Friday, January 3, 2014

ኦሕዴድ እና ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ...

January 3/2014


በበደኖ አርባጉጉ አሰቦት አበምሳ እና በቀሪው የኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ ዜጎች የማን ትእዛዝ ነበር?
"ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው::" ሀጅ ቃሲም (ኣርባጉጉ)

የፕ/ር ዓስራት ወልደየስ የመአሕድ ፕሬዝደንት ሰኔ 1ቀን 1984ዓ.ም ቁጥር መአሕድ /48/84 ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ የጻፉት ደብዳቤ ኦሕዴድ እን ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ ነው::
አንድ መቶ አመት ወደኋላ ተመልሰን ዛሬም አእምሮኣችንን እርቃኑን ከማስቀረት ከ100 አመት በፊት ከነበሩ ያልተማሩ መሪዎች ያነሰ የሚያስቡ ባዶዎች በዚህ በሰለጠነ ዘመን የፈጸሙት ወንጀል በትውልዳችን መጠየቅ ሊኖርበት ነው ብንል ባያስኬድም ለሁሉ የሚበጀው ግን መልካሙን ይዞ ማደግ ተመራጭ ነው::

በኣርባጉጉ የአውራጃ የኦህዴድ ተወካይ አቶ ዲማ ጉርሜሳ ግንቦት 26/1984 በአበምሳ ከተማና በኣካባቢው የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆችን ስብሰባ ከጠሩ በሆላ "ኣሼ :ኦዴ:ዒመና :ኣቡሌ በሚባሉ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ " በማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ ከተሰበሰቡት የኦሮሞ ተወላጅ መካከል ሀጅ ቃሲም የተባሉ እጃቼውን ኣውጥተው
"ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው " የሚል አስተያየት በማቅረባቼው
የኦህዴዱ ተወካይ በመናደዱ ሽጉጡን ኣውጥቶ "የነፍጠኛ እረዳት ነህ በማለት ማስፈራራት ሲጀምሩ ስብሰባው የሀጅ ቃሲምን ሀሳብ በመከተል ተበተነ ::
ምንሊክ ሳልሳዊ

ይህንን ባለ 6 ገጽ የፕሮፌሰር አስራትን ፊርማ የያዘ ደብዳቤ ይመልከቱ::

Image

Image

Image

Image

Image

Image

No comments:

Post a Comment