Monday, December 16, 2013

መንግስት ማይበቅል ዘር በመሰራጨቱ ውጥረት ተፈጠረ


በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ፣ ቦሌ ዴቀኛ ቀበሌ ምርጥ ዘር ተብሎ የተሰራጨው በቆሎ ሳይበቅል በመቅረቱ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን የአካባቢው
አርብቶ አደሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ በክስተቱ በአርሷደሮችና በባለስልጣናት መካከል ውጥረት ፈጥሯል፡፡የአካባቢው አርሶ አደሮቹ ለፍኖተ
ነፃነት እንዳስታወቁት በግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጉትጎታና በመንግስት ትዕዛዝ በግዳጅ የተቀበሉት የበቆሎ ምርጥ ዘር ጥራቱ የጠበቀ ባለመሆኑ ሳይበቅል
ቀርቷል፡፡ ገበሬዎቹ አያይዘው እንደገለፁት የታደሉትን ጥራቱን ያልጠበቀ ዘር በመዝራታቸው ለደረሰባቸው ኪሳራ መንግስት ሀላፊነቱን ባለመውሰዱ በአካባቢው
ከፍተኛ ቅሬታ ተፈጥሯል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጽ/ቤቱ ለኔልሰን ማንዴላ የመታሰቢያ በርሃግብር አካሄደ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ ታህሳስ
3 ቀን 2006 ዓ.ም በአንድነት ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደውን መርሀግብር በንግግር የከፈቱት የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ አስራት ጣሴ ናቸው፡፡ አቶ አስራት በንግግራቸው በታላቁ  ታጋይ ላይ ሊደረግ የነበረን የግድያ ሙከራ ኢትዮጵያ እንዳከሸፈች በመጥቀስ “ኔልሰን ማንዴላን ለአለም በማበርከት ከኢትዮጵያ በላይ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሀገር የለም” ብለዋል፡፡ 
በመቀጠል ገጣሚ ካሳሁን ገ/ሚካኤል የማዲባን ተምሳሌትነት የሚያሳይ ግጥም አቅርቧል፡፡ ስለጉዳይ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁትና ስማቸውን የደበቁ የዞኑ ከፍተኛ
የግብርና ባለሙያ የገበሬዎቹ ቅሬታ ትክክል መሆኑን አምነው “መንግስት የተጋነነ ትርፍ በሚያስገኝ የግብርና ግብአት ሽያጭ ንግድ ውስጥ መሰማራቱ ከገበሬው ጋር አቃሮታል፡፡” ብለዋል፡፡ 
አክለውም “ዘንድሮ የቡና አብቃይ በሆኑት ሀርጡሜ ሌሳ እና ቀርጫ አካባቢዎች ጭምር በጥቅምት ለተዘራውና በመጪው ሚያዝያ ለሚዘራው አዝመራ በግዳጅ
የተሰራጨውን ማዳበሪያ ህዝቡ ላለመውሰድ መወሰኑ አለመግባባት ፈጥሯል፡፡” በማለት አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም የግብርና ኤክስቴንሽን ለሙያዎች እየሰጡት ያለውን
አገልግሎት ከኢህአደተግ የተበረከተ ተደርጎ ለአርሶአደሮች ስለሚነገር የማይበቅል ምርጥ ዘር በመሰራጨቱ አርሶአደሮቹ “ኢህአዴግ ነው ያከሰረን” በማለት ከአካባቢው
ባለስልጣናት ጋር መግባባት በመታሰቢያ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሀሪ የማዲባን ተምሳሌታዊ የትግል ቁርጠኝነት አበክረው ተናግረዋል፡
፡ አክለውም የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲለወጥ የተበታተነው ትግል መሰባሰብ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡የአንድነት ፓርቲ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ አያሌው
ማዲባ ለ27 ዓመታት ታስሮበት የነበረውን የሮበን አይላንድ በጎነኘበት ወቅት የታዘበውንና ታሪካዊ ናቸው ያላቸውን የማንዴላን ንግግሮች በመርሀግብሩ ታዳሚዎች አቅርቧል፡፡
በማስከተልም ለኔልሰን ማንዴላ የህሊና ፀሎት ከተደረገ በኋላ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የተመራ የጧፍ ማብራት እንዳልቻሉና ይህም በአካባቢው ውጥረት እንደፈጠረ አስረድተዋል፡፡
የአካባቢው ባለስልጣናት በህዝብ እየተፈጠረባቸው ያለው ጫና ተጠናክሮ በኢህአዴግ አባላት መካከልም አለመግባባት የተፈጠረ ሲሆን በቅርቡ በተደረገው
የ2005 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2006ዓ.ም እቅ ላይ ሊመክሩ የተሰበሰቡት የገዢው ፓርቲ አባላትና ሹማምንት መግባባት ሳይችሉ እርስበእርስ
ተወነጃጅለው ስብሰባው ተበትኗል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በየገጠር ቀበሌው ያሰማራቸውን የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለፖለቲካ ስራ እና የገበሬውን አቅም
ያላገናዘበ የግብርና ግብአት በግዳጅ ለማሰራጨት እየተጠቀመባቸው ነው የሚሉ ስሞታዎች በየጊዜው እንደሚደመጡ ይታወቃል፡
ፍኖተ ነፃነት

No comments:

Post a Comment