Monday, December 16, 2013

ኧረ!.......ወገን ወገን በየቦታው እየረገፈ ነው ,,,,,,,

ኧረ!...የወገን ያለህ!!!ኧረ…የሰሚ ያለህ…
በቤይሩት በሀይሉ በዱሼ የተባለ ኢትዮጵያዊ ተገደለ፤ ሬሳው ሆስፒታል ፍሪጅ ውስጥ ቀርቷል 
     በግሩም ተ/ሀይማኖት
  በየአረብ ሀገሩ መሰደዳችንና መርገፋችን በአሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ከሳዑዲ አረቢያ ባልተናነሰ ወገን የሚረግፍበት ሌላኛው ቦታ ቤይሩት ነው፡፡ ከወር በፊት በአንድ ወር ውስጥ በቤይሩት 7 እህቶቻችን በመኪና ተገጭተው ሶስቱ ሲሞቱ ሌሎቹ መትረፋቸው በተለያየ ወቅት ተዘግቧል፡፡ በዚህን ወቅት መሞቱም ሆነ ስለሱ እንዳይሰማ የተፈለገ አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ሞቶ ለሁለት ወር ነገሩ ተቀብሯል፡፡ እስካሁንም ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ተቀምጧል፡፡ 
     ወጣቱ ሀይሉ በዱሼ ታዬ ይባላል፡፡ ቤይሩት ሰርቶ ራሱን እንዲለውጥ የወንድሙ ሚስት ናት የወሰደችው፡፡ አሰሪዎቹ (ቀጣሪዎቹ) በትሩን እየተባለ በሚጠራው ቦታ አካባቢ ሲሆን የሚኖሩት ከቤይሩት ወጣ ብላ የምትገኝ ቱላ የሚባል ቦታ የዘይቱን እርሻ አላቸው እዛም እየወሰዱት ይሰራል፡፡ እዛ እርሻ ቦታ ነው ሞቶ የተገኘው፡፡ እንደገደሉት ነው የሚያስታውቀው እንጂ በብዙ ነገር ራሱን የሚገልበት ምክንያት የለውም፡፡ ደግሞም እዛ እርሻ ቦታው ላይ ወፍ የሚያባርሩበት ቡሽ ነገር የሚተኩስ መሳሪያ አለ፡፡ በእሱ ራሱን ነው ያጠፋው ይላሉ፡፡ ይህ ግን የማይመስል ነው፡፡ 
     አንድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ከመሆኑ ጋር ይህን ይሰራል ብሎ ማሰብ የሚከብድ ነው፡፡ ሁለተኛ ራሱን ለማጥፋት ብሎ መምታት የሚችልበት ቦታ አይደለም የተመታውም፡፡ በሀይሉ እንደተገደለ ያመጣችውን የወንድሙን ሚስት ሬሳውን እኛ እንልከዋለን አንቺ ቀድመሽ ሄደሽ ነገሮች አመቻቺ አይነት ነገር ብለው አሳፈሯት፡፡ አሁን ሁለት ወር ሊሞላው ነው ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ከገባ፡፡ ቆንስላው ምንም ሊረዳቸው አልቻለም፡፡  ሶስተኛ ወሩ ካለቀ ኢንሹራንስ እንኳን ማግኘት አይችልም፡፡ ሬሳውን ወደ ሀገር ማስገቢያም አይኖርም፡፡ ሌላ ኮኮቤ የምትባል የአክስቱ ልጅ አለች፡፡ ሁኔታውን ለማስተካከል ብትጥርም ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡ የቤይሩት ቆንስላ ጽ/ቤት ሬሳው ሀገር እንዲገባ ቤተሰቦቹም ማግኘት ያለባቸውን ኢንሹራንስ እንዲያገኙ ማድርግ አልቻለም፡፡ ቢሮው ዜጎች የሚጎዱበትን ነገር ነው ለማመቻቸት የመጣው መሰለኝ፡፡ ከበር ላይ እየወሰዱ ሲገድሉ ዝም ከማለት ጀምሮ ሊሎችም ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት እንኳን ቢይዘው ሊገቡበት አይፈልጉም፡፡ ታዲያ ስራቸው ምን ይሆን? የቦንድ መሰብሰብ? የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ ጉራጌ ልማት ማህበር፣…እያሉ በሞሙኒቲ ስም ገንዘብ መሰብሰብ በቃ!....??
