Monday, December 16, 2013

ወደ ቁጫ የሄዱ የአንድነት አመራሮች ለሰዓታት ታገቱ

አንድነት ፓርቲ በደቡብ ክልል በቁጫ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት ስላሳሰበው በአካባቢው ያለውን
ሁኔታ የሚገመግም ቡድን መላኩንና የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በቁጫ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ አቋም ሊይዝ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ባካለፈው ሳምንት ዕረቡ ታህሳስ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ የገመገመው ከአንድነት ፓርቲ
የህግና ሰብአዊመብት ቋሚ ኮሚቴ፣ከፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤትና ከአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን የተውጣጡ አመራሮች
የተካተቱበት ቡድን ነው፡፡ የቡድኑ መሪና የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ጸሀፊ አቶ የአንድነት አባላት ስራ መስራት
እንዳይችሉና ከማህበራዊራ ተሳትፎም እንዲገለሉ የአካባቢው ባለስልጣናት በተቀነባበረ መንገድ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ “ተቃዋሚዎች አሸባሪ ናቸው”
በማለት ኮንትርት የተወሰዱ ስራዎችን እንዲመለሱ እያስደረጉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ቤተሰቦቻቸውን ጭምር
በማስፈራራትና ጥቃት በማድረስ ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስርዓት አልበኝነቱ በመባባሱ ህዳር 28 ቀን 2006 ዓ.ም
ከሌሊቱ በ7 ሰዓት ላይ በጎሮ ወረዳ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ሳተናው ኤሮ ቤት ላይ የሩምታ
ተኩስ ተከፍቶባቸዋል፡፡ የተኩሱን ምክንያት ለማጣራት የተደረገው ሙከራም በአካባቢው ባለስልጣናት ክልከላ እንዳይጣራ የደረገሲሆን
በቤታቸው ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው አቶ ሳተና ኢሮ ከማግስቱ ጀምሮ ትግስቱ አወሉ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በተለያዩ የመገናኛ
ብዙሃን ስለ ቁጫ የሚገለፀው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እውነት መሆኑን ቡድናቸው ታዝቧል፡፡ቡድኑ የአካባቢውን ህብረተሰብ
ተወካዮች በማነጋገር እና የእስር ሁኔታውን በመታዘብ በቁጫ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን መገንዘቡንም አቶ ትዕግስቱ ጨምረው
ገልፀዋል፡፡ የአካባቢውን የመንግስት ባለስልጣናት ቡድኑ ለማነጋገር በመሞከራቸው ለሰዓታት እንዲታገቱ ተደርጓል፡፡ ለቡድኑ አባላት
የታገቱበትን ምክንያት የተናገሩት ባለስልጣናት “ያለፍቃድ ወደ ቁጫ መጥታችኋል፤የታሰሩትንም ጎብኝታችኋል፡፡” የሚል አስገራሚ
ምላሽ ያገኙት የቡድኑ አባላት፣ በአካባቢው የተመለከቱትን ዝርዝር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እስካሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም፡፡
ይህ ድርጊት እየከፋ በመምጣቱም የአንድነት አባላት አካባቢውን ለቀው እንዲሰደዱ እያደረገ ሲሆን የወረዳው የአንድነት ለዴሞክራሲና
ለፍትህ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ግርጃ ለደህንነታቸው አስጊ የሆነ አጋጣሚ በመፈጠሩ ምክንያት ከወረዳቸው 85 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው
ክብረ መንግስት ገልፀዋል፡፡በዞኑ በሚገኙት ዴሮ ክብረ መንግስት ሻኪሶ የአንድነት አስተባባሪዎች ላይ ማሳደድ ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም
አሁን ግን ጥቃቱ እየጠነከረ መምጣቱን በአካባቢው ያሉ የፓርቲው አስተባባሪዎች ገልፀዋል፡፡በመረጃው ላይ የአካባቢውን ፖሊስ
ምላሽ ለማግኘት በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡ በዝርዝር የሚያስረዳ ሪፖርት
እንደሚያወጡ ተናግረዋል፡፡ በቁጫ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንድነትን እንዳሳሰበው የተናገሩት
የብሔራዊ ምክር ቤቱ ጸሀፊ አቶ ትግስቱ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ወደ ቁጫ የተጓዘው ቡድን ባመጣው ሪፖርት ላይ
በመበርኮዝ ውይይት አድርጎ አቋም እንደሚይዝም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ለወራት የቀጠለውና የማንነት ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት
ጥያቄዎችን ያነገበውን የቁጫ ህዝብ ጥያቄ ለመደፍጠጥ መንግስት የሀይል እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝና በሺ የሚቆጠሩ
የአካባቢው ተወላጆች ለድብደባና ለእስር መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡
fnotenetsanet

No comments:

Post a Comment