Wednesday, January 8, 2014

በህወሃት ኣመራር ባለስልጣኖች መሃል እየተፈጠረ ያለው ንትርክና ልዩነት ዋነኛው መንስኤው ከህዝብና ከሃገር በሚዘርፉት ሃብት ሳብያ መሆኑ ተገለፀ፣


ለትግራይ ህዝብ ረስተው በግላቸው ንሮኣቸው ተዘፍቀው የሚገኙ የህወሃት ባለስልጣናት ካለፈው ግዜ ጀምሮው በውስጣቸው እንዳይስማሙ ያደረገው ዋናው መንስኤ ለመሰረተ ልማት እየተባለ የሚወጣው በርከት ያለ ገንዘብ ወደ ልማቱ ከመዋሉ በፊት የክልሉ ስራ ኣስፈፃሚ ኣካል በየፈርጃቸው እየወረሩ ወደ ግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሆን ተገለፀ፣
በዚሁ ቅንነት የጎደለውና ብልሹ የህወሃት ኣመረር ኣሰራር ምክንያት። ህዝቡ በተደጋጋሚ ብሶቱን ቢገልፅና ሰሚ ሳያገኝ ቢቆይም ኣሁን ኣሁን ግን በስርቆቱ ያልተካፈሉና በወረራው ውስጥ የነበሩ ባለስልጣኖች በውስጣቸው ችግር በመፈጠሩ ምክንያት። መናናቅ የወለደው ኣለመረዳዳት ሰፍኖ እንዳለ ከውስጥ ኣዋቂዎች በመጣ መረጃ መሰረት ሊታወቅ ተችለዋል፣
በመረጃው መሰረት የህወሃት ሊቀመንበር ኣቶ ኣባይ ወልዱ በኣክሱም ከተማ ለሚሰራው የእስፋልት መንገድ ማለት ለእንድ ኪ/ሜትር በኣንድ ሚሊዮን ብር ሂሳብ ወጪ የተደረገው ገንዘብ። የሱ ምክትል የሆነው ኣቶ ደብረፅዮን በንደዚህ ኣይነት ወጪ በኣክሱም የተሰራ መንገድ የለም። ይህንን መንገድ ለመንገድ ስራ በሚል ሽፋን ተጠፋፍተዋል በማለቱ ምክንያት ያነሱትን ሃሳብ ወደ መናናቅና መሰዳደብ ስላመራቸው ሳይረዳዱ እንደቀሩ ለምረዳት ተችለዋል፣
በበልሹ ኣሰራር የተጨማለቁ የሕወሃት ስራ ኣስፈፃሚ ኣባላት ከኣባይ ወልዱ ጋር በመሆን እየዘረፉት ባሉ ገንዘብ በህዝቡ ላይ ትልቅ ተቃውሞ እየቀረበባቸው ባለበት ባሁኑ ሰኣት ውስጣዊ ችግራቸው ከማየት ይልቅ ያላቸው ስልጣን ተጠቅመው እየሸፋፈኑት እንደሆኑና። ነግር ግን እንዳንድ የድርጅቱ ባለ ስልጣኖች ደግሞ የስልጣናቸው ኣድሜ ለማራዘም ሲሉ እየተቋሙዋቸው እንደሆኑና በሚያደርጉት ስባሰባ ላይም ያለ ስምምነት እንዲበተኑ ግድ ይላቸው እንዳለ መረጃው ጨምሮ ኣስረድተዋ፣
T.P.D.M

No comments:

Post a Comment