Thursday, January 16, 2014

በአጋቾች የታፈነችው ሴት 4 ልጆች ወልዳ ወደ ሀገር ልትገባ ነው፡፡ ግሩም ቪዲዮ 31

በጤና ችግር ምክንያት ሁሌም መሄደድ ባልችልም በሄድኩ ቁጥር ሁሌም አሳዛኝ ነገር ነው እየገጠመኝ ያለው፡፡ የበዓል እለት እስረኞችን ለማየት እና በዓልን ለእነሱ ምሳ ማብላት አስበን ኢሚግሬሸን እስር ቤት ሄድን፡፡ ካጋጠሙኝ አሰቃቂ ነገሮች አንዱ አራት ልጅ ይዛ ብረድ ላይ እያደረች ያለች ሴት አወራኋት፡፡ አማርኛ መናገር የማትቸል በመሆኑ አስተራጓሚ ማግኘትም ችግር ሆኖብናል፡፡ የመን ውስጥ ያሉት ህገ-ወጥ አጓጓዦች ስደተኞችን እያፈኑ አሰቃይተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስደርጋሉ፡፡ እነዚህ አጋቾች ያገቷት አንዲት ኢትዮጵያዊት አንድ ልጅ ይዛ ነው ከሶማሊያ የተሻገረችው፡፡ ሶማሊያም አስገድዶ የመድፈር ሁኔታ ገጥሟት ወልዳ ነው የመን የገባችው፡፡ አሁን ደግሞ አግተው የያዟት ቦታ ሶስት ልጅ ወልዳለች፡፡ አራት በግዳጅ የመጡ ልጆች ይዛ ወደሀገር ልትገባ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment