Wednesday, December 4, 2013

የእሳት አደጋ በትግራይ በመቀሌ ......

ከአዲስ ኣበባ በስተሰሜን 780 ኪ ሜ ላይ የምትገኘው መቀሌ ከ300 000 በላይ ህዝብ ሲኖራት ካለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ወዲህ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ዋና የኢንዱስትሪ ማዕከልም ናት።

 ትላንት እና ዛሬ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከፍተኛ ንብረት መውደሙ ተሰማ። 


የኣይን እማኞች እንደሚሉት ትላንትና ለሊት በከተማይቱ ቀበሌ 06 የኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ በሚታወቅ ስፍራ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ 70 ያህል የማምረቻ ተቐማት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

ዛሬ ማለዳም እዚያው መቀሌ ውስጥ አዲቀይ በተባለ የገበያ ስፍራ በተመሳሳይ ሁኔታ በተነሳ የእሳት አደጋ በርካታ የንግድ ቤቶች መውደማቸውን የከተማይቱ ማ/ቤት ኣስታውቐል።
የአደጋው መንስኤ ገና በውል ባይገለጽም የማዘጋጃ ቤቱ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎች ግን ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ኣለመሰማራታቸው ታውቐል።

የመጀመሪያው አደጋ የደረሰው ከትላንት በስተያ ሰኞ ለሊት ለማክሰኞ ኣጥቢያ ነበር፣ በመቀሌ ከተማ 06 ቀበሌ የኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ በሚታወቅ ልዩ ስፍራ። በአደጋውም የኣይን እማኞች እንደሚሉት 70 ያህል የተለያዩ የማምረቻ ተቐማት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የጉዳቱም መጠን ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ተገምቷል። 
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የመቀlሌ ከተማ ማ/ቤት የእሳት አደጋ መቆጣጠርያ ተሽከርካሪዎች ወደስፍራው ኣለመንቀሳቀሳቸው ታውቐል። ምክኒያቱ ደግሞ ሁለቱም የማዘጋጃ ቤቱ የእሳት ኣደጋ ተሽከርካሪዎች ተበላሽተው ጋራዥ ገብቷል የሚል ነበር። 
በእርግጥ የአየር መንገድ የእሳት ማጥፍያ መኪና በመጨረሻው ሳዓት መድረሱ ታውቐል። የሲሚንቶ ፋብሪካው ግን ዘግይቶም ቢሆን መምጣቱ ባይቀርም በቂ ውኃ ሳይዝ በመምጣቱ ባይመጣ ይሻል ነበር ነው የተባለው። 
የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የነበረው አሮጌ የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር በመፈንዳቱ ነው የሚሉት የመቀሌ ኗሪ አቶ አብረኃ ደስታ ቃጠሎውን በፎተግራፍ ለማንንሳት የሞከሩ ሰዎች በፖሊስ መከልከላቸውን ነግረውናል።
esat 2
esat

የመቀሌ ከተማ ማ/ቤት ስራ ኣስኪያጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ተገኝ ደግሞ የደረሱት የእሳት አደጋዎች 3 ሳይሆኑ ሁለት ናቸው ይላሉ።
 መስፍን ኢንጂነሪንግን ጨምሮ መሶብ ሲሚንቶ እና ሌሎች በርካታ ፋብሪካዎችም ይገኙባታል። ዘመናዊው የዓሉላ አባነጋ ኣውሮፕላን ማረፊያና ትልቁ የመቀሌ ዩኒቨርስቲም ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።
Source-www.dw.de.com

No comments:

Post a Comment