Thursday, December 19, 2013

አቶ ምህረት ደበበ እንደመብራት ቆጣሪ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

አቶ ምህረት ደበበ እንደመብራት ቆጣሪ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የቀድሞው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በግምገማ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገለፁ። በትላንትናው እለት የቀድሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት መከፈልን አስመልክተው በሂልተን ሆቴል መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ በኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት የስራ አፈፃፀም ላይ በሰራተኞቹም ሆነ በከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ በተደረገ ግምገማ ዋና ስራ አስፈፃሚውን አቶ ምህረትን ጨምሮ ማኔጅመንቱ መስራት የሚገባውን ያህል ስላልሰራ በግምገማ ለውጥ የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አቶ ምህረት ከኃላፊነታቸው መነሳት ብዙዎችን ያስደነገጠ ቢመስልም በሰራተኛው በኩል ግን ሲጠበቅ የነበረ መሆኑ ኃላፊው አመልክተዋል። በማኔጅመንቱ በኩል ባሉት ችግሮች ላይ ከሰራተኛው ጋር ተነጋግሮ መስመር የማስያዝና ባለው አቅም ያለመስራት ችግሮች የነበሩ መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን ጨምረው ገልፀዋል። አቶ ምህረት በነበራቸው አፈፃፀም ኮርፖሬሽኑ በተፈለገው ደረጃ ባለመመራቱ በነበራቸው የስራ ዘመን ያስመዘገቧቸው አዎንታዊ የስራ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተካሄደው ግምገማ ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በሚል ለሁለት መከፈሉን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አሁን ባለው አዲስ አደረጃጀት ኃይል አመንጪውና አገልግሎት ሰጪ የተለያየ ኩባንያ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የግልገል ጊቤ ሶስት ፕሮጀክት ዋና ሥራአስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ መሆናቸው ታውቋል። ሁለተኛውን ማለትም የአገልግቱን ዘርፍ በማኔጅመንት ኮንትራት ደረጃ የሚመራው ፓወር ግሬድ የተባለው የህንድ ኩባንያ ነው።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ወደ 13ሺህ 375 አካባቢ ሰራተኞች የነበሩት መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን አስታውሰው እነዚህ ሰራተኞች በአዲስ መልኩ በሚደራጁት ሁለቱም ኩባንያዎች ውስጥም በሥራቸው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ኩባንያዎቹ 4ሺህ100 ተጨማሪ የሰው ኃይል ክፍተት ስለሚታይባቸው በቀጣይም ሰፊ ቅጥር የሚያስፈልግ መሆኑን በማመልከት የሰው ኃይሉንም ክፍተት ለሚሟላት በቅርቡ ቅጥር የተጀመረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ነባሩን ሰራተኛ ባለው የትምህርት ደረጃ፣ ልምድና ክህሎት በአዲስ መልኩ የመመደብ ስራ የተጀመረ መሆኑን በመግለፅ ይህም ከላይ የተጀመረው ምደባ ወደታች የሚወርድ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

የቀድሞው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በግምገማ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገለፁ። 
በትላንትናው እለት የቀድሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት መከፈልን አስመልክተው በሂልተን ሆቴል መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ በኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት የስራ አፈፃፀም ላይ በሰራተኞቹም ሆነ በከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ በተደረገ ግምገማ ዋና ስራ አስፈፃሚውን አቶ ምህረትን ጨምሮ ማኔጅመንቱ መስራት የሚገባውን ያህል ስላልሰራ በግምገማ ለውጥ የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አቶ ምህረት ከኃላፊነታቸው መነሳት ብዙዎችን ያስደነገጠ ቢመስልም በሰራተኛው በኩል ግን ሲጠበቅ የነበረ መሆኑ ኃላፊው አመልክተዋል።
 በማኔጅመንቱ በኩል ባሉት ችግሮች ላይ ከሰራተኛው ጋር ተነጋግሮ መስመር የማስያዝና ባለው አቅም ያለመስራት ችግሮች የነበሩ መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን ጨምረው ገልፀዋል። 
አቶ ምህረት በነበራቸው አፈፃፀም ኮርፖሬሽኑ በተፈለገው ደረጃ ባለመመራቱ በነበራቸው የስራ ዘመን ያስመዘገቧቸው አዎንታዊ የስራ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተካሄደው ግምገማ ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በሚል ለሁለት መከፈሉን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አሁን ባለው አዲስ አደረጃጀት ኃይል አመንጪውና አገልግሎት ሰጪ የተለያየ ኩባንያ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የግልገል ጊቤ ሶስት ፕሮጀክት ዋና ሥራአስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ መሆናቸው ታውቋል። ሁለተኛውን ማለትም የአገልግቱን ዘርፍ በማኔጅመንት ኮንትራት ደረጃ የሚመራው ፓወር ግሬድ የተባለው የህንድ ኩባንያ ነው።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ወደ 13ሺህ 375 አካባቢ ሰራተኞች የነበሩት መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን አስታውሰው እነዚህ ሰራተኞች በአዲስ መልኩ በሚደራጁት ሁለቱም ኩባንያዎች ውስጥም በሥራቸው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ኩባንያዎቹ 4ሺህ100 ተጨማሪ የሰው ኃይል ክፍተት ስለሚታይባቸው በቀጣይም ሰፊ ቅጥር የሚያስፈልግ መሆኑን በማመልከት የሰው ኃይሉንም ክፍተት ለሚሟላት በቅርቡ ቅጥር የተጀመረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ነባሩን ሰራተኛ ባለው የትምህርት ደረጃ፣ ልምድና ክህሎት በአዲስ መልኩ የመመደብ ስራ የተጀመረ መሆኑን በመግለፅ ይህም ከላይ የተጀመረው ምደባ ወደታች የሚወርድ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

No comments:

Post a Comment