Saturday, December 7, 2013

መንግስት ለቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ



ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል።

የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን ፎርም እንዲሞሉ እያደረጉዋቸው መሆኑን አንዳንድ ወታደሮች ለኢሳት ገልጸዋል።

መንግስት በአሁኑ ጊዜ ይህን እርምጃ ለምን ለመውሰድ እንደፈለገ አልታወቀም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሀይሎች የፈጠሩት ስጋት እና ለሰራዊቱ አባላት ያቀረቡት የትግል ጥሪ መንግስት እርምጃውን እንዲወስደ አስገድዶታል ብለዋል። በኤርትራ ድንበር እየታየ ያለው አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን የማከማቸቱ ዘመቻም ምናልባትም ከኤርትራ ጋር አንድ ዙር ጦርነት ሊካሄድ ከቻለ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን እግዛ ከወዲሁ ለመፈለግ ይሆናል የሚሉ አስተያየቶችም ቀርበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመከላከያ ባለስልጣናትን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment