Monday, December 9, 2013

ወያኔ/ህወአት/ኢህአዴግ የትልቅን ሰው ሞት የመጨረሻ ዜና ? የሌላው ሀገር እውነተኛ ዘገባና ሀዘን!?


በለው!
*ድንቄም!የዘር መድሎ ትግል! ህወአት/ኢህአዴግ ግን የዘር መድልዎ አፓርታይድ ማፈናቀልን የሜንጫ መጨፋጨፍን ታስፋፋላችሁ። ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግና ሆድዳር አድርባይ ምሁር እምዬ ምንይልክ አይታወስ ብላችሁ ለምን ለማንዴላ ተቆላችሁ? አስመሳይ! ማንዴላ ኢትዮጵያን ለማየት የመረጠው ለመልስና ለኅይለማርያም አደለም!ለትግል አጋሩ ለኮ/መንግስቱ ኅ/ማርያምና ለእውነተኞች ኢትዮጵያን ነው። ነጭን ድል የነሳው የጥቁር ህዝብ ኩራት፣ አንበሳው ትውልድ በእቴጌ ጣይቱ ተመክሮ በእምዬ ምንይልክ ጥሪ ክርስቲያን ሙስሊሙ በማርያም ተምሎ የጊዮርጊስ ታቦትን አስቀድሞ ብሔር ቋንቋ ሳይል አድዋ ላይ ነው ድል በኅብረት ተሠራው!።
*የህወአትሻቢያ ቤተሰቦችማ ከኋላ አሻጥር ሲሰሩ፣ ሲገድሉ ሚስጠር ለጠላት ሲያቀብሉ፣ንብረት ሲያወድሙ፣የወታደር ስንቅ በመርዝ ሲበክሉ፣ ለጠላት ቤተሰብ እንቁላል አቅራቢ ሹምባሽ ነበሩ። እናንተም የባንዳ ልጅ የልጅ ልጆች በኤርትራም በሱማሊያም ጦርነት ተበቀላችሁን ‘የዘሬን ብተው ይዘርዝረኝ አላችሁ!” እናንተም በዛን ዘመን ድልድይ አፍራሽ፣ ተገንጣይ፣ ወንበዴ ነበራችሁ፤በስምምነት ፸ሺህ በላይ ድሃ ልጅ ፈጃችሁ አስፈጃችሁ። ዛሬ ተገልብጣችሁ”በልማታዊ መንግስት”ሥም ሀገር ቆራረሳችሁ ትውልድ አፈናቅላችሁ አሰደዳችሁ ለባዕድ ሸጣችሁ።
*ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ…ሠላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ዕርቅ አንድነትና በጋራ እድገት የሚባል ነገር ሁሉ ጠላቱ ነው። ሽብር፣ አመጽ፣ ደልድይ ማፍረስ፣ ንብረት ማውደም፣ ማሠር፣ መደብደብ፣ መግደል፣ ቢሆን አንደኛ ነው። በዓለም የኒልሰን ማንዴላ ህልፈተ ሕይወት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ዘር ቀለቀም ሳይለይ ሰበር ዜና! አሳዛኝ ዜና!ትልቅ ሀዘን! ታላቅ ሰው ኣለም አጣች! ሲባልና ሲዘገብ የወሮበላ ሀገር…የጋጠ ወጥ ሥርዓት ውሸት ከሞላው ዜና “በመጨረሻም!” ብሎ የክቡር ሰው ሞት ይዘግባል። ለምን? ክብር አያቁማ! ሀገር የለማ! ምሁር የለም! ታጋይ ምሁር ጠበብት እኛው የሞቱ ጠ/ሚኒስትር ብቻ ናቸው። በባንዲራ ጠቅልለው ጥለው ታጋይ አይሞትም!! ብለው በፋውንዴሽን እያሳበቡ የውጭ ምንዛሪ እያቀባበሉ ንግድ አጣጡፈዋል “ቁጥር ሁለት ፋውንዴሽንም “ሀበሻ ፋውንዴሽን” የራዕይ ፋውንዴሽን፡ እያሉ በድሃ ሀገርና ሕዝብ ላይ ያሾፋሉ።
*ታላቁ መሪ መሌ ዜናዊ ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት በቀን አበል ተለቀሰለት፣ ኪራይ ስብሳቢ፣ ሙሰኛ፣አድርባይ በስሙ ከበረበት በዚያች ፵፻፪፻ብር የወር ገቢ ተቆራፍዶ ከኮብል አስቶን አንጣፊ ደሞዝ በታች ተቀጥሮ የሀብታም ልጅነቱን ጥሎ ድሃ ልሁን ብሎ በረሃ ገባ !? ለዓለም ምሳሌ የሆነ፣ እየተራበ ፫ነጥብ፫ ቢሊየን ዶላር መቆጠብ የቻለ ታጋይ! አትራፊ መሪ ! “በአባታችን ይጠራል እንጂ ምንም አያገናኘንም የሚሉት እህታቸው ጠላ ሻጭ ወንድማቸው ጢቢኛ ይሸጣል! ምድረ አድርባይ፣ ሆድአደር፣ የጎጠኛ፣ የዘረኛ፣ በኅብረት ሀገር አጥፊ፣ትውልድ አምካኝ፣ ባንዳ ሁሉ ባነር እየወጠረ በጸይ መነጽር ተሸፍኖ ፎቶግራፍ ተሸክሞ እየዞረ በሰውዬው ሥም ይነግዳል። ሌባ በለው! ለራሱ መሪ ክብር የሌለው፣ለራሱ ታሪክና ሉዓላዊነት ለዜጋው የማይቆሮቀር ለሰው ሀገር ጅግና ጭራ መቁላትም የሰውን ክብር ማሳነስም በጣም አሳፋሪ ነው። *ሠርታችሁ ዓላማን ተግብሩ! ቀብሮ ከማልቀስ ኖሮ ማስደሰት!”
* የአፋር ግመል የሚያውቀውን የሀገር ዳርድንበር፣ ሉዓላዊነት፤ ኅብረሔርና ሰንደቅ የጠፋችሁና ያጠፋችሁ አውርቶ አደሮች ሆይ፣! ብሔሮቻችሁን አታሰድቡ! መልካም ሥም ከመቃብር በላይ ነው” ሲባል ሠምታችሁ በዘጠኙም ክልል መለስን ቀብራችሁ ‘ታጋይ አይሞትም!’ እያላችሁ ታናፋላችሁ? ወይ ጥጋብ! ነፍሳችሁ አይማር!!
source: freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment