Sunday, January 5, 2014

“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ ::


“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ
የህዝብ ፊርማ ይዘን በፍ/ቤት ክስ እንመሰርታለን ብሏል
  የፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም “የሚሊዮኖች ድምፅ” በሚል መርሃግብር የህዝብ ፊርማ ሲያሠባስብ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል በቂ ድምፅ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ከ1ሚ. በላይ ፊርማ አሰባስቤአለሁ ያለው ፓርቲው፤ የህዝቡን ፊርማ በመያዝ ክስ እንደሚመሰርት ገልጿል፡፡ ፓርቲው ለ3 ወራት ባካሄደው ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ የፀረ ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሚያስችል ድምጽ ማግኘቱን የገለፁት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ አሁንም ድረስ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኦንላይን እየፈረሙ በመሆኑ አጠቃላይ የፈራሚዎቹን ቁጥር መግለጽ ቢያዳግትም፣ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ ፊርማ መሰባሰቡን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ የተሰባሰበው የፊርማ ብዛት ፓርቲው ከገመተው በላይ ስኬት መቀዳጀቱን ይጠቁማል ያሉት ሃላፊው፤ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን የፊርማ ብዛት ፓርቲያቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
    “አንድነት” ፓርቲ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ያለው አቋም ሙሉ ለሙሉ ይሰረዝ የሚል እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ የተሰበሰበውን የህዝብ ፊርማ ለፍ/ቤት በማቅረብ፣ ህጉ ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጭና የዜጐችን መሠረታዊ መብት እንደሚጥስ በመጥቀስ ክስ እንመሠርታለን ብለዋል። ከፍ/ቤት ቀጥሎም ጉዳዩን ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የገለፁት ሃላፊው፤ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም በህዝብ ድምፅ ህግ የማሠረዝ እንቅስቃሴ ተሞክሮ ባያውቅም ፍ/ቤቶች እና ምክር ቤቱ የፓርቲውንና የፈራሚውን ህዝብ ጥያቄ ተቀብለው ውሳኔ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጐችን ድምፅ ዝም ብለን ሜዳ ላይ አንጥልም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የፍ/ቤቶች ገለልተኝነት አጠያያቂ ከመሆኑ አንፃር ጥያቄው ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን ህዝቡ የተሣተፈበት የፓርቲው…..
http://goo.gl/p9g2D5

No comments:

Post a Comment