Sunday, January 5, 2014

የአንድነት አዲሱ አመራር ወህኒ ቤት የሚገኙ አመራሮችን ጎበኘ

Photo: የአንድነት አዲሱ አመራር ወህኒ ቤት የሚገኙ አመራሮችን ጎበኘ
አዲሱ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ በወህኒ ቤት የሚገኙትን የፓርቲውን አመራሮች በመጎብኘት አበረታች መልእክት ተቀበለ፡፡በቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘውን የፓርቲውን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ያመሩት አመራሮች ከአንዷለም ጋር መጠነኛ ቆይታ በማድረግ ተወያይተዋል፡፡አንዷለም በአዲሱ ስራ አስፈጻሚ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ ህዝቡን ለመብቱ እንዲታገል በማንቃት ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ትፋ ማድረጉን ነግሯቸዋል፡፡
ወደ ቃሊቲ ያመራው የስራ አስፈጻሚ ቡድን ሌሎች የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት እቅድ የነበረው ቢሆንም የእስር ቤቱን ፈቃድ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ወደ ዝዋይ የፕሬዘዳንቱን መልእክት በመያዝ ያመራው ቡድን የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነውን አቶ ናትናኤል መኮንንና በዚያ የሚገኙ ሌሎች እስረኞችን ጎብኝተዋል፡፡እንደአንዷለም ሁሉ ናትናኤልም በአዲሱ የአንድነት ስራ አስፈጻሚ አወቃቀር ደስተኛ መሆኑን ለጠያቂዎቹ ነግሯቸዋል፡፡

Finote nestanet

No comments:

Post a Comment