Thursday, January 2, 2014

እንደው በታሪክ ያለ/የነበረን ስህተት የሚያስተካክል መንገድ አዳሽ እና አስታራቂ ነጻ የዜና ማሰራጫ ማእከል/ሚድያ ሃገራችን የሚኖራት መቼ ይሆንከመንግስት ተጽእኖ የወጣ እና እውነተኛ መረጃ የሚያስተላልፍ የዜና ማሰራጫ ማእከል የሚኖረን መቼ ይሆን ...
የ አንድን ዜጋ ሰበዊ መብት እና ክብር ነፍጎ የሚያምንበትን እንዳይጽፍ እንዳይናገር ማፈን ብሎም መቅጣት ምን ማለት ይሆን ?ሰውን እያደኑ በማሰር ስራ ከመሰማራት ለምንስ መንግስት የሚነቀፍበትን /የሚተችበትን ጉዳይስ እንደማያርም ግርም ይለኛል አንዳንድ ጊዜ  እንደው የመንግስት አካላት ግን ምን ይሰማቸው ይሆን ብዬ ኣስባለሁ ,ይሄንን ያክል እራስ ወዳድነት ምን የሚሉት ይሆን ... ሰው እድሜው እየፋ ሲሄድ ቲኒሽዬ እንኩዋን አያስብም ? በወጣትነት ጊዜው ያጠፋውን ለማስተካከል ,ታሪክ እንዳይበላሽ የሚችለውን ይጥራል . የኛ ጉዶች ግን ብሶባቸው ቁጭ አሉ .

ከጥላቻ ፖለቲካ የሚገኝ ትልቅ ትርፍ ያለ ይመስል በአጉል አዋቂነት በአሽሙርና በምጸት ሕዝብን ከሕዝብ ወገንን ከወገን እየነጠሉ አንዱን እያሟካሹ ሌላውን እያንያኳሰሱና እየዘነጠሉ ያለውን የዜና ማሰራጫ ማእከል  ለዚ የረከሰ  ወራዳ  አላማ  ሲያውሉት ምን ይሰማቸው ይሆን  ...

የዜና ማሰራጫ ማእከል እኮ ዜጎች  “በኢትዮጵያዊነታቸው” ብቻ ያለ አድልዎ የላቀ አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸው ለሕዝባቸው የሚያካፍሉበት የሚገልጹበትና የሚስተናገዱበት መድረክ አንጂ ተራ አሉባልታ እና ትውልድን እርስ በእርሱ እንዲናቆር ,አንዱን በዳይ ሌላውን ተበዳይ እያደረገ ትውልድ በማይደርቅ  ጥላቻ አና ቂም እንዲሞሉ እና ለበቀል እንዲነሱ የሚያደርግ ኣይደለም በተጨማሪም መረጃዎችን በማዛባትና በመሸቃቀት የሀገርንና የሕዝብን ሰላም የሚነሳ፣ ጫፍ ይዞም አገር ምድሩ በውሸትና በቅጥፈት የሚያስስ ሁከት/ሽብር ፈጣሪ መሆን ኣልነበረበትም ...

ከተራ አሉባልታ የዘለለ በቋንቋ በነገድና በባህል በየዓይነቱ የሆነው ማህበረሰብ ወደ ሰላም: አንድነትና ሕብረት የሚያመጣ የሰሚ ጆሮ ልብ የሚያሳርፍ ሙሑራዊና ሳይንሳዊ አገላለጽ ጎልቶ የሚታይበት የህብረተሰቡን እውቀት እና ግንዛቤ የሚቸምር ሊሆን በተገባው 

መረጃዎች/ዜናዎች ሁሉ ሀገራችን ላይ የሚፈትሉት አውንታዊ ተጽእኖ እና ጥቅማቸውና የሚፈትሩትም ሕዝባዊ ፋይዳቸውን እየተመዘነ ግልጽና ፍትሐዊ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ ኃላፊነት የሚሰማው የነጻ የዜና ማሰራጫ ማእከል/ሚድያ 


መታሰቢያ ታደሰ


እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ !!!

No comments:

Post a Comment