Sunday, December 15, 2013

ልደቱ አያሌው እና አዲሱ የወያኔ ስትራቴጂ



ልደቱ አያሌው በመጪው ምርጫ ካለምንም ቅድመሁኔታ በከፍተኛ ድምጽ ያሸንፋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- የ1997 ምርጫን በቅንጅት ማሸነፍ ተከትሎ ከፍተኛ የፖለቲካ ክህደት የፈጸመው የኢዴፓው አቶ ልደቱ አያሌው ከፖለቲካው ባይወጣም እንደገና ወደ ፖለቲካ ተመለሰ በሚል ባረኮት እና ውዳሴ መንግስታዊ በጀት የሚያገኘው አዲስ አድማስ ሰፋ አድርጎት የመጀመሪያውን የፖለቲካ ሰንበቴውን አሳይቶናል:: ነገ ደሞ ሪፖርተር እና የወያኔ አፈቀላጤዎች አሟሙቀው ከምርጫ በፊት የልደቱን ስም ለማግዘፍ የተሸረበውን ፕሮፓጋንዳ ሊግቱን ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል::

የህዝብ ድምጽ በይፋ እንዲዘረፍ አብረው በቅንጅት ውስጥ የነበሩ ታጋዮች ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ በቅጥረኝነት ከፍተኛውን ሚና የተጫወተውና በየወሩ ከደህንነት ሹሞች ደምወዙን ይቀበል የነበረው ልደቱ አያሌው አሁንም ወያኔ ኢሕኣዴግ አርቅቆ በሰጠው አዲስ የሶስተኛ አማራጭ ስትራቴጂ ተቃዋሚዎችን እና ህዝብን ለማታለል በማድባት በመጪው ምርጫ ሃገራዊ ሃሳቦች ላይ መርዞችን ለመርጨት መሽጎ ዲስኩሩን ጀምሯል::

ከአና ጎሜዝ መምጣት በፊት የአውሮፓ ህብረት ተቃዋሚዎችን እንደሚያናግሩ መረጃ የነበረው ወያኔ ኢዴፓ ሊወክላቸው የሚችሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዳሉት እየታወቅ በደህንነት ሹሙ አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ትእዛዝ ልደቱ አያሌው በቦታው እንዲገኝ የተደረገው በ97 ምርጫ ወቅት ተከስቶ የነበረውን ጡዘት ለአና ጎሜዝ በፖለቲካዊ ቋንቋ ለመተንፈስ ታስቦ የታቀደ እንደሆን ታውቋል::ይህንን ተከትሎ ከአዲሱ አለቃው ከአቶ ኢሳያስ ጋር በሳምንት ሁለት ጊዜ እየተገናኘ አስፈላጊውን ውይይት የሚያደርገው ልደቱ ስሙን አግዝፎ ለማውጣት በተግባር ሊሰሩ ይችላሉ የተባሉ ሚዲያዎች ሁሉ አስፈላጊውን እንዲደረግላቸው በፍጥነት እየተሰራ መሆኑ ታውቋል:;

ሶስተኛ አማራጭ ብሎ በኢዴፓ ስም የወያነውን ስታራቴጂ ይዞ ብቅ ያለው ልደቱ አያሌው የተቃዋሚ ሃይሎችን በማዳከም ህዝቡን ለማጭበርበር የታቀደውን ሴራ እያንዳንዳችን ልንገነዘበው ይገባል:: ዛሬም በጥቅማ ጥቅም ተገዝቶ እንደከዚህ ቀደሞ ምርጫውን ተገን አድርጎ በህዝብ ድምጽ ለመነገድ የታቀደ ሴራ ሊሰራ እንደማይችል ልንነግረው ይገባል:: ልደቱ አያሌው ዛሬም ማንዴላ እንዲባል የወያኔ ካድሬዎች እንደከዚህ ቀደሙ ያለ ታሪክ ለመድገም ሰልጥነው ዝግጅታቸውን በማደርግ ላይ ሲሆኑ ልደቱ በሚወዳደርበት የምርጫ ጣቢያም በከፍተኛ ድምጽ እንደሚያሸንፍ ምንጮቹ ይጠቁማሉ:: ገና በወያኔ የደህንነት ቢሮ የሚወዳደርበት አከባቢ ያልተወሰነለት ልደቱ ከባለፈው በተሻለ ደምወዝ በታማኝ ተቃዋሚነት ወያኔን እያገለገለ እንደሚገኝ ሲታወቅ ተቃዋሚዎች እንዲዳከሙ ከኢዴፓ ውስጥ ያሉ የወያኔ የደህንነት መዋቅር አባሎችን ወደ አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በማስገባት ከወያኔ ጋር በጋራ እያሰለለ መሆኑ ታውቋል::

ልማታዊው ተቃዋሚ ኢዴፓ እያንዳንዳቸው አመራሮች ከወያኔ ከሚከፈላቸው ደምወዝ የሚሰሩ እና ከዚህ ቀደም በደህንነት መዋቅር ውስጥ በመንግስት ባለስልጣንነት- ከባለስልጣናት ጋር በጥቅም ትሥሥር እና የንግድ ሽርክና የተዋሃዱ እና ላለው የፖለቲካ ስርኣት ተገዢ እና አጎብዳጅ የሆኑ ታማኝ ተቃዋሚነትን ይዘው የሚሰሩ አመስጋኝ ተለጣፊዎች ናቸው::ኢሓዴግ ያለበትን ድክመት በራሱ ማንጸባረቅ እና መናገር ስለማይፈልግ እንዲሁም ጠንካራ ተቃዋሚዎች ቢናገሩት እፍረት እና ውርደቱ ስለሚወጣ በለዘበ መልኩ ኢዴፓን እየተጠቀመ መሆኑ እሙን ነው::

No comments:

Post a Comment