Saturday, December 7, 2013

ሳይጠሩት አቤት የመለስ ዜናዊ ጎረቤትእቺ አባባል ተሻሽላ ገና በጠዋቱ አፌ ላይ መጥታ አገልግሎት ላይ እየዋለች ትገኛለች። ባትሻሻልም ታስሄዳለች። 

ማንዴላን የመሰለ ለእኩልነት፣ ለነፃነት የታገለ ታላቅ መሪ እና በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ዘረኝነትን ያሰፈነን፣ እንደውም የነበረንን ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት ያፈረሰብንን አንድ መዥገር አምባገነን ሰውዬን ሞት አንድ ስለአደረጋቸው ብቻ "አፍሪቃ ሁለት ዕንቁወች አጣች" (ይታያችሁ ማርና ሬት ያለውን ልዩነት) እያሉ መለስን ያለ ቦታውና ያለ ክብሩ ክብር ለማልበስ እያደረጉ ያለውን ቅጥፈት ታዘብሁና መለስ የሰፈራቸው ልጅ ስለነበረ ነው አዴል እንድህ ቁምስቅሉን የሚያሳዮት በማለት "ሳይጠሩት አቤት የመለስ ዜናዊ ጎረቤት" ለማለት ተገድጃለሁ! 

በነገራችን ላይ ኔልሰን ማንዴላ በህይወት እያለ መለስ ዜናዊን እና ፓርቲውን ህወሓት/ኢአዴግን እንዴት ይጠየፍ እንደነበረ ብያውቁ ኖሮ ዛሬ መለስና ማዲባን አንድ ሊያደርጉአቸው ባልተሯሯጡ ነበር።

የዘረኝነት ልክፍት ለካ ከእብደት አይተናነስም!? መለስና ማዲባን በአንድ አይን ማየት ማለት ለኔ ከእብደት ውጪ የተለየ ትርጉም አይሰጠኝም።

Metasebia,


No comments:

Post a Comment