     ቢይሩት መሀል ከተማ በመኪና ኢትዮጵያዊያንን የመድፋቱ ሁኔታ በሚገርም ሁኔታ በአንድ ወር 7 ደርሶ ነበር፡፡ ገነት ጌታቸው በሞተችበት ወቅት ነው ይህ ልጅም የተገደለው፡፡ ነገሩ ተድበስብሶ ተድበስብሶ ከዛሬ ነገ ሬሳው ሀገር ይላካል እየተባለ ቢጠበቅም አልሆነም፡፡ ሬሳው ሀገር እንዲገባ ወይም አፈር እንዲቀምስ እንኳን ቆንስላው ምንም አይነት ጥረትም ሆነ ድጋፍ ሊያደርግ አልቻለም፡፡ የገነትም ሬሳ እስከዛሬ ሀገር ሊገባ አለመቻሉን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አመንጭተውልኛል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት የውሽት ፕሮፖጋንዳውን በETV እንደተንከባከቧት፣ እንደረዷት እና ከአቅም በላይ ሆኖ እንደሞተች አድርገው አቅርበዋል፡፡ ሬሳውን እንኳን ሀገር እንዲገባ ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡ ለፖለቲካ ስብከት ብቻ የረዱ አስመስለው አቀረቡት ግን ዞር ብለው አላዩዋትም ሲሉ ጓደኞችዋ በምሬት ይናገራሉ፡፡ ከገነት በኋላ የተገጨችው አንደኛዋ ታክማ ሲሻላት ሁለት ድጋሚ ተገጭተው ሲሞቱ አሰሪዎቻችው ጥሩ ስለነበሩ ወዲያው ተሯሩጠው ሬሳቸው ወደ ሀገር ገብቷል፡፡ ሌሎች በዛው ወር ውስጥ በመኪና የተገደሉ ልጆች ሬሳም በቆንስላ ጽ/ቤት እንዝህላልነት ፍሪጅ ውስጥ ይገኛል ሲሉ ውስጥ አዋቂ የሆኑ ልጆች ነገሩን ገላልጠው አውግተውኛል፡፡   ኧረ!.......ወገን ወገን ላይ ጨከነ በየቦታው እየረገፈ ነው፡፡ ኧረ…!!!! ዝምታው ምንድን ነው????
ኧረ!...የወገን ያለህ!!!ኧረ…የሰሚ ያለህ… በቤይሩት በሀይሉ በዱሼ የተባለ ኢትዮጵያዊ ተገደለ፤ ሬሳው ሆስፒታል ፍሪጅ ውስጥ ቀርቷል በግሩም ተ/ሀይማኖት በየአረብ ሀገሩ መሰደዳችንና መርገፋችን በአሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ 
ከሳዑዲ አረቢያ ባልተናነሰ ወገን የሚረግፍበት ሌላኛው ቦታ ቤይሩት ነው፡፡
 ከወር በፊት በአንድ ወር ውስጥ በቤይሩት 7 እህቶቻችን በመኪና ተገጭተው ሶስቱ ሲሞቱ ሌሎቹ መትረፋቸው በተለያየ ወቅት ተዘግቧል፡፡
 በዚህን ወቅት መሞቱም ሆነ ስለሱ እንዳይሰማ የተፈለገ አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ሞቶ ለሁለት ወር ነገሩ ተቀብሯል፡፡ 
እስካሁንም ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ተቀምጧል፡፡ 
ወጣቱ ሀይሉ በዱሼ ታዬ ይባላል፡፡ ቤይሩት ሰርቶ ራሱን እንዲለውጥ የወንድሙ ሚስት ናት የወሰደችው፡፡ 
አሰሪዎቹ (ቀጣሪዎቹ) በትሩን እየተባለ በሚጠራው ቦታ አካባቢ ሲሆን የሚኖሩት ከቤይሩት ወጣ ብላ የምትገኝ ቱላ የሚባል ቦታ የዘይቱን እርሻ አላቸው እዛም እየወሰዱት ይሰራል፡፡ እዛ እርሻ ቦታ ነው ሞቶ የተገኘው፡፡
 እንደገደሉት ነው የሚያስታውቀው እንጂ በብዙ ነገር ራሱን የሚገልበት ምክንያት የለውም፡፡ ደግሞም እዛ እርሻ ቦታው ላይ ወፍ የሚያባርሩበት ቡሽ ነገር የሚተኩስ መሳሪያ አለ፡፡ በእሱ ራሱን ነው ያጠፋው ይላሉ፡፡ ይህ ግን የማይመስል ነው፡፡
 አንድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ከመሆኑ ጋር ይህን ይሰራል ብሎ ማሰብ የሚከብድ ነው፡፡ ሁለተኛ ራሱን ለማጥፋት ብሎ መምታት የሚችልበት ቦታ አይደለም የተመታውም፡፡ በሀይሉ እንደተገደለ ያመጣችውን የወንድሙን ሚስት ሬሳውን እኛ እንልከዋለን አንቺ ቀድመሽ ሄደሽ ነገሮች አመቻቺ አይነት ነገር ብለው አሳፈሯት፡፡ አሁን ሁለት ወር ሊሞላው ነው ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ከገባ፡፡ ቆንስላው ምንም ሊረዳቸው አልቻለም፡፡ ሶስተኛ ወሩ ካለቀ ኢንሹራንስ እንኳን ማግኘት አይችልም፡፡ ሬሳውን ወደ ሀገር ማስገቢያም አይኖርም፡፡
 ሌላ ኮኮቤ የምትባል የአክስቱ ልጅ አለች፡፡ ሁኔታውን ለማስተካከል ብትጥርም ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡ የቤይሩት ቆንስላ ጽ/ቤት ሬሳው ሀገር እንዲገባ ቤተሰቦቹም ማግኘት ያለባቸውን ኢንሹራንስ እንዲያገኙ ማድርግ አልቻለም፡፡ ቢሮው ዜጎች የሚጎዱበትን ነገር ነው ለማመቻቸት የመጣው መሰለኝ፡፡ ከበር ላይ እየወሰዱ ሲገድሉ ዝም ከማለት ጀምሮ ሊሎችም ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት እንኳን ቢይዘው ሊገቡበት አይፈልጉም፡፡ ታዲያ ስራቸው ምን ይሆን? የቦንድ መሰብሰብ? የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ ጉራጌ ልማት ማህበር፣…እያሉ በሞሙኒቲ ስም ገንዘብ መሰብሰብ በቃ!....?? 
ቢይሩት መሀል ከተማ በመኪና ኢትዮጵያዊያንን የመድፋቱ ሁኔታ በሚገርም ሁኔታ በአንድ ወር 7 ደርሶ ነበር፡፡ ገነት ጌታቸው በሞተችበት ወቅት ነው ይህ ልጅም የተገደለው፡፡ ነገሩ ተድበስብሶ ተድበስብሶ ከዛሬ ነገ ሬሳው ሀገር ይላካል እየተባለ ቢጠበቅም አልሆነም፡፡ ሬሳው ሀገር እንዲገባ ወይም አፈር እንዲቀምስ እንኳን ቆንስላው ምንም አይነት ጥረትም ሆነ ድጋፍ ሊያደርግ አልቻለም፡፡
 የገነትም ሬሳ እስከዛሬ ሀገር ሊገባ አለመቻሉን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አመንጭተውልኛል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት የውሽት ፕሮፖጋንዳውን በETV እንደተንከባከቧት፣ እንደረዷት እና ከአቅም በላይ ሆኖ እንደሞተች አድርገው አቅርበዋል፡፡ ሬሳውን እንኳን ሀገር እንዲገባ ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡ 
ለፖለቲካ ስብከት ብቻ የረዱ አስመስለው አቀረቡት ግን ዞር ብለው አላዩዋትም ሲሉ ጓደኞችዋ በምሬት ይናገራሉ፡፡ ከገነት በኋላ የተገጨችው አንደኛዋ ታክማ ሲሻላት ሁለት ድጋሚ ተገጭተው ሲሞቱ አሰሪዎቻችው ጥሩ ስለነበሩ ወዲያው ተሯሩጠው ሬሳቸው ወደ ሀገር ገብቷል፡፡ ሌሎች በዛው ወር ውስጥ በመኪና የተገደሉ ልጆች ሬሳም በቆንስላ ጽ/ቤት እንዝህላልነት ፍሪጅ ውስጥ ይገኛል ሲሉ ውስጥ አዋቂ የሆኑ ልጆች ነገሩን ገላልጠው አውግተውኛል፡፡ 
ኧረ!.......ወገን ወገን ላይ ጨከነ በየቦታው እየረገፈ ነው፡፡ 
ኧረ…!!!! ዝምታው ምንድን ነው????

No comments:

Post a Comment