Saturday, December 14, 2013

ሰሞኑን አዲስ አበባ ማንዴላ አልሞተም።የእኛ ማንዴላ መንግስቱ ኃይለማርያም ነው።የሚሉ ድምፆች ተበራክተዋል።

የኮ/ል መንግስቱ ድምፅ በኢሳት መሰማቱ በዘመነ ኢሕአዲግ የተወለዱት የ 20 እና የ 22 ዓመት ወጣቶች ዘንድ ልዩ ስሜት ፈጥሯል።
ማንዴላን እና ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያምን የማመሳሰል ሁኔታዎች በደርግ ዘመን በተራው ሕዝብ ዘንድ ነበር።እንዲሁ ጥሎበት ህዝቡ ሁለቱን ማዛመድ ይወድ ነበር።በእዚህ ሳምንት ኮ/ል መንግስቱ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ካደረጉ ወዲህ በሀገር ቤት በተለይ በዘመነ ኢሕአዲግ የተወለዱት የ 20 እና የ 22 ዓመት ወጣቶች ዘንድ ልዩ ስሜት ፈጥሯል።ታሪክ እንግዲህ እንዲህ ነው።ጊዜ እና ወቅት ይፈልጋል።ከኢትዮጵያ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ወጣቶቹ ስለ ኮ/ል መንግስቱ መንግስት ታላላቆቻቸው በሶስት ጉዳዮች ሲያደንቁ እየሰሙ ማደጋቸው ለዛሬው ኮ/ል መንግስቱን ለማድነቅ እና ለማክበር አብቅቷቸዋል።

1/ በሱማሌ ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያ የሚረዳት ባጣችበት ወቅት በአጭር ጊዜ ከ 300ሺህ ያላነሰ ጦር አነቃንቀው የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበራቸውን፣

2/ ዓለም አቀፍ ሽልማት ከዩነስኮ ሳይቀር ያተረፈላቸው መሃይምነት ለማጥፋት ያደረጉትን ዘመቻ እና 

3/ 'ድሃ - ተኮር' የሆነ እስከ ታች ቀበሌ ድረስ መሰረታዊ ሸቀጦች እንዲዳረሱ የዘረጉት መዋቅር የሚሉትን ከብዙ በጥቂቱ በምሳሌነት የጠቅሳሉ

ከሁሉም በላይ እነኝህ ወጣቶች በዘመነ ኢህአዲግ የከተማ ነዋሪዎች ለፍተው የሰሩት ቤት በላያቸው ላይ ክፍለ ከተማ ሲያፈርሰው አይተዋል፣መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ የማይቀመስ መሆኑን አስተውለዋል፣ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ጎሳ እና ዘር የሚያስቀድም መንግስት ቤተ መንግስት ገብቶ ሀገር ሲያተራምስ ተመልክተዋል።እናም ከመወለዳቸው በፊት ስለነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ለማድነቅ ምክንያታቸው የሚናቅ አይደለም።ሰሞኑን አዲስ አበባ ማንዴላ አልሞተም።የእኛ ማንዴላ መንግስቱ ኃይለማርያም ነው።የሚሉ ድምፆች ተበራክተዋል።
ሰሞኑን አዲስ አበባ ማንዴላ አልሞተም።የእኛ ማንዴላ መንግስቱ ኃይለማርያም ነው።የሚሉ ድምፆች ተበራክተዋል።

የኮ/ል መንግስቱ ድምፅ በኢሳት መሰማቱ በዘመነ ኢሕአዲግ የተወለዱት የ 20 እና የ 22 ዓመት ወጣቶች ዘንድ ልዩ ስሜት ፈጥሯል።
ማንዴላን እና ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያምን የማመሳሰል ሁኔታዎች በደርግ ዘመን በተራው ሕዝብ ዘንድ ነበር።እንዲሁ ጥሎበት ህዝቡ ሁለቱን ማዛመድ ይወድ ነበር።በእዚህ ሳምንት ኮ/ል መንግስቱ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ካደረጉ ወዲህ በሀገር ቤት በተለይ በዘመነ ኢሕአዲግ የተወለዱት የ 20 እና የ 22 ዓመት ወጣቶች ዘንድ ልዩ ስሜት ፈጥሯል።ታሪክ እንግዲህ እንዲህ ነው።ጊዜ እና ወቅት ይፈልጋል።ከኢትዮጵያ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ወጣቶቹ ስለ ኮ/ል መንግስቱ መንግስት ታላላቆቻቸው በሶስት ጉዳዮች ሲያደንቁ እየሰሙ ማደጋቸው ለዛሬው ኮ/ል መንግስቱን ለማድነቅ እና ለማክበር አብቅቷቸዋል።

1/ በሱማሌ ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያ የሚረዳት ባጣችበት ወቅት በአጭር ጊዜ ከ 300ሺህ ያላነሰ ጦር አነቃንቀው የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበራቸውን፣

2/ ዓለም አቀፍ ሽልማት ከዩነስኮ ሳይቀር ያተረፈላቸው መሃይምነት ለማጥፋት ያደረጉትን ዘመቻ እና

3/ 'ድሃ - ተኮር' የሆነ እስከ ታች ቀበሌ ድረስ መሰረታዊ ሸቀጦች እንዲዳረሱ የዘረጉት መዋቅር የሚሉትን ከብዙ በጥቂቱ በምሳሌነት የጠቅሳሉ

ከሁሉም በላይ እነኝህ ወጣቶች በዘመነ ኢህአዲግ የከተማ ነዋሪዎች ለፍተው የሰሩት ቤት በላያቸው ላይ ክፍለ ከተማ ሲያፈርሰው አይተዋል፣መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ የማይቀመስ መሆኑን አስተውለዋል፣ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ጎሳ እና ዘር የሚያስቀድም መንግስት ቤተ መንግስት ገብቶ ሀገር ሲያተራምስ ተመልክተዋል።እናም ከመወለዳቸው በፊት ስለነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ለማድነቅ ምክንያታቸው የሚናቅ አይደለም።

No comments:

Post a Comment