Monday, December 16, 2013

ደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራን አከሸፈች- ፕሬዚዳንት ኪር

ደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራን አከሸፈች- ፕሬዚዳንት ኪር

Image










የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የቀድሞው የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ታማኞች የነበሩ ወታደሮች ያካሄዱት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን ይፋ አደረጉ።
ለሊቱን የአገሪቱ መዲና ጁባ በተኩስ ውስጥ ማደሯን ተከትሎ ነው ኪር መግለጫውን የሰጡት።
በመዲናዋ ጁባ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ እስከዛሬ ማለዳ ድረስ ዘለቆ ነበር።
ፕሬዚዳንት ኪር እንዳሉት፥ ዩኒፎርም ያላደረጉ ወታደሮች በሱዳን ህዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ /ኤስ ፒ ኤል ኤም/ ስብሰባ ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ግጭት መቀስቀሱን ነው ያስረዱት።
መንግሰት በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ አገሪቱን መዲና መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ ኤስ ፒ ኤል ኤም በደቡብ ሱዳን ስልጣን በሀይል እንዲተላለፍ አይፈቅድም ብለዋል በመግለጫው ላይ።
ሳልቫ ኪር ታማኝ አፍርተዋል ያሏቸውን ምክትላቸው የነበሩት ሪክ ማቻር ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ካቢኒያቸውን ሲያፈርሱ አብረው ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል።
ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው መግለጫ የሰጡት ኪር ከዛሬ ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱንም ይፋ አድርገዋል።
ከጁባ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የመዲናዋ የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ የተዘጋ ሲሆን፥ የአገሪቱም የቴሌቪዥን ጣቢያም ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር።

No comments:

Post a Comment