Sunday, December 8, 2013

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ግቢውስጥ ከብዙ ዓመታት በፊት ሰጥቷቸው የነበረው መስገጃ ቦታተነጠቁ፡

 


1486833_571026969645055_481474716_n   መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 4 ግቢዎች አሉት፤ ከአራቱ ግቢዎች አሪ ግቢ እየተባለ በሚጠራው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ የነበረው ጀማዓ የግቢው ማኔጅመንት ክፍል በዩኒቨርሲቲው ግቢውስጥ ከብዙ ዓመታት በፊት ሰጥቷቸው የነበረው መስገጃ ቦታተነጠቁ፡፡ በ15/02/2006 ዓ.ል ጁማዓ ቀን የግቢው ሙስሊም ተማሪዎች ለመስገድ እየተሰባሰቡ ባለበት ሰዓት በግቢው ማኔጅመንት ትዕዛዝ መሰረት ግቢው ውስጥ ማንኛውም የአምልኮ ሥርዓትን የሚከለክል ማስታወቂያ ተለጠፈ፤ ነገር ግን ተማሪው ተሰባስቦ ለመስገድ ሲዘጋጅ የግቢው ዘቦች ተማሪውን ለመበተን ጥረት ማድረግ ጀመሩ፤ ነገር ግን የተማሪው ብዛት በመጨመሩ መበተን ስለተሳናቸው ድርድርና ውይይት ማድረግ ተጀመረ፤ ነገር ግን ያቀረቡት ምክንያት አጥጋቢ አልነበረም፤ ያቀረቡትም ሃሳብ “መኪና እናዘጋጅላችሁና ከተማ ሰግዳችሁ ኑ” የሚል ነበር፡፡ ይሄ ሃሳብ በተማሪው ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ተማሪው በመሰባሰብ የዩኒቨርሲቲው የምረቃ አዳራሽ አካባቢ ባለው ሜዳ ላይ ተሰብስበው ሰገዱ፡፡ ከዛም ተማሪው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ስለጠየቁ“ ውይይት እናደርጋለን” ተብለው ተበተኑ፡ጥያቄው ሳይመለስ ቀጣይ ጁማዓ ደረሰ፤ 22/02/2006 ዓ.ል. የካምፓሱ ዘቦችም
በጧት ማንም ሰው ለመሰባሰብ እንዳይችል ዝግጅት ማድረ ጀመሩ፤ ባለፈው የተለጠፈውም አምልኮን የሚከለክለማስታወቂያ እንደገና በዚህኛውም ጁማዓ ተለጠፈ፡፡ተማሪውም ነገሮች እንዳይካረሩ በማለት ከግቢው ውጭ በሚገኘው ዓይናለም መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው ቦታ ላይ ሰገዱ፤ ያም ቢሆን ግን ጥያቄያቸውን ከማቅረብ አልተቆጠቡም ነበር፤ቢሆንም ግን ጥያቄያቸው መልስ ሳያገኝ ሶስተኛው ጁማዓ ደረሰ፤ 29/02/2006 ተማሪዎቹ ከዚህ በፊት በነበረው ጁማዓ እንዳደረጉት በአሁኑም ጁማዓ ከካምፓስ ውጭ ዓይናለም መናፈሻ ጀርባ ሰገዱ፤ አሁንም ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ አራተኛው ጁማዓ መጣ 6/03/2006፤ እናም የግቢው ተማሪዎች በአራተኛው ሳምንት እንደተለመደው ሶላታቸውን ዓይናለም መናፈሻ ጀርባ ከሰገዱና ሶላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ
በቅርቡ የባነኑ ግን ምንም የማያውቁ 3 የአህባሽ አስተሳሰብ አራማጅ ተማሪዎች ፖሊስ ይዘው ተማሪዎቹ የሰገዱበት ቦታ ድረስ ይዘው መጥተው ተማሪውን በግልጽ ቋንቋ “አሸባሪዎች ናቸው ከዚህ በኋላ እዚህ እንዳይሰግዱ” በማለት ፖሊሶቹ ባሉበት ዝተው ሄዱ፡፡ 
የነዚህ የአህባሽ አስተሳሰብ አራማጅ ተማሪዎች ስም፡-
1. አህመድ 4ኛ ዓመት መካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ
ሲሆን የኮምቦልቻ ልጅ ነው
2. አወል 1ኛ ዓመት ስፖርት
ሳይንስ ተማሪ ሲሆን የባህርዳር ልጅ ነው
3. አቡበከር 3ኛ ዓመት ሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ሲሆን የመቀሌ ልጅ ነው፡፡
ጥያቄያቸው ምንም መልስ ሳያገኝ አምስተኛው ጁማዓ መጣ፤ 13/03/2006 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንደለመዱት ዓይናለም መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው ቦታ ላይ ለመስገድ ሲሄዱ ቦታውን ቀድሞ ፖሊስ ስለያዘው ተማሪዎቹ የነበራቸው አማራጭ ወደ ከተማ ሄዶ 17 ተብሎ በሚታወቀው መስጅድመስገድ ነበር፤ እናም መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር ጁማዓ አምልጧቸው ነበር መስጅድ የደረሱት፤ እናም ተሰባስበው ዝሁርን ሰግደው ተመለሱ፤ የተማሪው ስሜት በጣም ያሳዝን ነበር፤ በዚህ ሳያበቁ ደግሞ ሲመለሱ ተከራይተውት የነበረውን መስገጃ ቤታቸውን ማለትም ዳረል አርቀም ዘግተው ጠበቋቸው፤ እናም ተማሪዎቹ ካሁን አሁን ይከፈታል ብለው ተስፋ አድርገው ቢጠብቁም ነገሩ እንዳሰቡት አልሆነም፤ እናም ከሶስት ቀን በኋላ መስገጃ ቤታቸውን ጨምሮ በዚያ አካባቢ ያሉ ካፌዎችና ሬስቶራንቶችን ጨምሮ ብዙ ቤቶች መሬቱ በመንግስተ ስለተፈለገ በሚል አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት እንዲፈርሱ ተደረገ፡፡ ከዚህ ሁሉ በጣም የሚያሳዝነው የመቀሌዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ክንዳይ በቦታው ሲያልፉ ፊታቸው ላይ የደስታ ስሜት በማሳየት መፈንደቃቸው ነው፡፡ ከዛ ቀጥሎ
ባሉት ሁለት ተከታታይ ጁማዓዎች ተማሪው ከግቢው በጣም ርቆ ከሚገኘው መስጅድ ታክሲ ኮንትራት እየያዙ በመሄድ እየሰገዱ ይገኛል፡፡ እናም ተማሪዎቹ በገንዘብ ወጪም ሆነ በጊዜ ከፍተኛ የሆነ ብክነት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ እስካሁንም መስገጃ ቦታ ይሰጠን የሚለው የተማሪው ጥያቄ አልተመለሰም፡፡ ከዚህ በኋላ ተማሪው የደረሰበትን ነገር እየተከታተልን እናሳውቃለን ኢንሻአላህ፤ በዱዓ አትርሷቸው!===============================
በተማሪዎች ዙሪያ ያለውን ማንኛውንም ጉዳይ ለመከታተል ፔጃችንን LIKE , SHARE, ይበሉ>>>
https://www.facebook.com/EthiopianMuslimUniversityStudentsEmus for more information follow us on >>>>>>

No comments:

Post a Comment