛ መኮንኖች ላይ ግምገማ እንዲደረግ መወሰናቸው ሲታወቅ በግምገማው ላይ የሚገመገሙ መኮንኖች ስም ዝርዝር እንዲዘጋጅ ለወታደራዊ ደህንነት ክፍል ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቀሱ መኮንኖች እንደማይገመገሙ ሆኖም እንደሚገመግሙ ታውቋል::ምኒልክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment