በትምህርት ተቋማት ላይ ቦምብ በማፈንዳት፤ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ በደረሰው የ2 ሚሊዮን ብር ዝርፊያ በመሳተፍ፣ አብያተ-ክርስቲያናትን በማቃጠል፣ አባላትን በመመልመልና አመፅ በማነሳሳት የኦሮሚያ ፌዴሬሽንን ከህገ-መንግስቱ ተቃራኒ በሆነ መንገድከኢትዮጵያ ግዛት ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ ከመሰረተባቸው 69 ተከሳሾች መካከል 45ቱ ጥፋተኛሆነው በመገኘታቸው ከ3 እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሲቀጡ 18 በነፃ ተሰናበቱ።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ባስቻለው ችሎት፤ የፈፀሙት ድርጊት በንባብ ሲቀርብ እንደተሰማነው ተከሳሾቹ በኬኒያ፣ በሶማሊያና በኤርትራ በመዘዋወር የጦር ስልጠናን በመውሰድና የአባላትን ቁጥር ለመጨመር ከመስራት በተጨማሪበሀገር ውስጥና በውጪ ከሚገኙ ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ወይም ኦነግ ለተሰኘውና መንግስት አሸባሪ ብሎ በሰየመው ቡድን ስም የገንዘብዝውውር ሲያደርጉ እንደነበር ተዘርዝሯል።
በተለይም 1ኛ ተከሳሽ ተሻለ በከሺ፤ በ1998 ዓ.ም በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ በተካሄደው ዝርፊያ ከግብረአበሮቹ ጋረ በመሳተፍ መንግስት 2ሚሊዮን ብር እንዲያጣ ከማድረጉም በተጨማሪ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ ቦምብ በመወርወር ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል። ሌላኛውተከሳሽም በኦሮሚያ ቆሬ መንደራደዩ በሚባል አካባቢ ከኦነግ አባል በተሰጠ ትዕዛዝ በ1996 ዓ.ም አብያተ ክርስትያናትን አቃጥለው ሰውገድለዋል ሲል ዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝሩን ያስረዳል። ተከሳሾቹ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ በማሴር፤ ገንዘብ በማሰባሰብና መሳሪያበመግዛት፤ አባላትን በመመልመልና በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት የሽብር ቡድኑን አላማ በመደገፍ ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ዐቃቤ ሕግያስረዱልኛል ያላቸውን ከሃምሳ በላይ የሰውና የሰንድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
የግራ ቀኙን ሀሳብ ሲመረምር የቆየው ፍርድ ቤቱ፤ ተከሳሾቹ የፈፀሙትን ወንጀል ያብራራው የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ የደረሰውን ውድመትበዝርዝር የሚያሳይ ካለመሆኑ መነሻነት የወንጀሉን ደረጃ መካከለኛ ነው ሲል ያስቀመጠው ሲሆን፤ ይህም ቢያንስ እስከ 15 ዓመት ፅኑእስራት ያስቀጣ እንደነበር በማስታወስ ተከሳሾቹ ያቀረባቸውን በርካታ የቅጣት ማቅለያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የቅጣት ውሳኔውመዘጋጀቱን አትቷል።
ሰኞ ዕለት የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎትም ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድማስረጃዎች በአግባቡ ካየ እና የተከሳሾቹንም የመከላከያ ማስረጃዎችና የቅጣት ማቅለያዎችን ከመረመረ በኋላ ቀደም ላለው ጊዜ 18የሚሆኑትን ተጠርጣሪዎች ነፃ ናችሁ ሲል በብይን ያሰናበታቸው ሲሆን፤ የሁለት ተከሳሾች ጉዳይ ደግሞ ለብቻው ተነጥሎ በመታየት ላይ ነውሲል አስረድቷል። በተቀሩት 45 ተከሳሾች ላይም የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ከ3 እስከ 12 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራትና 40በሚደርሱት ላይም ከ2 እስከ 3ዓመት የሚደርስ የህዝባዊ መብት እገዳ ጥሎባቸዋል።
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/117

No comments:
Post a Comment