Sunday, December 8, 2013

በመነጣጠሉ ተጠቃሚው ማን ይሆን? ተጎጂውስ? ??ሀገራዊና ክልላዊ ብሔርተኝነት ተጻራሪ የዕድገት አቅጣጫዎች ናቸው ,ኢትዮጵያ ነገስታት በጊዜ ሂደት ክልላዊ ብሔርተኝነትን እያሳነሱ ሀገራዊ ብሔርተኝነትን አዳብረዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የተጠቀሙበት ዋና ዘዴ ከንጉሳዊ ቤተሰቦች ጀምሮ ብሔረሰቦች እርስ በርሳቸው ተጋብተው እንዲዋለዱ ማድረግ ነበር፡፡ ሌላው አቢይ ዘዴ የውስጥ አስተዳደራዊ አካባቢዎች በተቻለ መጠን በብሔረሰብ ስያሜ እንዳይጠሩ ማድረግ ነው፡፡ በተለይ የሁለቱ ታላላቅ ብሔረሰቦች አካባቢዎች ከዚህ ዓይነት ስያሜ የፀዱ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡

የቅርቡን ታሪክ እንኳን ብንወስድ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌም ናቸው፡፡ በአባታቸው በኩል የዘር ግንዳቸው ተፈሪ መኮንን ወ/ሚካኤል ጉዲሳ እያለ የሚቀጥል ሲሆን፣ በሸዋ ክፍለ ሀገር አማራ እና ኦሮሞ እስከ ሰማኒያ በመቶ ያህሉ እርስ በርስ ተጋብተው ተዋልደዋል፡፡ ኦሮሞዎችና አማራዎች በብዛት የሚገኙባቸው አካባቢዎች ወለጋ፣ አርሲ፣ ሐረርጌ ወዘተ እየተባሉ ይጠሩ ነበር እንጂ፣ እንደ አሁኑ ተጠቃልለው ‹‹ኦሮሚያ›› አይባሉም ነበር፡፡ በተመሳሳይ፣ አማራዎች በብዛት የሰፈሩባቸው አካባቢዎች ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ወዘተ ተብለው ተሰይመው ነበር፡፡ አሁን ግን ተጠቃልለው ‹‹አማራ ክልል›› ተብለዋል፡፡ ከአንዱ ክፍለ ሀገር ወደ ሌላኛው ያለ አንዳች ገደብ መዘዋወር ይቻል ነበር፡፡ የአፄዎቹ ዋና ዓላማ ብሔርተኝነትን ወደ ኢትዮጵያዊነት መቀየር ነበር፡፡

ያሁኖቹስ አካሄድ ግን የዚህ ተጻራሪ ነው፡፡ በረጅም ዓመታት አፄዎቹ የገነቡትን ኢትዮጵያዊነት ወደ ትናንሽ ክልላዊ ብሔርተኝነት ለመሸንሸን ነው የሞከሩት፡፡ ኦሮሞዎች በብዛት የሰፈሩባቸውን አካባቢዎች በማጣመር ኦሮሚያ የሚባል ክልል ፈጠሩ፡፡ የክልሉ ሕዝብ በፈለገ ጊዜ የመገንጠል መብት ሰጡት! ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በኢትዮጵያ በዜግነታቸው እኩልነታቸው ከተከበረ የተለየ ልዩነት ለምን አስፈለገ ? ለምሳሌ አንድ ኦሮሞ በየትኛውም ክልል በሚገኝ መሬት ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ የባለቤትነት መብት አለው፡፡ በዚህ መሰረት ቢፈልግ ወለጋ፣ ቢፈልግ ደግሞ ጎንደር ሄዶ ለእርሻ የሚሆን መሬትና የመኖሪያ ቤት ለመስራት የሚያስፈልገውን ቦታ ጠይቆ የማግኘት መብት አለው፡፡ ቋንቋን በተመለከተ ቢፈልግ በኦሮምኛ፣ ቢፈልግ ደግሞ በአማርኛ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር መግባባት ይችላል፡፡ ብሔረሰቡ አማራ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኦሮምኛ መናገርና መጻፍ ቢችል የበለጠ ኢትዮጵያዊ ይሆናል እንጂ ምን ጉዳት ይኖረዋል? ኦሮሞኛ ቋንቋ በሀገር ደረጃ ቢዳብር ለአማርኛ ቋንቋ መዳበር አስተዋጽኦ ያደርጋል እንጂ ምን ዓይነት ጉዳት ያስከትላል?

ያሁኖቹስ ግን አንድ ኦሮሞ መናገርና መጻፍ ያለበት ኦሮምኛ ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት ኦሮሞዎች ከአማሮች ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዲቋረጥና በጠላትነት የጎሪጥ እንዲተያዩ የታለመ ይመስላል፡፡ በጋብቻም በቋንቋም ከተለያዩ ኢትዮጵያዊነታቸው ያበቃለታል! ኢትዮጵያዊነታቸው ከተበጠሰ ደግሞ ለየብቻቸው ሀገሮች (ኦሮሚያ እና አማራ) መስርተው፣ እንደ ኤርትራ ነጻ ሀገር በመሆን ከተባበሩት መንግስታት እውቅና ይጠይቃሉ፡፡ እቅዱ ይህን ይመስላል፡፡ በመነጣጠሉ ተጠቃሚው ማን ይሆን? ተጎጂውስ? ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡ ያሁኖቹስ አካሄድ ይህን የመጨረሻ ውጤት እንደሚያስከትል ጥርጥር የለውም፡፡

ያሁኖቹስ የሚያራምዱትን ክልላዊ ብሔርተኝነት ለማጠናከር የብሔር ፌዴራሊዝምን መስርተዋል፡፡ እያንዳንዱ የብሔር ክልል የመገንጠል መብት አለው፤ ግን በተጨባጭ መገንጠል አይችልም፡፡ ምክንያቱም የብሔር ክልሎች ሕገ መንግሥቱ የሚሰጣቸው ሥልጣን የላቸውም፡፡ የብሔር ክልሎቹን ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯቸው የህወሓት ባለስልጣኖች ናቸው፡፡

ያሁኖቹስ ራሳቸው ባጻፉት ሕገመንግስት ውስጥ ለብሔር ክልሎች የተሰጠውን የመገንጠል መብት ለምን ከለከሏቸው ? አጭሩ መልስ፣ ለኤርትራ ከሌሎች የብሔር ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ እና ከደቡብ በቂ የሀብት መሠረት ለመገንባት ነው፡፡ በኤርትራዊነታቸው አቶ መለስ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብና ሀብት እንዲሸጋገር አድርገዋል፡፡
ታዲያ ለምን ይሆን??? እራሳችንን እንጠይቅ???
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment