Wednesday, January 1, 2014

የመሬት ባለቤትነት መብት ገንዘብ ላለው ሁሉ ብቻ ነው ማለት የሚያዋጣ ነው ወይ ? በሚሸጠው መሬት ላይ የሰፈረው ሕዝብ ለሱዳን ይሸጥ ወይንም አይሸጥ ብሎ በዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ወሰናል ማለት ነው ወይ ?

 መሬት የህዝብ ነው  !!!! ህዝብ  (እያንዳንዱ ) ዜጋ በመሬቱ ላይ መብት ሊኖረው ይገባ !!! ወያኔ  እያደረገ ያለው ግን የሕዝብ መሬት የሕዝብ  ሳይሆን  የወያኔ ተወካይ/የወያኔን የልብ  ባለሙያዎች የግል ንብረት እንደሆን ተቀብሎትና አምኖበት የወሰነው ነው
አንቀጽ 2 የኢትጵያ ግዛት ወሰን
የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፌዴራሉን አባሎች ወሰን የሚያጠቃልል ሆኖ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት የተወሰነ ነው፡፡ አንቀጽ 8 1. የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉኣላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው 2. ይህ ሕገ መንግስት የሉዓላዊነታቸው መግለጫ ነው 3. ሉዓላዊነታቸውም የሚገለጸው በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት ይሆናል፡፡ ከፍ ሲል የተጠቀስኳቸው ሁለት አንቀጾች ከኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ላይ የተገለበጡ ናቸው፡፡ ሰሞኑን ለሱዳን የሚሸጠው የኢትዮጵያ መሬት ቀደም ሲል ከ22 ዓመታት በፊት ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ የጸደቀ ነው በሚለው ሕገ መንግሥት ላይ ለዛሬ በሚያመች ሁኔታ የጻፈው ነው፡፡ ለነገሩ ሕገ መንግሥት ተብዬውን በወቅቱ ወያኔና ጥቂት ደጋፊዎቹ ተወያይተን አጸደቅነው ይበሉ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተቀብሎትና አምኖበት የፀደቀ ሕገ መንግሥት አልነበረም፡፡ ሥራዬ ብሎም ያነበበውና ያጤነው የለም፡፡ የሱዳን ጉዳይም ሊመጣ ይችል ይሆናል ብሎ የገመተ ሰው ይገና ብዬ አላምንም ምናልባት ተቂት የተረዱና በጊዜው ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች የሉም ለማለትም አየቻልም፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጵያውን መካከል ብዙ የሕግ ባለሙያዎችና ሌሎችም አርቆ አሳቢ ምሁራን አሉንና ነወ፡፡ እዚህ ላይ ዶ/ር መራራ ጉዲና በአንድ ወቅት የተነገረውን ማጤን የግድ ይላል፡፡ “የወያኔን ልብ እንኳን ሰው እግዚአብሔርም ለማወቅ ይቸግረው ይሆናል” ይሁን እና መሬት ሕዝቦች ነው ማለት እያንዳንዱ ዜጋ በመሬቱ ላይ መብት ሊኖረው አይገባም ማለት ነው ? ማለት ሊሆን አይችልም፤ እያንዳንዱ ዜጋ ለአገሩ መሬት ህይወቱን እስከመሰዋት ድረስ ለመገበር ግዴታ አለበት ከተባለ የግዴታው ዋጋ የሆነውን መብቱን መንፈግ እንዴት ይቻላል ? 
የአገሩ ሰው መሬት ሳያገኝ ለውጭ አገር ሰው መሬት በምንም መልኩ የሚታደለው በማን ፈቃድና ለማን ጥቅም ነው ? ዜጎችን ለአገራችሁ ለመሞት ተሰለፉ፣ ነገር ግን የመሬት ባለቤትነት መብት ገንዘብ ላለው ሁሉ ብቻ ነው ማለት የሚያዋጣ ነው ወይ ? ኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለነገሩ ሕገ መንግሥት ተብዬውን በወቅቱ ወያኔና ጥቂት ደጋፊዎቹ ተወያይተን አጸደቅነው ይበሉ እንጂ ለሱዳን የሚሸጠው መሬት ባለቤት በሆነው ክልል ተወካይ አማካኝነት ለመሸጥ እንደሆነ አካሄዳቸው ግልጽ በመሆኑ በአንቀጽ 8 ተራ ቁጥር 3 ላይ የመጨረሻው ሐረግ …በቀጥታ በሚያደረጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት ይሆናል ተብሎ የተጻፈው አንቀጽ በሚሸጠው መሬት ላይ የሰፈረው ሕዝብ ለሱዳን ይሸጥ ወይንም አይሸጥ ብሎ የመወሰን መብት አለው ሕዝብ በዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ
ተቀብሎትና አምኖበት የተወሰነ ነው ነው... የመሬት ባለቤትነት መብት ገንዘብ ላለው ሁሉ ብቻ ነው ማለት የሚያዋጣ ነው ወይ ? በሚሸጠው መሬት ላይ የሰፈረው ሕዝብ ለሱዳን ይሸጥ ወይንም አይሸጥ ብሎ በዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ወሰናል ማለት ነው ወይ ? የአድዋ ጦርነት፣ የማይጨው ጦርነት፣ የኦጋዴን ጦርነት፣ በኋላ ደግሞ የባድም ጦርነት ለመሬት ሲባል የተደረጉ ናቸው፤ እርግጥ አንዳንዴ በተለያዩ ምክንያቶች ሰፊ የአገርን ቁራሽ በወንበር ልዋጭ ወይም በስጦታ ማስረከብ ይቻል ይሆናል፤ ቅድም የጠቀስኋቸው ባለስልጣኖች ከተናገሩት ውስጥም መሬት የህዝብ ነው ያሉት ለእኔ ሙሉ እውነት ሆኖ ጦርነቶቹን ሁሉና በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የከፈሉትን የመጨረሻ መስዋዕትነት የሚያስረዳ ነው፤ ለውጭ አገር ሰው መሬት አይሸጥም ሲባል የነበረበትም ምክንያት አባቶቻችን የሞቱበትንና በህይወታቸው ዋስትና የተያዘውን መሬት ለሌላ አንሰጥም በማለት ነው፤ ይህ ካልሆነ ለባድመ ለምን ተዋጋን ? እነዚያ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ሁሉ ለምን ሞቱ ? ለምን በባድም ምክንያት ለሌላ ጦርነት እንዘጋጃለን ?

መሬትን ከወራሪ በሕይወታቸው የሚጠብቁ ዜጎች ናቸው፤ ዜጎች በመሬቱ ላይ ምንም መብት ከሌላቸው ከወራሪ ለመከላከልስ ምን ግዴታ አለባቸው ? 

መታሰቢያ ታደሰ
እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ

No comments:

Post a Comment