Monday, January 6, 2014

እስከ መቼ ግን ??


ይሄ ጥያቄ የሁላችንም ሀገር ወዳድ እና ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው :: እኛ ኢትዮጵያኖች መብታችን ተረግጦ ነጻነታችን ተገፎ በዲሞክራሲ ቸነፈር ተመተን መኖር ከጀመርን ከድፍን ሁለት አስር አመታቶች በላይ አስቆጠርን በእነዚህ ዓመታቶች ብዙዎች ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት ታግለዋል ነገር ግን ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት የታገሉ ብዙዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው ለብዙ መከራ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ የሀገሪቷ ዜጓች ገበሬው፣ ነጋዴው፣ ተማሪው፣ አስተማሪው ፣ጋዜጠኛው ወዘተ ......አልፎ ተርፎም የሀይማኖት አባቶችን ሳይቀር በሀገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች አጉሮ እያሰቃየ ይገኛል::
 አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም፡፡ አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐለምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆዳደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል ይበቃል ልንለው የግድ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment