Saturday, December 14, 2013

መድረክ በኢትዮጵያ ያለው አፈና መባባሱን ገለጸ

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ዓርብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአገሪቱ ወቅታዊ
ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መሄዱ መግለጫውን ለመስጠት አስገድዷቸዋል። የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም መድረክ ቢጠይቅም በገዢው ፓርቲ መከልከሉን ዶ/ር መረራ አውስተዋል ( 1፡49-03፡10)

መንግስት የሳውድ አረቢያ ጉዳይ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ ሊሆን አይገባም በማለት እየተከራከረ ነው ፣ የእናንተ አቋም ምንድነው ለተባሉት፣ “ዜጎች በሃገራቸው ላይ ሀብት አርፍርተው፣ እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የተሻለ ህይወትና የተሻለ ተስፋ መያዝ አለመቻላቸው ለስደታቸው ምክንያት በሆነበት ሁኔታ፣ ይህ ፖለቲካ ካልሆነ ሌላ ምን ፖለቲካ ሊሆን ነው?’ ሲሉ መልሰዋል። ስቃዩን ለፖለቲካ አንጠቀምም፣ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት የሳውዲን ጉዳይ ለፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት ነው ሲሉ መንግስትን ወቅሰዋል። “ከሳውዲ አረቢያ ጋር ወንድማዊ ግንኙነታችን ይቀጥላል” የሚል መግለጫ በመስጠት በዜጎች ሞት፣ ስቃይና እንግልት ላይ ተሳልቋል ብለዋል ( 06፡30-09፡07)

የአራት ፓርቲዎች ስብሰብ የሆነው መድረክ በሳዑዲዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን በደል በመቃወም ለሁለት ጊዜ ያህል የጠራው ሰልፍ አንድ ጊዜ ኣለም አቀፍ ስብሰባ ይካሄዳል፣ሌላ ጊዜ በቂ የፖሊስ ኃይል የለንም በሚሉ ምክንያቶች የተከለከለ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በተለይ ህዳር 29 መነሻውን 6ኪሎ መድረሻውን ደግሞ ጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት በማድረግ ሊያካሂድ ያቀደውን ሰልፍ የተከለከለበት አጥጋቢ ያልሆነ ምክንያት በርካታ የመድረኩን አመራር አባላት ማበሳጨቱ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment