Monday, December 9, 2013

የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች የዋስትና መብት ተከለከሉ



ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታስረው ከተለቀቁ በሁዋላ ተመልሰው እንዲታሰሩ የተደረጉት የቁጫ ወረዳ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ተመልሰው በአርባምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ መደረጉን ከሽማግሌዎች አንዱ ገልጸዋል።
ችግሩን ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት እስከዛሬ ሲመላለሱ የቆዩት የአገር ሽማግሌዎች አንድም ባለስልጣን ሳያገኙ በመቅረት ነገ ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው ፍርድ ቤት እንደሚቆሙና እንደ ጓደኞቻቸው የዋስትና መብታቸው ተገፎ እስር ቤት እንደሚገቡ ለኢሳት ገልጸዋል።

ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው የሚሉት ሽማግሌዎች፣ በአሁኑ ጊዜ የአካባቢው ህዝብ መንግስት አለ ብሎ እንደማያምን ተናግረዋል በጋሞጎፋ ዞን የሚገኘው የቁጫ ወረዳ ህዝብ ከማንነትና ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡

No comments:

Post a Comment