Saturday, December 7, 2013

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በውሃ እጥረት እስረኞች እየተሰቃዩ መሆኑ ተገለፀ::




በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን ጨምሮ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 2500 የሚጠጉ ታሳሪዎች በውሃ እጥረት ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በማረሚያ ቤቱ በተፈጠረው የውሃ እጥረት ምክንያት ለምንም አይነት አገልግሎት የሚሆን ውሃ መጥፋቱ ተሰምቷል፡፤ ይህ የውሃ እጥረት የማረሚያ ቤቱን ጠባቂ ፖሊሶችን ሳይቀር ችግር ውስጥ እንደከተታቸው እየተገለጸ ነው፡፡

ይህንን ከባድ ችግር ለመፍታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እስካሁን ምንም እያደረገ አለመሆኑ ተገልፆል፡፡

ውሃ ለሰው ልጅ ለመኖር ወሳኝ ግብአት እንደሆነ እየታወቀ ከ2500 በላይ ታሳሪዎች ባሉበት ማረሚያ ቤት በውሃ እጥረት ምክንያት ታሳሪዎች በውሀ እጥረት እንዲሰቃዩ ማድረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት መሆኑ እየተገለጸ ነው::

ማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ከ 2500 በላይ እስረኞችን ሂወት ሊታደግ እንደሚገባ መልዕክታችን ነው፡፡

No comments:

Post a Comment